“አዋጆቹ ከህጋዊ ተፈጻሚነታቸው ይልቅ የፖለቲካ መሳሪያ የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው”

“አዋጆቹ ከህጋዊ ተፈጻሚነታቸው ይልቅ የፖለቲካ መሳሪያ የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው”

👉 አዋጆቹ የዜጎች ንብረት የማፍራትና ሰብአዊ መብት የሚጠብቁ ናቸው – ፍትህ ሚኒስቴር

በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ እርጎ የማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ተግባርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ ረቂቅ አዋጅ በፓርላማው ክርክርና ጥያቄ አስነስቷል፡፡

በረቂ አዋጁ ውስጥ የተካተቱ በሽብር የተጠረጠረን አካል ንብረት ማገድ፣የልዩ ምርመራ ሂደት እንዲሁም የመያዣ ትእዛዝን እስከ 3 ዓመት እንዲጸና የሚያስቀምጡ ድንጋጌዎችና ሌሎች ጉዳዮች ላይም የምክርቤቱ አባላት በጥያቄና በስጋት መልክ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡

በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ አካላትን ለመመርመር በልዩ ሁኔታ እስከ 120 ቀን ወይም 4 ወር የሚወስደው የምርመራ ሂደት ተራዛሚና ዜጎችም በፍትህ ስርአቱ ላይ ጥያቄ እንዲያስነሱ የሚያደርግ ነው ሲሉም ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

እንደዚህ አይነት አዋጆች ከህግ ተፈጻሚነታቸው ይልቅ የፖለቲካ መሳሪያ የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው ያሉት እንደራሴዎቹ ይህ ደግሞ የአዋጁ ተግባራዊነት ላይ ጥያቄ እንዲነሳ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አዋጁን የደገፉ የፓርላማ አባላት እንደዚህ አይነት አዋጆች ከዚህ ቀደም ንብረትን ለተፈለገ የወንጀል ተግባር የማዋል ሂደትን ይከላከላል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

የፍትህ ሚኒስትሯ ሃና አርዓያስላሴ አዋጆቹ የዜጎች ንብረት የማፍራትና ሰብአዊ መብት የሚጠብቁ ናቸው ሲሉ የአዋጆቹ አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በአዋጆቹ ላይ ውይይት ከተደረገም በኋላ ለዝርዝር እይታ ወደ ህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ተልከዋል፡፡