Blog Archives

በቤንሻንጉል መተከል ዞን የ10 አመት ታዳጊ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ።

  በቤንሻንጉል መተከል ዞን የ10 አመት ታዳጊ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ። Tesfaye Woldeselassie በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ኤጀንታ ቀበሌ የ10 አመት ታዳጊዉ ሙሉሰዉ ያብባል አማራ በመሆኑ ብቻ ለመግለጽ በሚዘገንን ሁኔታ ሰዉነቱ ተቆራርጦ ተገድሏል ። ታዳጊዉ ትናንት ቀን ዘጠኝ ሰአት ከብት እየጠበቀ እያለ ነዉ ግድያዉ የተፈጸመበት።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመተከል ዞን ታዳጊው ላይ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡

በመተከል ዞን ታዳጊው ላይ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡ በመተከል ዞን ዲባጢ ወረዳ በአንድ የአማራ ተወላጅ ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደበሌ በልጋፎ ተናገሩ፡፡ የተሰራው ወንጀል ወረዳውን እንዳሳዘነ አቶ ደበሌ ገልፀው እንደዚህ አይነት ችግሮች ዳግም እንዳይፈጠሩ ማህበረሰባዊ ውይይቶችን እያደረግን ነው ብለዋል፡፡የተጠርጣሪዎችን የምርመራ ውጤትም ለህዝብ እንገልፃለን ብለዋል፡፡ የ 14 ዓመቱ ተጎጂ አበጠር ወርቁ አጎት አቶ አያሌው አበረ በበኩላቸው በወንድማቸው ልጅ ላይ የደረሰው አስነዋሪ ድርጊት እንዳሳዘናቸው ገልፀው፣ተጎጂው ለህክምና ከፓዊ ወደ ባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል እንደገባ አረጋግጠውልናል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደበሌም ለከፍተኛ ህክምና ወደ ባህርዳር እንደሚሄድ ቀደም ብለው ያረጋገጡ ሲሆን፣ወረዳው ከተጎጂው ጎን ይቆማልም ብለዋል፡፡ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቱን ለማጥፋትም እንደሚሰራ ተገልጧል፡፡ በዲባጢ ወረዳ የአማራ፣የኦሮሞ፣የጉምዝ፣የሽናሻ ወ.ዘ.ተ ህዝቦች በጋራ እንደሚኖሩ አቶ ደበሌ ተናግረዋል ፡፡ የሺሀሳብ አበራ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሕዴድና የብአዴን ልዩነት ( አቻምየለህ ታምሩ )

1. ኦሕዴድ ለተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች ጊዜያዊ መጠለያ ከመስራት ጀምሮ የተፈናቃዮችን ደህንነት በተቻለ መጠን ለመጠበቅ ሲሞክር፤ ነውረኛው ብአዴን ግን ለተፈናቃዮቹ ጊዜያዊ መጠለያ መስራት ይቅርና ያስጠለላቸው ቤተ ክርስቲያን እንኳ ማረፊያ እንዲነሳቸውና ከግቢው እንዲያስወጣቸው ትዕዛዝ በማስተላለፍ ሕጻናት፣ሴቶችና አረጋውያን ሜዳ ላይ እንዲወድቁ ያደርጋል። 2. ኦሕዴድ ለተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ አትሌቶች፣ ድምጻውያንና ባለሐብቶት የተካተቱበት የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ሲያደርግ፤ ነውረኛው ብአዴን ግን በደብረ ብርሃን ከተማ ተቆርቋሪ የአማራ ልጆች የጀመሩትን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት እንዳይካሄድ ያግዳል። 3. ኦሕዴድ በጅግጅጋ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች እያለ ሲዘግብ ነውረኛው ብአዴን ግን ከጎጃም መተከል የተፈናቀሉ፤ እዚያው ተወልደው የኖሩ አማሮችን «በቤንሻንጉል ጉሙዝ የሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች» ይላል። 4. ኦሕዴድ የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆችን ለማነጋገርና ተስፋ ለመስጠት «የክልሉ አስተዳደር» መደበኛ ስራ አቁሞ ከለማ መገርሳ እስከ ታች ድረስ ያሉ ሹመኞች፤ ከአባ ገዳዎች እስከ ተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች ድረስ ተንቀሳቅሰው መቶ ኪሎሜትሮችን እየተጓዙ ተፈናቃዮች በሚገኙነትን ሁኔታ እንያዩ ሲያደርግ፤ ነውረኛው ብአዴን ግን ከጽሕፈት ቤቱ 500 ሜትር፣ እንደራሴ ከሚገኝበት ቢሮ ደግሞ 1 ኪ.ሜ ርቀር ላይ ብርድና ፀሐይ፣ ዝናብና አቧራ እየተፈራረቀባቸው ሜዳ ላይ ተጥለው የሚገኙ የአማራ እናቶችን፣ ሕጻናትንና አዛውንቶችን ለመጎብኘት አይደለም ሌላ ሰው እንኳን እንዳይጠይቃቸው በማገድ ቀድመው ባህር ዳር የደረሱ ተፈናቃዮችን በእቃ ማጓጓዣ ጭነው የት እንዳደረሷቸው እስካሁን አይታወቅም፤ ያልተረጋገጡ መረጃዎች እስር ቤት እንዳጋዟቸው ያሳያሉ። 5. ኦሕዴድን የኦሮሞ ተወላጆችን መፈናቀል ከተፈናቃዮች በስልክ እንደደረሰው በብርሃን ፍጥነት ሙሉ ኃይሉን አንቀሳቅሶ ለተፈናቃዮች ሲደርስና ተስፋ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከመተከል ተፈናቅለው ለአቤቱታ ባህር ዳር የመጡ ስምንት የአርሶ አደር ተወካዮች ታሰሩ

ከድሮዉ ጎጃም መተከል (የአሁኑ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል) ተፈናቅለዉ ወደ ባህር ዳር ለአቤቱታ መጥተዉ የነበሩ የአማራ አርሶአደሮች 8 ተወካዮች ለአንድ ቀን በባህር ዳር ሁለተኛ ፓሊስ ጣቢያ ታስረዉ መለቀቃቸዉን ገልጸዉልናል፡፡ ይሄንን ህዝብ በትኑ ካልበተናችሁ ግን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት 6 ወር ትታሰራላችሁ ተብለዉ ነበር፡፡ ትላንት ማታ አባይ ማዶ ቴሌ ፊት ለፊት ከሰነበቱበት ግቢ የተባረሩ ሲሆን ወይ ወደ ቤንሻንጉል ክልል ተመለሱ ወይም ደግሞ አማራ ክልል ወደ ዘመዶቻቸሁ ተበተኑ ተብለዋል፡፡ እነርሱም ዘመዶቻችን እንኳን ለኛ ለነርሱም በቂ የርሻ መሬት የላቸዉም ብለዋል፡፡ ትላንት ሌሊት ያደሩበት የአባይ ማዶ ቅዱስ ገብርዔል ቤተ-ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችም ዛሬ ደግመዉ እንዲያድሩ ከፈቀዳችሁላቸዉ ትጠየቃላችሁ ተብለዋል፡፡ የቀበሌ 11 ወጣቶች ዛሬ በገበያና በየሰፈሩ እየዞሩ ለወገኖቻችን ለምግብ የሚሆን ገንዘብ መዋጮ እየሰበሰቡ እንደሆነም ተረድተናል፡፡ የተወሰኑት ተፈናቃዮች በግዳጅ ወደ ፍኖተ ሰላም እንደተጫኑ ታዉቋል፡፡ የምዕ/ጎጃም ዞን መስተዳድርና ወረዳዎችም የናንተ ጉዳይ ከአቅማችን በላይ ነዉ ፤ ክልሉ መፍትሄ ካልሰጣችሁ እኛ ጋር እንዳትመጡ እንዳላቸዉ ገልጸዋል፡፡ የአቤቱታ ደብዳቤ ለጠ/ሚ/ር ጽ/ቤት አስገብተዉ በስልክ እየተከታተሉ ቢሆንም ጠ/ሚ/ሩ እስከአሁን ቢሮ አልገቡም ተብለዋል፡፡ ፍትህና አስቸኳይ መፍትሄ ለተፈናቃይ ወገኖቻችን! (ደሳለኝ ጫኔ)
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News