“መለስ ታመመ” የሚለውን ወሬ ተከትሎ፣ ኮማ ውስጥ መግባቱና መሞቱ እየተነገረ ሰንብቶአል። የወያኔ መንግስት ግን ወሬውን አፍኖ ለመቆየት ተጨናነቀ። መለስ ጀርመን ሃገር ላይ ቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉ በአንድ ወገን ሲገለፅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ቤልጅየም 10 ቀናት አልጋ ይዞ መሰንበቱ ተሰምቶአል።
“አዲሳባ …
“መለስ ታመመ” የሚለውን ወሬ ተከትሎ፣ ኮማ ውስጥ መግባቱና መሞቱ እየተነገረ ሰንብቶአል። የወያኔ መንግስት ግን ወሬውን አፍኖ ለመቆየት ተጨናነቀ። መለስ ጀርመን ሃገር ላይ ቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉ በአንድ ወገን ሲገለፅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ቤልጅየም 10 ቀናት አልጋ ይዞ መሰንበቱ ተሰምቶአል።
“አዲሳባ …
ይህን ከመፃፌ በፊት አልጀዚራ እያየሁ ነበር። ያሲር አረፋት የተገደለው (…he might have been poisoned with polonium, a rare radioactive isotope. ) ተመርዞ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም ወሬ አወጁ። ልብሱና የጥርስ ብሩሹን ስዊዘርላንድ ላይ በመመርመር የተገኘውን ውጤት ዋቢ በማድረግ፣ አራፋት 2004 ላይ …
ከተስፋዬ ገብረአብ
“አበበ ባልቻ – እንደ ሕወሓት” በሚል ርእስ ‘ሰውለሰው’ በሚለው ድራማ ላይ የፃፍኩትን ተከትሎ አንዳንድ አስተያየቶችን ሳነብ ቆይቻለሁ። አበበ ባልቻ ሕወሓትን ወክሎ ሲተውን እንደነበር በብዙዎች ዘንድ ታምኖበታል። የአስናቀ አወዳደቅ የሕወሓት (አዜብ / መለስ)ን ፍፃሜ የሚያመለክት ስለመሆኑም ሰፊ ግንዛቤ አለ።…
ከተስፋዬ ገብረአብ
“ሰው ለሰው” የተባለው ድራማ በድንገት ከመጠናቀቁ ጋር በተያያዘ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። ትኩረቴን የሳበው ግን ስለ ተዋንያኑ ውክልና ፌስ ቡክ ላይ የተሰራጨው ወግ ነው። ይችን ቁራጭ መታጥፍ ለመክተብ መነሻ ሆኖኛል።
አበበ ባልቻ ሲተውነው የቆየው ገፀባህርይ (አስናቀ አሸብር) እንደ …
ከብዙ አመታት በፊት ተፈሪ መኮንን የሚባል አንድ ወጣት ደጃዝማች በሃረር አካባቢ ይኖር ነበር። እና ኑሮውን በሰላም በመኖር ላይ ሳለ አንድ ቀን ያልጠበቀው ነገር ገጠመው። ተፈሪ እንደወትሮው ጸሎት ላይ ሳለ ስልክ እንደሚፈልገው ተነገረው። የደወለለት የአጤ ምኒልክ ዙፋን ወራሽ ልጅ እያሱ ነበር። …
ከተስፋዬ ገ/አብ
“የእናቷን ውበት ወርሳለች” ይሏታል። ርግጥ ነው፣ ወይዘሮ ላቀች ይህ ቀረሽ የማይባሉ ደርባባ ወይዘሮ ነበሩ። የቀድሞ የወጣትነት ወዘናቸው ወደ ልጃቸው ተሻግሮ ማየት ችለዋል። በዚህም ተባለ በዚያ ልጅቱ የንጉስ ተክለሃይማኖት ሴት ልጅ ናት። ስምን መልአክ ያወጣዋልና ስሟ ንግስት ይባላል። ስለዚህ …
ከተስፋዬ ገ/አብ
የኮሎኔል መንግስቱን መፅሃፍ ሳነብ ከገረሙኝ ነገሮች አንዱ የኮሎኔል ጎሹ ወልዴን ስም አለመጥቀሱ ነበር። ቢያንስ፣ “የታጠቅ ጦር ሰፈር አመሰራረት” በሚለው ምእራፍ ስር እንኳ ስሙን ሊያነሳው በተገባ።
በቂ ምክንያት ማቅረብ ባልችልም ስለ ኮሎኔል ጎሹ በጎ ስሜት አለኝ። ምናልባት የመንግስቱን ስርአት …
ወደ ጎንደር የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ለማስተማር የመጣ አንድ ጀርመናዊ ሃኪም አንዲት የገበሬ ሚስት እያከመ ነበር። እንዴት ሾልኮ እንደገባ ባይታወቅም የሴትየዋ ባል ከሚስቱ ራስጌ ላይ ቆሟል። ገበሬው የታመመች ሚስቱን በስስት አይን፣ ፈረንጁን ሃኪም ደግሞ በተስፋ ይመለከታል። ጀርመናዊው ሃኪም ቆጣ ብሎ ከሚስቱ …
ከተስፋዬ ገ/አብ
ወቅታዊውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ የሃይል አሰላለፍ በመገምገም፣ “መለስ ዜናዊ! – በማን ይተካል?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ መስጠት በርግጥ ቀላል አይደለም። በቅድሚያ ግን “በርግጥ መለስ ዜናዊ ስልጣኑን ይለቃል?” ብሎ መጠየቅ ይገባል። መለስ ዜናዊ፣ “ከሁዋላ ሆኜ ማገዜ ባይቀርም፣ እለቃለሁ” ብሎ ደጋግሞ ነግሮናል። …
ርግጥ ነው ሰሞኑን ወያኔ በጣም ተጨናንቆአል።
ለአመፅ እርሾ ሊሆኑ በሚችሉ ቁጣዎች ተከበዋል። የሶማሊያ ተልእኮ እየከሸፈ ነው። አልሸባብ እያሸመቀ ደጋግሞ አደጋ መጣሉን በመቀጠሉ፣ ከዚህ በላይ ሶማሊያ መቆየት እንደማይችሉ ተረድተው ጓዛቸውን መሸከፍ ይዘዋል። ከኤርትራ ጋር የጀመሩት የጦርነት ድራማ፣ ላይ ላዩን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ …
ከተስፋዬ ገብረአብ
ትረካውን ጥቂት አሰማምሬው ይሆናል እንጂ ይህ የምገልፅላችሁ ታሪክ በትክክል የተፈፀመ ነው። ታሪኩን ካጫወተኝ ሰው ጋር ስናወራ፣
“ልፃፈው?” ስል ጠየቅሁት።
ሳቀ! በጣም ሳቀ! እና ፈቀደልኝ።
“ፃፈው! ድክመታችንን ያሳያል …” አለ።
* * *
ባጭር ጊዜ ውስጥ የታቀደ ነበር። በረቀቀ …
ሰሞኑን “አዲስ ነገር – ድረገፅ” የለጠፋቸውን የዜና ጭማቂዎች ሳነብ ትኩረት የሚስብ ርእስ ገጠመኝ። ይህም ካርል ሄንዝ ለተባሉ ጀርመናዊ አዲሳባ ላይ ሃውልት ሊቆምላቸው የመወሰኑ ዜና ነበር።
ለመሆኑ እኒህ ሰው ማናቸው? ማነው የወሰነላቸው? በምን መለኪያ? ከማን ጋር ተወዳድረው? ለኢትዮጵያ ምን በጎ ቢሰሩ …
ከተስፋዬ ገብረአብ
(pdf)
ከጥቂት ቀናት በፊት ‘ብዙ ወንድምአገኝ’ ከካናዳ ስልክ ደውላ እንዲህ ስትል ጠየቀችኝ፣
“ምነው ጠፋህ ታዲያ?”
መልስ ከመስጠቴ በፊት በግሳፄ እንዲህ ቀጠለች፣
“በአመት አንድ መፅሃፍ መፃፍ በቂ ይመስልሃል? ከሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ስለ ቀድሞ አለቆችህ አንድ …
በዚህ ሰሞን “የዋህ አዛውንት” በሚል ርእስ ያሰፈርኩትን አጭር መጣጥፍ አስመልክቶ አንዳንድ አሉታዊ አስተያየቶችን አንብቤያለሁ። እናም “ዶክተር ነጋሶ ተርበዋል፣ ተጠምተዋል” በሚል ርእስ ታትሞ ያነበብኩት ቃለመጠይቅ እጅግ እንዳስገረመኝ ተጨማሪ አስተያየት ማከሉን ወደድኩ።
ዶክተር ነጋሶ የቤታቸው ጣሪያ ውሃ እንደሚያፈስና ቀዳዳውን በላስቲክ እየሸፈኑ ክረምቱን …
በስደት በከተምኩባት የስደት ጎጆዬ በፀጥታ ተቀምጬ፣ “የስደተኛው ማስታወሻ”ን የአርትኦት ስራ እየሰራሁ ሳለ አንድ ጓደኛዬ የኢሜይል መልእክት ላከልኝ።
“ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ስላንተ ተናግረዋልና አንብበው” የሚል ነበር መልእክቱ።
በተጠቆምኩት ሊንክ ገብቼ ቃለመጠይቁን አነበብኩት። እናም በእውነቱ የነጋሶ ቃለመጠይቅ ልቤን ክፉኛ ስለነካው፣ የአርትኦት ስራዬን …
ወያኔ ጉባኤውን አዳማ ላይ አካሄደ።
እናም ጉባኤው በአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ንግግር ተቋጨ። መለስ ዜናዊም በሃይሌ ንግግር ሲስቅ በቴሌቪዥን ተመለከትነው። መለስ ዜናዊ፣ “በአምስት አመታት አጠናቅቀዋለሁ” ያለውን ትንግርታዊ፣ አስማታዊና ሰማያዊ የልማት እቅድ ዶክተር ሃይሌ ከመለስ ብሶ፣ “በሁለት አመታት እንጨርሰዋለን” ሲል ቃል ገባ። …
እነሆ! “የስደተኛው ማስታወሻ” የተባለው መድፍ ተሰርቶ ተገባዶአል…
በዚህ አያያዜ ቶሎ የምጨርሰው ይመስለኛል። “ስደት” ርእሰ ጉዳዩ ሰፊ ነው። ይፃፍ ከተባለ 20 ጥራዝም አይበቃው። ሆኖም አጀንዳዬ ከሃገራችን ፖለቲካ ሊያፈነግጥ እንደማይችል ግልፅ ነው። የአብዛኛው የስደት ምክንያቱ ፖለቲካውም አይደል? በመሆኑም ስደትና ፖለቲካውን ከወቅታዊ ጉዳዮቻችን …
የነሱን ቢራ ከምትጠጣ ለነፃነትህ ውሃ ጠጣ!!
እንግዲህ ይሄ ዳሸን ቢራና ፔፕሲኮላን የሚመለከት ሊሆን ይችላል።
እነሱ ያመረቱትን ከምትለብስ የተቀደደ ልብስ ልበስ!
የአልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ Made in USA የሚል ታግ እየለጠፈ የአዲስአበባን ገበያዎች ማጥለቅለቁን ያውቃሉ? ከዱባይ ኮንቴይነር እያስጫኑ፣ ያለቀረጥ እያስገቡ ትርፍ ስለሚዝቁ …
ስዬ አብርሃ የፃፈውን መፅሃፍ አነበብኩት።
የተደጋገመውን ዝባዝንኬ እየዘለልኩ እንደምንም ጨረስኩት። የስዬ ወንድሞች የገዟቸው መኪኖች የሻንሲ ቁጥር ምንም ስለማያደርግልኝ እየነጠርኩ አልፌዋለሁ።
ስዬ ላይ አልፈረድኩበትም።
ከነበረበት የስልጣን ደረጃ ጋር የሚመጣጠን የማንበብ ልምድ እንደሌለው ይታወቃል። በአናቱ የተፈጥሮ እብሪቱ ሲታከልበት ማንኛውም የተጠረዘ ነገር ሁሉ …