በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሕገ ወጥ የነዳጅ ንግድ በመስፋፋቱ በከተማዋ ለቀናት የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ተጠቃሚዎች ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። በከተማው በተለይም በማደያ በ93 ብር ገደማ የሚሸጠው አንድ ሊትር ቤንዚን በአሳቻ ሰዓት ከማደያ እየወጣ በድብቅ እስከ 250 እየተሸጠ መኾኑን ገልጸዋል።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ተሰማርተው ነዳጅ ሲሸጡ እና ሲያዘዋወሩ ተ…