“አቶ ጌታቸው ረዳ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ናቸው” – አቶ አማኑኤል አሰፋ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው ቡድን ባካሄደው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመኾናቸው ፕሬዝደንትነታቸውን እንደማይቀበል፣ በቅርቡ በተካሄደው አወዛጋቢ የህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ኾነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ ተናገሩ።

አቶ አማኑኤል ዛሬ መቐሌ ላይ በሰጡት መግለጫ አቶ ጌታቸውን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሲሉ ጠርተዋቸዋል።…