አምነስቲ፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በሦስት ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የጣሉትን እገዳ ባስቸኳይ እንዲያነቡ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
ድርጅቱ፣ እገዳው “ግልጽነት የጎደለው” እና “ባልተረጋገጡ ውንጀላዎች ላይ የተመሠረተ” እንደኾነ ገልጧል።
እገዳው ከጅምሩም መጣል አልነበረበትም ያለው ድርጅቱ፣ ውሳኔው በሲቪል ማኅበረሰብ ምኅዳር ላይ የተቃጣ ነው በማለት ወቅሷል።
አምነስቲ፣ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትም ለኢትዮጵያ ያለውን አተያይ እንዲፈትሽና በትግራይ፣ አማራና ኦሮሚያ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምር ጠይቋል።