Blog Archives

የአማራና የቤንሻንጉል ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት የተፈናቀሉ አማሮችን አወያይተዋል፡፡

Update፡- የዛሬ አርብ (03/9/2010 ዓ.ም) የተፈናቃዮች ሁኔታ የአማራና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት የተፈናቀሉ አማሮችን ትላንት በ02/9/2010 ዓ.ም አወያይተዋል፡፡ የአማራ ክልል ባለስልጣናት በአቶ ንጉሱ ጥላሁን የተመሩ ሲሆን ከቤንሻንጉል የመጡ የክልል ፣ የወረዳና የቀበሌ አመራር አባላትም ተሳትፈዋል፡፡ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የመጡ አንዳንድ አመራሮች በወቅቱ የነበረዉ ችግር ከነርሱም አቅም በላይ እንደነበር ገልፀዉ ፣ ተፈናቃዮች የደረሰባቸዉ ችግርና የደህንነት ስጋት ትክክለኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብአዴን አስተባባሪዎችም በዉይይቱ ወቅት እንኳን የተፈናቃዮች የነርሱም ህይወት አደጋ ላይ ወድቆ እንደነበር አሳዉቀዋል፡፡ ……………………………………… በዉይይቱ ላይ እንደመፍትሄ የቀረበላቸዉ ጉዳይ ይኖሩባቸዉ የነበሩ የቤ.ጉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ስለተረጋጉ ወደነበሩበት አካባቢ እንዲመለሱ ሲሆን ፣ የሁለቱ ክልሎች መንግስታት በጽሁፍ የተደገፈ የደህንነት ዋስትና ካልሰጡን አንመለስም ብለዋል፡፡ አማራ ክልል ወደሚገኙ ዘመዶቻቸዉ እንዲመለሱ ሲጠየቁ ፤ እንኳን አሁን አግብተን ወልደን ፣ አንድ የነበርነዉ ሶስት አራት ሆነን ቀርቶ በፊት አንድ ራሳችንን እንኳ የሚስተዳድሩበት መሬትም ሆነ ሌላ ሃብት ቤተሰቦቻችን የሌላቸዉ በመሆኑ ወደ ሌላ አካባቢ እንጀራ ፍለጋ እንደሄዱ አስታዉሰዉ ፤ በቋሚነት ቀርቶ በእንግድነት እንኳ ሊያስተናግዱን አቅም የላቸዉም ብለዋል፡፡ ……………………………………… ወደነበርንበት እንድንመለስ ዋስትና መስጠት የማትችሉ ከሆነ በክልሉ ለእርሻ ኢንቨስትሜንት ከተከለሉ አካባቢዎች ባንዱ የእርሻ መሬት ሰጥታችሁ አስፍሩን ወይም ደግሞ በከተማ ልማት አደራጅታችሁ አቋቁሙን የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ በዉይይቱ ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ገብረ ጻድቅ የተፈናቃዮቹ ጥያቄ ተገቢ እንደሆነና መሬት ከሰጣችኋቸዉ ወገናቸዉ ያቋቁማቸዋል የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡ በመጨረሻም ባለስልጣናቱ በሉ እናንተም ከህዝቡና ከሃይማኖት አባቶች
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማሽ ዞን የቅዱስ ገብርኤል ደብር ሃላፊና ቀሳውስት ተፈናቀሉ።

ቀሳውስቱንም አሳደዷቸው! (ጌታቸው ሽፈራው) የተረጋገጠ የመሬት ይዞታ እያላቸው፣ የመሬት ግብር እየከፈሉ የተባረሩበት ሰበብ አንድ ሰው በመገደሉ ነው። ቀሳውስት የሚያስተምሩት የእግዚያብሔርን ቃል ነው። ከቃሉ ዋነኛው ደግሞ “አትግደል” ነው። ሆኖም ግብር ሲያስከፍላቸው የኖረው የቤንሻንጉል ክልል መንግስት ቀሳውስቱ ለሚቃወሙት ወንጀል በጅምላ ተጠያቂ አደረጋቸው። እናቶችን፣ ህፃናትን፣ ምስኪን ገበሬዎችን በጅምላ እንዳባረረው ቀሳውስትንም አሳደዳቸው። እንደ እግዚያብሔር ፈቃድ ሆኖ ህይወታቸውን ተርፏል። በምስሉ የሚታዩት ቄስ እንኳሆነ ቸሬ ይባላሉ። በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማሽ ዞን ጅንጋፎይ ወረዳ፣ በለው ደዲሳ ቀበሌ የሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ኃላፊ ነበሩ። በግል ፀብ ምክንያት “ሰው ተገደለ” ተብሎ በጅምላ ከ2000 በላይ ሕዝብ ሲባረር የቅድስ ገብርኤሉን ኃላፊ ቄስም አሳድደዋቸዋል። ቄስ እንኳሆነ ቼሬ ሜዳ ላይ ከወደቁትና በአሁኑ ወቅት የጤና እክል ከገጠማቸው ተፈናቃዮች መካከል ናቸው። ከቄስ እንኳሆነ በተጨማሪ ሌሎች 14 ቀሳውስትንም አሳድደዋቸዋል። “አትግደል” እያሉ ከሚያስተምሩበት ደብር ከተፈናቀሉት ቀሳውስት መካከል:_ 1) ቄስ እንኳሆነ ቼሬ 2)ቄስ ምንአለ አያሌው 3) ቄስ ጎጃም በየነ 4) ቄስ ውበቱ እንየው 5)ቄስ አዲስ አንተነህ 6)ቄስ በለጠ ንጉሴ 7)ቄስ መንክር ውቤ 8ኛ )ቄስ ጫኔ ታደሰ 9) ቄስ ሀብታሙ ሽበሽ 10)ቄስ አደመ መኮንን 11)ቄስ የሽዋስ የኋላው 12)ቄስ ላቀው መንግስቴ 13)ቄስ ስልጣኑ ከፍአለ 14)ቄስ አበበ በእውቀቱ 15)ቄስ አበበ መልሰው ይገኙበታል። ሌሎች በስም ያልተጠቀሱ ቀሳውስትም እንደተፈናቀሉ ለማወቅ ተችሏል
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከተፈናቀሉት መካከል የ340 አባውራና እማውራዎች ዝርዝር ( ጌታቸው ሽፈራው )

ከተፈናቀሉት መካከል የ340 አባውራና እማውራዎች ዝርዝር ( ጌታቸው ሽፈራው ) ጥቅምት 16/2010 ዞነ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማሺ ዞን ከበለው ጅጋንፎይ ወረዳ በለው ደዴሳ ቀበሌ በሁለት ግለሰቦች ፀብ አንድ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተወላጅ በመገደሉ ምክንያት የይዞታ ማረጋገጫ እያላቸው “ህገ ወጥ ተብለው ከተባረሩት የአማራ ተወላጆች መካከል የ340 አባውራዎችና ባው እና እማውራዎች መካከል ያስተዳድሩት የነበረው ቤተሰብ ቁጥር ከስር በዝርዝር ቀርቧል። በዝርዝሩ የቀረበው የ340 አባውራዎች እና እማውራዎች ዝርዝር ሲሆን የተፈናቀሉት 527 አባውራና እማውራዎች ናቸው። 1)ቄስ ምንአለ አያሌው (የቤተሰብ ብዛት 8 2)ዋሴ ጥላሁን (የቤተሰብ ብዛት 5 3) ተስፋየ ዋለ (6 4) ምን አለ ተሾመ (የቤተሰብ ብዛት 3) 5) ድረስ ታረቀኝ (የቤተሰብ ብዛት 4) 6) አእምሮ ተገኘ (የቤተሰብ ብዛት 5) 7) አዱኛ ታረቀኝ (የቤተሰብ ብዛት 8……) 8ኛ ) ይልቃል መኮንን (የቤተሰብ ብዛት 6) 9) የስጋ ሽበሽ (የቤተሰብ ብዛት 5) 10) አንተነህ ምስሌ (የቤተሰብ ብዛት 4) 11) ቄስ ጎጀም በየነ (የቤተሰብ ብዛት 7 12) ቄስ ውበቱ እብየው (የቤተሰብ ብዛት 3) 13) ታገለ ፈንቴ (የቤተሰብ ብዛት 3) 14) ገሬ አወቀ (የቤተሰብ ብዛት 3) 15) ጌታነህ ሽፈራው (የቤተሰብ ብዛት 3) 16) ተሾመ ደረሰ (የቤተሰብ ብዛት 5) 17) አለማየሁ ዋለ (የቤተሰብ ብዛት 2) 18) ዘላለም ዋሴ (የቤተሰብ ብዛት 2) 19) እንቻለው አበበ (የቤተሰብ ብዛት 6) 20) በቃል እንቻለው (የቤተሰብ ብዛት 2) 21) ቄስ አዲስ አንተነህ (የቤተሰብ ብዛት 5) 22) አስሜ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተፈናቃይ አባወራዎች ጥፋት አማራ መሆናቸው ብቻ ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

የሕወሓቱ ነውረኛ ድርጅት ብአዴን ላለፉት 27 አመታት አማራ ባገሩ ስደተኛ ሆኖ ሲፈናቀልና ሲገደል ለይምሰል እንኳ መግለጫ አውጥቶ አያውቅም። ነውረኞቹ ብአዴዎች ውክልናቸው የትግራይ እንጂ የአማራ ስላልሆነ የአማራ ጉዳይ አይመለከታቸውም። ባለፈው ጥር ወር ላይ ግን በወልድያ፣ በቆቦና በመርሳ የትግራይ ነፍሰ በላ ወታደሮች አማራ ሲጨፈጭፉና አማራ ራሱን የመከላከያ ርምጃ ሲወስድ ሁሉም የብአዴን ድርጅታዊ መዋቅሮች መግለጫ አወጡ። የብአዴን ቃል አቀባዩ Nigussu Tilahun፣ እንደራሴው ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተብዮው፣ የነውረኛው ብአዴን ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮምቴ አባላት በሙሉ የትግራይ ተወላጆች ተጠቁ ብለው የተጨፈጨፈውን አማራ የሚያወግዝ መግለጫ በሬዲዮ፣ በጋዜጣና በቴሌቭዥን አስተላለፉ። አማራ ሲፈናቀልና ሲሰደድ፣ ሲገደልና ሜዳ ላይ ሲጣል ግን ባለፈው ጥር ወር ለገዳይ የትግራይ ወታደሮች አዝነው መግለጫ ያዥጎደጎዱት እነ ንጉሱ ጥላሁን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተብዮው፣ የነውረኛው ብአዴን ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮምቴ ትንፋሻቸው የለም። እንዴውም በተቃራኒው በክህደት ተሰማርተው ከጎጃም መተከል የተፈናቀሉትን አማሮች የመለስ ዜናዊን አገላለጽ በመጠቀም «ሕገ ሰፋሪዎች» በማድረግ እየወነጀሏቸው ነው። ከታች የታተሙት ፎቶዎች «ሕገ ወጦች» ተብለው የተፈናቀሉት አማሮች የተፈናቀሉበት ምድር «የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ» ደብተሮች ናቸው። እነዚህ ደብተሮች አገርና መንግሥት አልባ ሆነው ባህር ዳር አባይ ማዶ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ተባራሪ አርሷደሮች የተባረሩበት መሬት «የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ» ደብተሮች ናቸው። ይህ በግልጽ የሚያሳየው አባወራዎቹ የተባረሩት አማራ ብቻ በመሆናቸው ብቻ እንደሆነ ነው።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከመተከል ተፈናቅለው ለአቤቱታ ባህር ዳር የመጡ ስምንት የአርሶ አደር ተወካዮች ታሰሩ

ከድሮዉ ጎጃም መተከል (የአሁኑ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል) ተፈናቅለዉ ወደ ባህር ዳር ለአቤቱታ መጥተዉ የነበሩ የአማራ አርሶአደሮች 8 ተወካዮች ለአንድ ቀን በባህር ዳር ሁለተኛ ፓሊስ ጣቢያ ታስረዉ መለቀቃቸዉን ገልጸዉልናል፡፡ ይሄንን ህዝብ በትኑ ካልበተናችሁ ግን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት 6 ወር ትታሰራላችሁ ተብለዉ ነበር፡፡ ትላንት ማታ አባይ ማዶ ቴሌ ፊት ለፊት ከሰነበቱበት ግቢ የተባረሩ ሲሆን ወይ ወደ ቤንሻንጉል ክልል ተመለሱ ወይም ደግሞ አማራ ክልል ወደ ዘመዶቻቸሁ ተበተኑ ተብለዋል፡፡ እነርሱም ዘመዶቻችን እንኳን ለኛ ለነርሱም በቂ የርሻ መሬት የላቸዉም ብለዋል፡፡ ትላንት ሌሊት ያደሩበት የአባይ ማዶ ቅዱስ ገብርዔል ቤተ-ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችም ዛሬ ደግመዉ እንዲያድሩ ከፈቀዳችሁላቸዉ ትጠየቃላችሁ ተብለዋል፡፡ የቀበሌ 11 ወጣቶች ዛሬ በገበያና በየሰፈሩ እየዞሩ ለወገኖቻችን ለምግብ የሚሆን ገንዘብ መዋጮ እየሰበሰቡ እንደሆነም ተረድተናል፡፡ የተወሰኑት ተፈናቃዮች በግዳጅ ወደ ፍኖተ ሰላም እንደተጫኑ ታዉቋል፡፡ የምዕ/ጎጃም ዞን መስተዳድርና ወረዳዎችም የናንተ ጉዳይ ከአቅማችን በላይ ነዉ ፤ ክልሉ መፍትሄ ካልሰጣችሁ እኛ ጋር እንዳትመጡ እንዳላቸዉ ገልጸዋል፡፡ የአቤቱታ ደብዳቤ ለጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት አስገብተዉ በስልክ እየተከታተሉ ቢሆንም ጠ/ሚ/ሩ እስከአሁን ቢሮ አልገቡም ተብለዋል፡፡ ፍትህና አስቸኳይ መፍትሄ ለተፈናቃይ ወገኖቻችን! (ደሳለኝ ጫኔ)
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከካማሼ ዞን የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች መፍትሄ አላገኙም (BBC Amharic)

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች አብረው በሚኖሩ ህዝቦች መካከል የሚቀሰቀሱ ግጭቶች እንዲሁም የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሞት እና ውድመትን ከማስከተላቸውም ባለፈ በርካቶችን ለመፈናቀል መዳረጋቸው በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተደጋግሞ የሚስተዋል እውነታ ሆኗል። የተፈናቃዮቹ ቁጥር እጅጉን ከፍተኛ መሆን ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት አዳጋች ያደረገው ይመስላል። ግጭቶች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች ያሉ ቅራኔዎችን የመፍታቱን ያህል መልሶ የማስፈር እና የማቋቋም ኃላፊነቶች ለአገሪቷ ከባድ የራስ ምታት ሆኗል። ባለፈው ጥቅምት ወር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሼ ዞን የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ አላገኘንም ይላሉ። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሼ ዞን በአካባቢው ተወላጆች እና ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ስፍራው በማቅናት ኑሯቸውን በመሰረቱ አርሶ አደሮች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ ሞትና የንብረት ውድመትን ማስከተሉ ባለፈው ጥቅምት ወር መዘገቡ የሚታወስ ነው። ግጭቱ ካፈናቀላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች መካከል ከአምስት መቶ የሚልቁ አባወራዎች በባህር ዳር ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ። ከተፈናቃዮቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አበባው ጌትነት በምዕራብ ጎጃም ዞን ውስጥ የምትገኘውን የትውልድ ቀያቸው ቋሪት ወረዳን ለቀው ወደ ካማሼ ዞን ደዴሳ ቀበሌ ያመሩት በ1992 ዓ.ም እንደነበር ይናገራሉ። ብዙ አዝመራ በማይሰበሰብበት ጥቅምት ወር ላይ ግጭቱ በመነሳቱ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ጥለው እንደወጡ ይናገራሉ። “ግጭቱንም አላወቅነውም። ትንሽ የተወሰነ ረብሻ ነበር የመሰለን። አዝመራ የሚሰበሰብበት ወቅት ስላልነበር 527 አባወራ ምንም ነገር ሳይዝ ትልቅ ኪሳራ ደርሶበት ንብረቱን አጥቶ ለመሰደድ ተገዷል። በባህርዳር አባይ ማዶ የምግብ ዋስትና ግቢ መጋዘን ውስጥ ነው የምንገኘው” ብለዋል። ግጭቶችም ሆነ መፈናቀል
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News