በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የሁለት ዓመታ ሕጻን ታግታ ከተወሰደች በኋላ ትናንት ሰኞ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም. ተገድላ አስክሬኗ በወላጆቿ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ።የሕጻኗን በአጋቾቿ ተገድሎ መጣል አስመልክቶ የተቆጡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በትናንትናው ዕለት አደባባይ የወጡ ቢሆንም፣ ከከተማዋ የጸጥታ ኃይሎች ጋር መጋጨታቸውን እና ጉዳት መድረሱን የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
…