ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ሰሜን ኮሪያ ለደቀነችው አደጋ የሶስትዮሽ የትብብር ምላሽ እየተዘጋጁ መሆናቸው ተገለጠ

ሰሜን ኮሪያ፣ ሩስያ ዩክሬን ውስጥ እያካሄደች ያለችውን ጦርነት በመደገፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችቿን ወደ ሥፍራው መላኳን ተከትሎ እና ፒዮንግያንግ በኒውክሌር ፕሮግራሟ አማካኝነት ለደቀነችው አደጋ የተባበረ ምላሽ ለመስጠት በታለመ እቅድ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ አርብ ከደቡብ ኮሪያ እና ከጃፓን አቻዎቻቸው ጋር ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ተገለጠ። ሶስቱ መሪዎች የሚወያዩት ሊማ ፔ…