Blog Archives

በአማራ ወልቃይት ህዝቦች ላይ ዘር መሰረት ያደረገ ጥቃት እንደተደረገባቸው ከወልቃይት የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ተናገሩ፡፡

Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአማራና አፋር ድንበር ግጭት የሚናፍቁ ሴረኞች እና የመሬት ወረራ ኮንትሮባንዲስቶች መስጂድ አቃጠሉ።

የድንበር ግጭት ይቁም! ሆን ተብሎ በአፋርና በአማራ ህዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር የተደረገ ሴረኞች እና የመሬት ወረራ ኮንትሮባንዲስቶች የፈፀሙት ሴራ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህ የምትመለከቱት የእሳት ቃጠሎ በደን ላይ የተፈፀመ ቃጠሎ አይደለም፡፡ የአላህ ቤቶች ናቸው የተቃጠሉት፡፡ እንዲሁም የህዝብ መኖሪያዎች ናቸው የተቃጠሉት፡፡ ቦታ አፋር ክልል ኡዎ ወረዳ ውስጥ ነው፡፡ ዛሬ ከአሱር ሰላት ቡሗላ የአማራ ሶዶማ ድንበርተኞች መስለው የገቡ ሴረኞች እና ኮንትሮባንዲስቶች የፈፀሙት ጥቃት ነው፡፡ ጦርነቱ እሰከ ምሽት ድረስ በድንበር ላይ መቀጠሉን የአይን ምስክሮች ያስረዳሉ፡፡ በዚህ አካበቢ ተደጋጋሚ የሆነ ያልተለመደ ግጭቶች እየተፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ የመሬት ወረራ ኮንትሮባንድስቶች እየፈፀሙ የሚገኘው ሴራ በመሆኑ የፌዴራል መንግስት ግጭት ሰፍቶ አስካፊ እልቅት በሁለቱ ብሔሮች መካከል ከመፍጠሩ በፊት አፋጣኝ መፍትሄ በክልሎች ጉዳይ ላይ መስጠት አለበት፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በወልቃይት የትግራይ ፖሊስና ሚሊሻ በነዋሪዎች ላይ የሚያደርሰው ግፍ ቀጥሏል።

ከስር የሚታየው ፎቶ ወጣቶች ከአራት ቀናት በፊት በወልቃይት ወደ አድረመጥ ፖሊስ ጣቢያ የኋሊት ታስረው ሲወሰዱ የሚያሳይ ነው! ወልቃይት ውስጥ ሲፈፀሙ የኖሩ የተወሰኑ ዘግናኝ ድርጊቶችን ከስር በሚታየው ፎቶ አስደግፌ ለመግለፅ እሞክራለሁ! እስከዛሬ ሲፈፀሙ የኖሩትን በደሎች የዛሬው ፎቶም በትንሹ ይገልፃቸዋልና! አፓርታይድ በወልቃይት! አታላይ ዘነበ፣ ባየው ቢያድግልኝ፣ አሻግር ዘውዴ፣ ማሙ ዘውዴ፣ ይርሳው ዘውዴ፣ ተበጀ በቀለ፣ ጎይቶም ሀድጎ፣ አያሌው ሰሙ፣ ገብረ መድህን ዘረፋ፣ ነጋ ተገኘ የማንነት ጥያቄ ያነሱ የነበሩ ናቸው። ከእነዚህ መካከል አብዘኛዎቹ የትህነግ/ህወሓት ሰዎች ሌሊት ቤታቸውን አፍነው አስረው ያጠፏቸው ናቸው። አስከሬናቸው የት እንዳለ አልታወቀም። አንድ የወልቃይት ኮሚቴ አባል ስለነዚህ ሰዎች አሟሟት እንዲህ አጫውቶኛል። “ጉድጓደረ ቆፍረው አሰረገቧቸው። አፉን ማገዶ ማገዱት። እሳት አቃጥለው። ጫምዳ የሚባል እንጨት ቅጠሉን ቆርጠው አፈኑት። ከቅጠሉ በላይ አፈር። በጢስ ነው የሞቱት። ይህ የተደረገው ሀለዋ ወያኔ የሚባል እስር ቤት አውጥተው ነው” ወልቃይት ላይ ይህን የመሰለ ጭካኔ ይፈፀማል! ( ይህን ፎቶ ወልቃይት ላይ የሰፈነው የአፓርታይድ አገዛዝ ዛሬም መቀጠሉን የሚያሳይ ነው። ፎቶው ዛሬም ወጣቶች በዚህ መልኩ ታስረው ወደ እስር ቤት እንደወሰዱ የሚያሳይ ነው) አበበ ይርጋ፣ አለበል ይርጋ፣ ገረማርያም አረፈ አይኔ፣ አንጋው እሱባለው፣ ጫኔ ይርጋ፣ በሪሁን ይርጋ፣ አላቸው አለማየሁ፣ መኮንን ለውጤ በማንነት ጠያቂነታቸው የተገደሉ ናቸው። አብዛኛዎቹ ተመሳሳይ ሰቆቃና ግፍ ተፈፅሞባቸዋል። በውጊያ ተገድለው አስከሬናቸው በመከከና የማይጎተቱት ጥቂቶች ናቸው። ተሰማ አውለው፣ ብርሃን በላይ፣ ሀየሎም ወንድማገኝ፣ አለም መብራት፣ ይልማ ገብረስላሴ፣ ደሞዝ ምትኬ ውጊያ፣ ፈጠነ ዘነበ ውጊያ ላይ የተገደሉ
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ ክልል የአማራ ተወላጆችን በደብዳቤ እያፈናቀሉ እንደሆነ ብአዴን ይፋ አድርጓል።

በትግራይ ክልል በመቀሌና በሌሎች ልዩ ልዩ የክልሉ ከተሞች አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ 1ኛ. ከጃናሞራ ወረዳ ደሮና ቀበሌ ወ/ሮ አልማዝ ዘረፋዉ ከእህቷ አዝመራ አስማማዉና ከ3 ዓመት ህጻኗ ጋር፣ 2ኛ. ከዳባት ወረዳ ጃንበለዉ ቀበሌ ወ/ሮ ፍቅርአዲስ ማሬ ከ1 ወንድ የ4 ዓመት ልጇ ጋር 3ኛ. ከደንቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ቀበሌ 01 ወ/ሮ አለም ታረቀኝ ከ1 ወንድ የ16 ዓመት፣ከ2 ሴት የ10 ዓመትና የ2ዓመት ልጅቿ ጋር ተፈናቅለዉ እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን እቃቸዉን ይዘዉ እንዲወጡም ህጋዊ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን ያጓጓዘዉ ሾፌርም ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰበት ገልጾልናል፡፡ ዘጋቢ፡-ፈንታ ተረፈ Source https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1803888919708175&id=1614679661962436
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አማራን ትጥቅ የማስፈታት አዲሱ ስትራቴጂ! (ሙሉቀን ተስፋው )

አማራን ትጥቅ የማስፈታት አዲሱ ስትራቴጂ! (ሙሉቀን ተስፋው ) ባለፉት ዓመታት የወያኔ አገዛዝ የአማራ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት ብዙ ጥሮ አልተሳካለትም ነበር፤ አሁን ያለው አደገኛ አካሔድ በጊዜ ካልተገታ ውጤቱ የከፋ ነው፡፡ ገበሬዎችን በገንዘብ በመደለል ትጥቃችሁን ፍቱ ማለት እጅግ ነውረኛ አካሔድ ነው፤ ሕወሓቶች መሣሪያ ከማስታጠቅም አልፈው ሁሉንም ትግሬ ወታደር ለማድረግ በሚነቀሳቀሱበት በዚህ ወቅት የአማራን ገበሬ በገንዘብ በመደለል ትጥቅ ለማስፈታት መሮጥ እጅግ እጅግ የከፋ መርዘኛ አካሔድ ነው፡፡ በበኩሌ ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት የአማራ ገበሬዎችን በየቦታው እየመዘገበ የእኔ ጦር የነበሩ ናቸው በማለት ሲያቀርብ አልተቃወምኩም ነበር፤ ምክንያቱ ደግሞ መንግሥት ለኦነግ ወታደሮች መቋቋሚያና ቤት ወዘተረፈ ለማቅረብ ስለተስማማ በዚህም የእኛ ገበሬዎች ተጠቃሚ ቢሆኑ ጉዳት የለውም ከሚል ነው፤ ይህም ብቻ ሳይሆን የአማራ ገበሬዎች አገዛዙ ተንኮታኩቶ እንዲወድቅ የእነርሱንና የልጆቻቸውን ሕይወት ስለገበሩ መቋቋሚያ ማግኘት የግድ በመሆኑ በየትኛውም በኩል ይህን እገዛ ማግኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን አሁን አካሔዱ መስመር እየለቀቀ ነው፡፡ በዚህ ቀውጢ ጊዜ ነገሮችን ከመቼም ጊዜ በላይ አስተማማኝ ሳይሆኑ የእኛን ገበሬዎች መቋቋሚያ ታገኛላችሁ በሚል መሣሪያና ትጥቅ ማስፈታት እጅግ አደገኛና ሁላችንም ልንቃወመው የሚገባ ነው፡፡ የግንቦት ሰባት አመራሮች ያሠማራችኃቸውን ወኪሎቻችሁን ይህን አደገኛ አካሔድ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ብታደረጉ መልካም ይመስለኛል፡፡ የአማራ ገበሬወችን ትጥቅ የማስፈታት ሒደት በእጅጉ እቃወማለሁ፡፡ ምስሉ የምዕራብ ጎጃም ገበሬዎች በግንቦት ሰባት የትጥቅ ማስፈታት ፕሮግራም ውስጥ እንዳሉ ነው የሚያሳየው፡፡
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአማራና በአፋር አወሳኝ የተነሰው ግጭት ይቁም! (በአሎ ያዮ)

በአማራና በአፋር አወሳኝ የተነሰው ግጭት ይቁም! (በአሎ ያዮ 4/12/2010) ከአዳም በፊት ሠው የተባለ ፉጡር አልነበረም፡፡ አምላካችን(ሱ.ወ)በተከበሩ እጆች የሠው ልጅ አባት የሆነውን አዳም(ዐ.ሠ) ፈጠረ፡፡ ዘሮቹ እንዲራቡ ዘንድ የሱ ፍላጎት ሆነ፡፡ እናታችን ሃዋን(ህዋንን) ከጎኑ ፈጠረ፡፡ ከዛም ሐዋ መንታ መንታ በመውለድ ከመሃላቸው በርካታ ሴቶችና ወንዶች ልጆች ተወለዱ፡፡ የሠው ልጅ ግጭት ከህዋን መንታ ልጆች ይጀምራል፡፡ወንድማማቾቹ ሀቤልና ቃቤል በጭካኔ ተገዳደሉ፡፡ ከዛ ግዜ ጀምሮ ለሚሞቱ የአዳም ዘሮች ነፍስ ላይ 50% ቃቤል ነፍስ ተጠያቂ ነው፡፡ የግድያ አስካፊ ሞት ከዚህ ይጀምራል፡፡ ከዚያ ቡሗላ የተከበረ የሠው ልጅ ህይወት አንድም ቀን አርፎ አያውቅም፡፡ገምሲ በስልጣን፡ ሌላው በገንዘብ፡ ሌላኛው ደግሞ በሌላ ሰበብ በጭካነ ይገደደላል፡፡ በሠው ልጅ አይረሴ የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ተደርጓል፡፡ ሁሉም ግድያዎች በስተጀርባ የተደበቀ ሴራና ፍላጎቶች ከጀርባው አሉ፡፡ ወደ አማራና አፋር ጉዳይ ስንመለስ ሁለቱ ብሔሮች ለዘመናት የቆዩ ወዳጅነት በመካከላቸው አሏቸው፡፡ ከወዳጅነት አልፈው በደም በዝምድና ተሳስረዋል፡፡ ከአስራ አምስት በላይ የሆኑ የአፋር ክልል ወረዳዎች ከሌሎች በላቀ መልኩ በድንበር በጎርብተና ከአማራ ጋር ይገናኛል፡፡ በአፋር ክልል ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች የህዝብ ቆጠራ ስሌት ከፍተኛ ቁጥር የያዘው #የአማራ ህዝብ ነው፡፡ በክልሉ በሚገኙ የኢኮኖሚ እሴቶች ውስጥ በአይነት የአማራ ተወላጆች በሥራ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በመንግሥት ሴክተር ላይ እንደ ወሎ ተወላጆች በቢሮዎች በርካታ ቁጥር የያዙ የሉም፡፡ ይህን ሁሉ ዘመን አንድም ቀን ዘር መአከል ያደረገ ግጭት በክልሉ በአፋርና በሌሎች ማህበረሰብ መካከል ተፈጥሮ አይታወቅም፡፡ በዚሁም አፋር ለሌላው አርአያ መሆን ይችላል በሠላም ረገድ፡፡ አሁን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አማራን የሚያገልና የሚጨቁን የፌዴራሊዝም አተገባበር ነው የነበረው!!

በኩር፤ ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓም አማራን የሚያገልና የሚጨቁን የፌዴራሊዝም አተገባበር ነው የነበረው!!   ዶክተር ሲሳይ መንግሥቴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግና አስተዳደር መምህር ናቸው:: በሰብዓዊ መብት ዙሪያም የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አላቸው:: ዶክተር ሲሳይ በአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ በምክትል ሀላፊነት ያገለገሉ ሲሆን በቀድሞ ስሙ የኢህዴን (ብአዴን) ታጋይም ነበሩ:: ዶክተሩ የዚህ እትም እንግዳችን ናቸው:: መልካም ንባብ! ስምዎ በተለየ ሁኔታ ከራያ ህዝብ ጋር ብዙ ጊዜ ይነሳል:: ምክንያቱ ምንድን ነው? ተወልጀ ያደግሁ ራያ ውስጥ ነው:: በራያ ስማር በነበረው የፖለቲካ ትኩሳት ወደ ኢህዴን ገብቸም ታግያለሁ:: ኢህዴን /ብአዴን/ በነበርኩበት ጊዜ የራያን ህዝብ መብትና ጥቅም እንዲጠበቅ እታገል ነበር:: የራያ ህዝብ ፍላጐት ሳይጠየቅ በሁለት ክልሎች እንዲተዳደር ተደርጓል:: በ2005 ዓ.ም የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ እና የማዕከላዊ መንግሥታት ምላሽ ከአፄ ዮሐንስ እስከ ኢህአዴግ የሚል መጽሀፍ ከጓደኛዬ ጋር ሆነን አዘጋጅተናል:: የራያን ህዝብ ታሪክ እና ተጋድሎም እያሳወቅሁ ነው:: የራያን ህዝብ ተጋድሎ ትግራዮች ደግሞ ቀዳማዊ ህዝብ ወያኔ ትግል የሚሉትን ታሪክ በተመለከተ በማስረጃ ሞግተናል:: ቀዳማዊ ህዝብ ወያኔ የራያ ህዝብ ታሪክ ነው:: በዚህ ጉዳይ ጽፌያለሁ፤ሞግቻለሁ:: ለዚህ ይመስለኛል ስሜ ከራያ ህዝብ ጋር ጐልቶ የሚነሳው:: የራያ ህዝብ ስነ ልቦናዊና ባህላዊ ቅርበቱ ከየትኛው ማህበረሰብ ጋር ነው? የራያን ህዝብ ሠዎች በተለያየ መንገድ ይገልፁታል:: የራያ ህዝብ ስንል በድሮው የራያ ቆቦና አዘቦ አውራጃ የሚኖር ህዝብ ድምር ነው:: የራያነት ስነ ልቦና አለው:: ራያ የነ ጥላሁን ግዛው ሀገር ነው:: አማርኛ ይነገራል:: ትግረኛ የሚመስል
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ብአዴን ለራሱ ሲል መውሰድ ያለበት አንድ አማራጭ (ጌታቸው ሺፈራው)

ብአዴን ለራሱ ሲል መውሰድ ያለበት አንድ አማራጭ (ጌታቸው ሺፈራው) ~በቅርቡ ብዙ እስረኞች ተፈትተዋል። ከ80 በላይ ክሳቸው ተቋርጧል ተብለው ፍች እየተጠባበቁ ነው። አብዛኛዎቹ ተፈችዎች ታጣቂ የነበሩ ናቸው። በተለያየ አጋጣሚ መሳርያ አንስተው የነበሩ ናቸው። ~ብአዴን እነዚህን ወጣቶች ደፍሮ የሰራዊቱ አካል ያደርጋቸዋል ተብሎ አይታሰብም። አይደለም እነዚህን ሲወጉት የነበሩ ወጣቶች እነ ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ በማንነታቸው ከሰራዊቱ የተባረሩትን ከ42 ሺህ በላይ የሰራዊት አባላትን መጠቀም አልቻለም። ~ዛሬ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ (አዴኃን) ልዑካን ዛሬ ባህርዳር ገብተዋል። የአዴኃን ሰራዊት አባላት ኤርትራ ይገኛሉ። የትግራዩ ደሚት እያፈነ የወሰዳቸው ( የደሚት ሰራዊት አባላት ታፍነው በግድ የሰለጠኑ የአማራና ኦሮሞ ልጆች ናቸው) የአማራ ወጣቶች ወደ ሀገር ቤት ይገባሉ። የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት የነበሩትም እንዲሁ። ~ከአንድ ወር ውስጥ ብዙ ከትጥቅ ትግል የተመለሱ ወጣቶች ይኖራሉ። ከእነዚህ ወጣቶች መካከል አብዛኛዎቹ ቤተሰብ የላቸውም፣ ቤተሰብ ቢኖራቸው ህይወታቸው ይናጋል። ስራ አይኖራቸውም። ወታደሮች ናቸውና የራሳቸው ህይወት መምራት አያቅታቸውም። አማራጭ ግን ይወስዳሉ። አማራጫቸው ግን መልካም ላይሆን ይችላል። ~የወታደሮቹ አማራጭ መልካም የሚሆነው መንግስት ሁኔታዎችን ሲመቻቹ ነው። ባለፉት ወራት ከሱዳን ሰራዊት ጋር ሲዋጉ የነበሩት የአማራ ገበሬዎች እነ መለስ ለሱዳን የተሰጡትን መሬት ማስከበር ችለዋል። የአማራ ገበሬዎች የራሳቸውን መሬት ማረስ ባይችሉም ለሱዳን የተሰጠውን መሬት ማስከበር ችለዋል ተብሏል። ~የአማራ ገበሬዎች እነ መለስ ዜናዊ ፈርመው ለሱዳን የሰጡትን መሬት ቢያስመልሱም አንድ ችግር ተፈጥሯል። ጉዳዩ ሲረጋጋ መሬቱን በመከፋፈል ችግር ይፈጠራል ተብሎ እየተሰጋ ነው። ከሱዳን ለጊዜውም ቢሆን የተመለሰው
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ብአዴን የገበሬውን መሳርያ ለማስፈታት ዘመቻ እያደረገ ነው ።

የገበሬውን መሳርያ ለማስፈታት ብአዴን የጀመረው ዘመቻ ብአዴን እነ አረጋ አለባቸው ላይ ዘመቻውን ቀጥሏል። በድርጅት ደረጃ መሳርያ ያነሱት ወደ ሀገር ግቡ ሲባሉ ብአዴን በግለሰብ ደረጃ መሳርያ ያነሱትን አርበኞች እያሳደደ ነው። ትጥቅ ፍቱ ተብለው ያልፈቱ ድርጅቶች ላይ እንኳ ጥሩ መለሳለስ ታይቷል። ብአዴን ግን ግለሰቦችን እያሳደደ ነው። በቅርቡ እነ አረጋ ምንም ስላደረጉ አይደለም። ሕዝብን መሳርያ ለማስጣል መጀመርያ እነዚህን አርበኞች ማጥፋት ስለታሰበ ነው። በቀጣይ ደግሞ እነ መሳፍንት ላይ ያዘምታል። አርበኞችን ሲያጠፋ ደግሞ ወደ ሕዝብ ይዘምታል። በአማራ ክልል በተደረጉ ሰልፎች ሰልፈኛው የእነዚህን አርበኞች ፎቶ ይዞ ነው የወጣው። ብአዴን ከሕዝብ ጎን እሆናለሁ እያለ ግን ሕዝብ “አሸባሪ አይደሉም፣ አርበኞች ናቸው” ያላቸው ላይ ጦር እያዘመተ ነው። ከሕዝብ ጎን እቆማለሁ እያለ ሕዝቡ “የእኔ ናቸው” ያላቸውን እየወጋ ነው!
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ሕዝብ ማንን ይመርጣል? (ጌታቸው ሺፈራው)

የአማራ ሕዝብ ማንን ይመርጣል? (ጌታቸው ሺፈራው) ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ፣ ባለፉት 10 አመታት ወደመዘጋት ደርሶ የነበረው የፖለቲካ ምህዳር መስፋት ጀምሯል። ይህን መልካም አጋጣሚ ድርጅቶች ወደሕዝብ ለመግባት እየተጠቀሙበት ነው። አማራው ሕዝብ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ለማየት ብንሞክር እንኳ ብአዴን፣ አብንና አርበኞች ግንቦት ሰባት ከሌሎች በተሻለ ራሳቸውን ለማጠናከር ተፍ ተፍ እያሉ ይገኛሉ። 1) ብአዴን:_ ባለፉት 27 አመታት ሕዝብን ሲያስገዛ የኖረው ብአዴን የዶክተር አብይ አይመድን “መደመር”ና መሰል ፍልስፍናዎች ጠገግ አድርጎ፣ እነ ዶክተር አብይ አህመድ በሕዝብ ያገኙትን ተቀባይነት መሰረት በማድረግ በሕዝብ ልብ ለመግባት ተፍ ተፍ እያለ ነው። እነ ገዱ አንዳርጋቸው ባህርዳር በተደረገው ሰልፍ ላይ “ከአሁን በኋላ አማራ አንገቱን አይደፋም” ብለዋል። እነ ተቀባ ተባባል ሀምሌ 5 የአማራ ሕዝብ የነፃነት ቀን ነው ሲሉ ተደምጠዋል። የአማራ ተጋድሎን እውቅና መስጠት ጀምረዋል። ይህን የሚሉት የዶክተር አብይ አዲስ አስተሳሰብ ነው የሚሉትን ጠገግ በመያዝ ሲሆን ከሕዝብ የሚጠጉበት ብቸኛው አማራጭም “አዲሱ አስተሳሰብ” ነው እያሉ ነው። በዚህ ሂደት ትህነግ/ህወሓትና የቀድሞ የብአዴን አመራሮች ጋር ልዩነት እንዳላቸው በማስመሰል ለሕዝብ ራሳቸውን እንደአዲስ ማስተዋወቅ እየጣሩ ነው። የሕዝብ በደልና መከፋትን እውቅና እንደሚሰጡ ለማስመሰል እየጣሩ ነው። ብአዴን የአማራ ሕዝብ ላይ ተቀባይነት ባይኖረው እንኳ አደረጃጀቱን ይዟል። የዶክተር አብይን ተቀባይነት በኢህአዴግ ስር ሆኖ እየተጠቀመባት ይገኛል። ይሁንና ለ27 አመት የለመደበት የአስገዥነት፣ የአድርባይነትና የተላላኪነት አባዜ አልለቀቀውም። ከዚህም ባሻገር የአማራ ሕዝብ በኢኮኖሚው እንዲገለል፣ በሌሎች እንዲጠላ፣ ብዙ በደሎች እንዲደርሱበት የሰራ በመሆኑ በሕዝብ ዘንድ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቤንሻንጉል መተከል ዞን የ10 አመት ታዳጊ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ።

  በቤንሻንጉል መተከል ዞን የ10 አመት ታዳጊ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለ። Tesfaye Woldeselassie በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ኤጀንታ ቀበሌ የ10 አመት ታዳጊዉ ሙሉሰዉ ያብባል አማራ በመሆኑ ብቻ ለመግለጽ በሚዘገንን ሁኔታ ሰዉነቱ ተቆራርጦ ተገድሏል ። ታዳጊዉ ትናንት ቀን ዘጠኝ ሰአት ከብት እየጠበቀ እያለ ነዉ ግድያዉ የተፈጸመበት።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አማራ-ጠል ደዌ የህወሃት ብቻ ህመም አይደለም ( መሥከረም አበራ )ቸ

አማራ-ጠል ደዌ የህወሃት ብቻ ህመም አይደለም ዛሬ እግሯ ገደል የገባው ህወሃት ከተፈጠረች ጀምሮ በተቆራኛት አማራ-ጠል ደዌ ስትሰቃይ የኖረች ንኡስ ፍጡር ነች፡፡ይህ በሽታ ግን ህወሃትን ብቻ የሚያሰቃይ አይደለም፡፡ይልቅስ ፈውስ በሌለው የዘረኝነት ልክፍት የተለከፉ ፖለቲከኞችን ሁሉ የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ የሞት አፋፍ ላይ ያለችውን ህወሃት ከሞት ሊመመልሳት ባይችል እንኳን በጣር የመፈራገጧ ጊዜ እንዲረዝም የሚያስችሏትም የእነዚሁ የበሽታ ተጋሪቿ እርዳታ ይመስለኛል፡፡ የአማራ ጥላቻ በብዙ መንገድ ይገለፃል፡፡ ለምሳሌ የህወሃት ባስልጣናት እና የአረና አክቲቪስቶች የወንዛቸው ልጆች መሳሪያ ተደግፈው ከተቀመጡበት ወንበር በአፍጢማቸው የደፋቸው የኦቦ ለማ እና የጠ/ሚ/ር አብይ ኦህዴድ ሆኖ ሳለ አምርረው እየወቀሱ ያሉት በስንት ግፊያ መላወስ የጀመረውን አማራውን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን እና “አለ ሞቷል?” እያልን ስንወራረድበት የኖርነውን ፓርቲያቸውን ብአዴንን ነው፡፡ የኢንሳው ሰውየ እንደውም “የኦህዴድ እና የኦሮሞዎች ችግር ስስ ነው የብአዴን እና የአማሮች ችግር ነው የደደረው” ብለው መቃብር ብቻ የሚለየውን አማራን ሁልጊዜ የመጥላት በሽታቸውን አስመሰከሩ፡፡ ይህ በሽታ የህወሃቶች እና ትግሬ አክቲቪስቶች ብቻ ስላልሆነ ባለፈው ሳምንት ዶ/ር አወል ቃሲም (ምክንያታዊ ይመስለኝ ነበር) በሃገሩ ላይ ከተደረገው ሰልፍ ሁሉ የባህርዳሩ ሰልፍ ላይ ተይዞ የተወጣው ባንዲራ የአሮጌውን አብሮነት ምልክት አየሁበት ብሎ ተብሰለሰለ፡፡ አዛውንቱ ዶ/ር ነጋሶ ደግሞ ዛሬ የሆነ መፅሄት ላይ ቀርበው ባደረጉት ቃለ ምልልስ የባህር ዳሩ ሰልፍ የለየለት የህገ-መንግስት ጥሰት ነው ሲሉ “ስለፃፍኩት ተፀፀትኩ” ላሉት ህገ-መንግስት ጠበቃ ሆነው ብቅ አሉ፡፡ በዚህ ቃለ ምልልስ ከዶ/ር ነጋሶ ጋር የተገናኘው ሰውየ ጋዜጠኛ መሆኑን እጠራጠራለሁ! ዶ/ር
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“አሁን ያለው የፌደራሊዝም ሥርዓት የአማራውን ህዝባዊ አንድነት የሚገረስስ ሆኖ ነው ያገኘነው” – የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ

ላለፉት ቀናት የመስራች ጉባዔውን በባህር ዳር ከተማ ሲያከናውን የቆየው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ፤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን በመምረጥ ተጠናቅቋል። በዚህም መሠረት በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔን የፓርቲ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል። የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ክርስቲያን ታደለን በፓርቲው ምስረታ፥ ቀጣይ እርምጃዎች እንዲሁም በተነሱ ትችቶች ዙሪያ ቢቢሲ አነጋግሯቸዋል። ቢቢሲ- በቅርቡ መስራች ጉባኤያችሁን አካሂዳችኋል፤ ምን ይመስል ነበር? አቶ ክርስቲያን ታደለ- ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ የስራ አስፈጻሚው ቁጭ ብሎ ተወያይቶ ነበር። ምስረታው ከጠበቅነው በላይ እጅግ ስኬታማ ነበር። ምስረታውም ትክክለኛ እንደነበረ አረጋግጦልናል። ይህ ጉዳይ የተወሰኑ አባላት ብቻ ጉዳይ አይደለም፤ በትንሹ ከ40 እስከ 45 ሚሊየን የሚገመተው የሁሉም አማራ ተወላጅ ጉዳይ ነው ብለን ነው የምናምነው። በሃገራችን ህግ መሰረት አንድ ሃገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ሲመሰረት ቢያንስ 1500 አባላት ከአምስት ክልሎች ማስመዝገብ ስለሚጠበቅበት፤ እነሱን ነው ለምርጫ ቦርድ በመስራች አባልነት ያስመዘገብነው። ቢቢሲ- የአጭር፤መካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅዶቻችሁ ምንድናቸው? አቶ ክርስቲያን ታደለ- እንግዲህ ሁሉም ሰው እንደሚከታተለው፤ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ በየጊዜው ተለዋዋጭ እና እጅግ ፈጣን፤ ጊዜ የማይሰጥና ሌት ከቀን መስራት የሚጠይቅ ነው ብለን እናምናለን። የአጭር ጊዜ ግባችን ድርጅቱን ለህዝቡ ማስተዋወቅ ነው። አደረጃጀቱን በከተማ፤ በገጠር እንዲሁም ምሁራን አካባቢ ማጠናከር እናስባለን። በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጪም ያለውን የአማራ ተወላጅ እናደራጃለን። ከዚያም ቀጥሎ ሊመጣ የሚችለው፤ እንደ ሃገር በአሁኑ ሰአት በጣም ፈጣን የሚባሉ ውሳኔዎች እየተወሰኑ ስለሆነ፤ አማራውን በቁመቱ እና በወርዱ ሊወክለው የሚችል የፖለቲካ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ( National Movement of Amhara – NAMA) መስራች ጉባዬ በባሕር ዳር ተጀመረ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መስራች ( National Movement of Amhara – NAMA) ጉባዬ በባሕር ዳር ተጀመረ። የአማራ ህዝብ መብትና ጥቅም መከበርን አላማው አድርጎ የሚታገል የአማራ ፓርቲ የምስረታ ጉባኤ በዛሬው እለት በይፋ ተጀመረ። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መስራች ጉባዬ በባሕር ዳር የተጀመረ ሲሆን ፓርቲው ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጂት ሆኖ ለመንቀሳቀስ የሚያስችለውን የፊርማ ማሰባሰብ እና ተያያዥ መስፈርቶችን አሟልቶ ጉባኤውን እንደጀመረ ታውቋል። ፓርቲው ከምስረታ በኋላ ማዕከሉን ሸዋ፣ አዲስ አበባ በማድረግ በመላ ሀገሪቱ ስራውን ይሰራል ተብሏል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ በፕር አስራት ወልደየስ ይመራ ከነበረው መአህድ ወዲህ ሀገር ውስጥ የሚመሰረት ብቸኛው የአማራ ፓርቲ መሆኑ ነው።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

13 ጄኔራሎችን ጨምሮ 41 ሺህ የአማራ ተወላጆች ከመከላከያ ሰራዊቱ በግፍ ተባረዋል።

ፀረ አማራው መከላከያ ሰራዊት በማንነታቸው ከሰራዊቱ የተባረሩ አማራ #ጀኔራሎች በአስር አመት ውስጥ ከ13 በላይ ጀኔራሎች፣ ከ45 በላይ ኮረኔሎች፣ ከ250 በላይ ሻለቆች ከ21 ሺህ በላይ ከመስመራዊ መኮንን እስከ ተራ ወታደር ብሔራቸው አማራ ስለሆኑ ተባርረዋል። ከዛ በፊት 20 ሺህ ወታደሮች ተባርረዋል። በአጠቃላይ ከ41 ሺህ በላይ የአማራ ተወላጆች ከሰራዊቱ ተባረዋል። 1) ብ/ ጀኔራል ተፈራ ማሞ በተለያዩ የውጊያ ቦታዎች ላይ ሰራዊቱን መርቶ ተዋግቷል፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመሪነት ቦታ የሚያየው ሰው ነው። ጀኔራል ተፈራ የህወሃት የበላይነትን ከበረሃ ጀምሮ በመታገሉ “ነፍጠኛ፣ ትምክተኛ፣ ፊውዳል” እየተባሉ ፍረጃ ሲሰጣቸው ከነበሩት መካከል ቀዳሚው ነው። ከ1998 ጀምሮ አማሮች ከሰራዊቱ በማንነታቸው ሰበብ እየተፈለገ “በዲሲፕሊን” እየተባሉ ሲባረሩ ጀኔራል ተፈራ “በዲስፕሊን አይደለም” ብሎ ተከራክሯል። ከሰራዊቱ ለተባረሩት ድጋፍ ደብዳቤ በመፃፉ፣ በግምገማ ወቅት ስለህወሓት ጀኔራሎች ሙስና በመናገሩ ጥርስ ውስጥ ገብቷል። የአማራ ተወላጅ የሆኑ የሰራዊት አባላት “ጀኔራል ተፈራ፣ ከጀኔራል ኃይሌ ጥላሁን ጋር ሆኖ መለስ ዜናዊን ለማስገደል እያሴረ ነው” ብለው በሀሰት እንዲመሰክሩበት ተገድደው በሀሰት አንመሰክርም በማለታቸው ከእስር ተርፎ ነበር። በመጨረሻም በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ክስ እድሜ ልክ ተፈርዶበት 9 አመት ታስሮ በቅርቡ ተፈትቷል። ብ/ጀ ተፈራ ማሞ ከሙስና የፀዳ በመሆኑ በሰራዊት ዘንድ “ድሃው ጀኔራል” በመባል ይታወቃል። 2) ብ/ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ~”ትምህርት ቤቱ ይፈርሳል እንጂ አማራ አይማርበትም” ጀኔራል ሳሞራ የኑስ አሳምነው የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ ነበር። ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ የጀኔራልነት ማዕረግ አግኝቷል። የህወሃት የበላይነት በሰራዊቱ ውስጥ መኖሩን በመረጃ በመሞገት ሀረር በተደረገ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠሚ ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ የሚፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል፤ (ሙሉቀን ተስፋው)

ጠሚ ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ የሚፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጡ ይገባል፤ (ሙሉቀን ተስፋው) በኦሮሚያ ክልል በብዙ ዞኖች አማሮች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ ለምሳሌ በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ቡኖ በደሌና ሌሎችም የአዲስ አበባ ዙሪያ ዞንን ጨምሮ አማሮች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ አንዱ ሲያቆም ሌላው እየተከተለ ሁሉም ቦታ ተፈናቃይ ብቻ ሆኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ የሚፈናቀሉት በሕወሓት ትእዛዝ ነው ማለት ትልቅ ሞኝነት ነው፡፡ ሁሉም አማሮች እየተፈናቀሉ ያሉት ለአማራ ተወላጆች ከ2 ሔክታር መሬት በላይ አይገባቸውም በሚል ከኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በወረደ ትእዛዝ ነው፡፡ ከዚህም ባለፈ አንዳንድ የፀጥታ አካላት በአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባና እንግልት ያደርሳሉ፡፡ ለምን ብለው የሚጠይቁ በወንጀለኛነት ይታሠራሉ፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆነው ከአመያና ኖኖ ወረዳ ቤት ንብረታቸው ወድሞ እንደገና 14 ዓመት በላይ እስር ተፈርዶባቸው በአምቦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አማሮች አሉ፡፡ የሚፈጠሩ አጋጣሚዎችን ሁሉ ወደብሔር ግጭት ለመውሰድ የሚጥሩ አካላት በሁለቱም በኩል እንዳሉ እሙን ነው፡፡ ይህ ችግር የኦሮሞ ሕዝብ ችግር እንዳልሆነ እናምናለን፡፡ ችግሩ የሚያስፈልገው ፖለቲካዊ መፍትሔ ነው፡፡ አቶ ለማና ዶክተር ዓቢይ ለአገር አንድነት እንሠራለን እንደሚሉት የዚህን ጉዳይ በአፋጣኝ መልስ ሊሰጡት ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን የሚከተለውን ቀውስ ለመተንበይ የግድ ነብይ መሆን አያስፈልግም፡፡ ስለሆነም በሰከነ አእምሮ የሚያስብ ማንኛውም ፍጡር ሁሉ ይህን ኢሰብአዊ ድርጊት እያወገዘ ውስብስብ ችግር ውስጥ ከመግባታችን በፊት ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ልንጠይቅ ይገባል፡፡
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አራት ወታደራዊ ጥቃቶችን ሰነዘረ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አራት ወታደራዊ ጥቃቶችን ሰነዘረ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ /አዴኃን/ ትላንት ግንቦት 18 ግንቦት ለ ግንቦት 19 አጥቢያ ከሌሊቱ 6፡ 00 ላይ በስናን ወረዳ አባ ጃኒ ጫካ በሚገኘው የወያኔ ህወሃት ወታደራዊ ጦር ሰፈር ላይ ወታደራዊ ጥቃት ሰነዘረ። እንዲሁም በተመሳሳይ ቀንና ስዓት ከህወሃት ወያኔ አገዛዝ ጋር ጋብቻ በመፍጠር አማራን አሁንም ለባሰ ህወሃታዊ ምርኮና ባርነት አሳልፎ ለመስጠት ቆርጠው በተነሱት የጎንጅ ቆለላ ወረዳ አስተዳድር ኃላፊ አቶ ጥጋቡ ደምስ፡ የቢቡኝ ወረዳ አስተዳድር ሃላፊ አቶ ጥላሁን ተረፈ እና የአዴት ወረዳ አስተዳድር ምክትል ኃላፊ አቶ ደረሰ ክንዱ በተባሉ የወያኔ ቅጥረኞች ቤት ላይ ወታደራዊ ጥቃቶችን አድርሷል። አማራው አረመኔያዊና አሰቃቂ በሚባል ደረጃ እንደ በግ በሚታረድበት እና አማራ ስለሆነ ብቻ በዘር ጅምላ በሚፈናቀልበት በዚህ ስዓት ግንቦት 20 ነጻ የወጣንበት የድል በዓል ነው እያሉ የህወሃቶችን ርባና ቢስ መዝሙር በሚዘምሩ በሚያዘምሩ ቅጥረኛና ህወሃትን አምላኪዎች ላይ የተሰነዘረ ሲሆን አሁንም ከህወሃት ወያኔ ጋር ተባብረው ጸረ አማራ የባርነትና ምርኮ ቀምበር ለመጫን በቅጥረኛነት በሚሰለፉ ሃይሎች ላይ የሚሰነዘረው ወታደራዊ ጥቃት ከዚህ በከፋ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ህዝብ ትግል አይደራደርም!!! (ፍፁም አየነው)

የአማራ ህዝብ ትግል አይደራደርም!!! (ፍፁም አየነው) የነገን ተስፋ መገንባት ሚቻለው ዛሬ በምንሰራው ትልቅ ስራ ነው፡፡ተስፋ በተግባር ስራ መመስረት አለበት፡፡ያላከበርካት ዛሬ ፤ነገ አታከብርህም፡፡ የትግል ፍሬ በሂደት የሚመጣ እንጂ በአንድ ጀንበር የሚሞላም ሆነ የሚፈፀም አይደለም፡፡ ….የጀመርከውን የትግል ፍሬ ባልመረጥከው ሁኔታ ጠላትህ ይሰጠኛል ብለህ ምታስብም ሆነ ምጠብቅ ከሆነም ያኔ አንተ ሞተሃል….፡፡ጠላትህ ያለ ጦርነት የማረከህ ታጋይ ማለት አንተ ነህ፡፡የአራጆችህ እና የጮሌ ጠላቶችህ መሪነትና ዳኝነት ውስጥ ጭላንጭል ነፃነት አታገኝም፡፡አገኘው ብትል እንኳ ወይ ብልጭልጭ ወይ ወጥመድ ነው፡፡የሰው ልጅ ለነፃነት መታገል ተፈጥሯዊው ባህሪው ቢሆንም ጠላትህን አሸነፍኩ ማለት የምትችለው ነፃነትህን በእጅ ይዘህ ነው፡፡ያለ ትግል የምታመጣው ነፃነት ተንበርካኪነት ፣ተገዢነት ነው ሊሆን የሚችል…. ስለ ምንም ጉዳይ ብለህ ትግል ችላ ማለትም ነፃነት አሳልፎ ለመስጠት መዘጋጀት ነው፡፡ራስ ላይ ጦርነት ማወጅም ነው፡፡ በእጅ የሌለ ነፃነት ድል የለበትም ደግሞም ሆሮበትም አያውቅም፡፡ ማንም ሰው በሰራው ልክና መጠን ነው ውጤት ሚያገኘው ማለትም በትክክለኛው አሰራር እና ሂደት እስከሰራ ድረስ፡፡በትግል መስመርም ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ስለዚህ ማንኛውም ታጋይ ትግል ከእራሱ ነው መጀመር ያለበት በታገለበት መጠን ደግሞ ያሸንፋል፡፡ራሱን ማወዳደር ያለበትም ከእርሱ በተቃራኒ ከተሰለፈ ጠላቶቹ እና ተቀናቃኞቹ ጋር ነው እንጂ ከሚበልጡት ወዳጆቹ ጋር መሆን የለበትም፡፡ በጣርነው ልክ እናሸንፋለን፡፡በአባከነው ጊዜና ስራ መጠንም ዋጋ እንከፍልበትለን፡፡ የሰው ልጅ ከትግል ውጭ ሆኖ መኖር አይችልም፡፡ በአለማዊም ሆነ በመንፈሳዊ ህይወት ውስጥም ቢሆን፡፡ በአለማዊ ህይወቱ በኑሮ ሂደቱ ፣በምጣኔ ሃብት አቅሙ ፣ነፃነትን ፍለጋ ፣በቤተሰባዊ አስተዳደርም ሆነ ራስን ከመምራት ጀምሮ ካሉ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የነውረኛው ብአዴን ጉድ!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ከታች የታተመው ገጽ ነውረኛው ብአዴን በ1986 ዓ.ም. ባሳተመው ድርጅታዊ ፕሮግራም ገጽ ሁለት ላይ ይገኛል። የሕወሓቱ ነውረኛ ድርጅት ብአዴን በፕሮግራሙ መግቢያ ላይ ፋሽስት ወያኔ «የአማራ ክልል» በሚል ከፈጠረው ክልል ውጭ የሚኖሩ አማሮችን «በአማራ ብሔር ስም የሚነግዱ ነፍጠኛ» ፣ «ትምክህተኞች» እና « የሌሎችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጨቋኞች» ሲል ይገልጻቸዋል፤ እነሱንም እንደማይወክል ይነግረናል። በብአዴን አስተሳሰብ ዛሬ በአምቦ፣ በኢሉ አባቦራ፣ በመተከል፣ በጅማ፣ ወዘተ. . . የሚኖሩና ቤታቸው እየተቃጠለ፣ ንብረታቸው እየተወረሰ፣ እየተገደሉ፣ እጃቸው እየተቆረጠና ቤት ተዘግቶባቸው እየተቃጠሉ እንዲፈናቀሉ እየተደረጉ ያሉት አማሮች «በአማራ ብሔር ስም የሚነግዱ ነፍጠኛ» ፣ «ትምክህተኞች» እና « የሌሎችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጨቋኞች» ናቸው። ከመተከል፣ ከአምቦ፣ከጅማ፣ ከኢሉ አባቦራ፣ ወዘተ ተፈናቅለው በየመንገዱ ስንት መከራ እየተቀበሉ ባሕር ዳር ድረስ ተጉዘው ችግራቸውን ለብአዴን ለማስረዳት ጽሕፈት ቤቱ ደጃፍ ሲደርሱ «ለምን ለአቤቱታ መጣችሁ?» እየተባሉ በሕወሓት/ብአዴን ቅልብ ፖሊሶች የሚታሰሩት፣ ከእንደራሴው ቢሮ ፊት ለፊት ባለው ሜዳ «ማደር አትችሉም!» የሚል መልስ እየተሰጣቸው የሚባረሩት ለብአዴን «አማራ ክልል» ከሚባለው ውጭ ያሉ አማሮች «በአማራ ብሔር ስም የሚነግዱ ነፍጠኛ» ፣ «ትምክህተኞች» እና « የሌሎችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ጨቋኞች» ስለሆኑና ብአዴን ደግሞ በፕሮግራሙ እንደነገረን የሚታገለው ነፍጠኞችና ተባባሪዎቻቸው ሲል የሚገልጻቸው የአማራ ክልል ከሚባለው ውጭ የሚኖሩ አማሮችን ለመቃወምና ለመታገል ስለሆነ ነው። ነውረኛው ብአዴን ባሳለፍነው ሳምንት በደብረ ብርሃን ከተማ ተቆርቋሪ የአማራ ልጆች ከጎጃም መተከል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ርዳታ ይሆን ዘንድ የጀመሩትን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ያስቆመው፤ እሁድ እለት የፋሲል ከነማና የባህር ዳር ከነማ የእግር
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት ከቤኒሻንጉል ለተፈናቀሉ አማራዎች የ30 ሺ ብር ድጋፍ አደረጉ ።

“ከገንዘብ በላይ ልብ ነው ይዘን የመጣነው!” የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት አታላይ ዛፌ፣ አለነ ሻማ፣ ጌታቸው አደመ እና እነ አክቲቪስት ንግስት ይርጋ ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉ አማራዎችን ጠይቀዋል፣ ወገናዊ መልክትም አስተላልፈዋል። የ30 ሺ ብር ድጋፍም አድርገዋል። “ከገንዘብ በላይ ልብ ይዘን ነው የመጣነው!” ብለዋል አቶ አታላይ ዛፌ $bp("Brid_14563_1", {"id":"12272","video":"228509","width":"550","height":"309"});
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከመተከል (ቤኒሻንጉል) የተፈናቀሉት አማሮች ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ ።

ከመተከል (ቤኒሻንጉል) ተፈናቅለው ለ1 ወር ከሳምንት በባህር ዳር ከተማ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙት ወገኖች ሁለት አማራጭ ቀርቦላቸው ሁለቱንም አልተቀበሉትም። እነሱ ያቀረቡት አማራጭ ደግሞ በመንግስት ተቀባይነት አላገኘም። የመንግስት አካላት ተፈናቃዮች ወደነበሩበት አካባቢ እንዲመለሱ፣ አልያ ግን ቤተሰቦቻቸው ይኖሩበታል ወደሚባል ቀበሌና ወረዳ እንዲበተኑ ውሳኔውን ነግሯቸዋል። ሆኖም ተፈናቃይ ወገኖች ወደነበሩበት ቦታ ለመመለስ የደህንነት ዋስትና እንደሌላቸው በመግለፅ አልተቀበሉትም። በሁለተኛነት የቀረበላቸው “አማራጭ” ደግሞ ወደ “ቀደምት” የቤተሰቦቻቸው ቀዬ እንዲበተኑ የሚለው ነው። ተፈናቃዮቹ ሀብት ንብረት ያፈሩበት፣ ወልደው ከብደው የኖሩበት አካባቢ አሁን የተፈናቀሉበት እንደሆነ በመግለፅ ሌላ የሚሄዱበት ቀዬ እንደሌላቸው ገልፀው አማራጩን አልተቀበሉትም። በሌላ በኩል ግን ተፈናቃዮቹ ለእርሻና መኖሪያ በሚመች ቦታ የአማራ ክልል መንግስት እንዲያሰፍራቸው መጠየቃቸውን በማስታወስ፣ ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንዳላገኘ ገልፀውልኛል። ተፈናቃዮቹ አሁን በሚገኙበት ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ የአማራ ህዝብ ድጋፍ ሳይለያቸው ለጊዜው ውሉ ያልታወቀ ጊዜ እያሳለፉ መሆናቸውን ይናገራሉ። “ህዝብ እየደገፈን ነው። ሆኖም ዘላቂ መፍትሄ ተሰጥቶን ሰርተን የምንኖርበትን ጊዜ እንናፍቃለን” ብለውኛል። ተፈናቃይ ወገኖች የት ይሂዱ??
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በምስራቅ ጎጃም ብአዴን በድንገት መሣሪያ መግፈፍ ጀምሯል፡፡

በምስራቅ ጎጃም ብአዴን በድንገት መሣሪያ መግፈፍ ጀምሯል፡፡ (ሙሉቀን ተስፋው) በሁለት እጁነሴ ወረዳ ቁስቋም ቀበሌ በግምት ከሞጣ 25 ኪ.ሜ አርሶአደሮችን በድንገት በመክበብ መሳሪ ለመንጠቅ የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አበረ በላይ፣ የወረዳው ሚሊሻ ኃላፊ ጌታቸው እንዲሁም ሌሎች በርካታ አበሮቻቸውን ይዘው እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል፡፡ በዚህም ግንቦት 1 ቀን ሁለት መሳሪያ የወሰዱ ሲሆን አቶ አዲሱ የኋላ የተባለን ግለሰብ በአፈሙዝ በመምታትና ፒፒስ መሣሪያ በመወሰድ ግለሰቡ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሕክምና ላይ እንደለ ተነግሯል፡፡ ሁለት መሣሪያ አንድ አልቢንና አንድ ፒፒስ መሣሪያዎች እንደወሰዱ ሕዝቡ መሣሪያውን በመደበቁና በመከላከሉ ሌላ ሰው መንጠቅ አልቻሉም፤ ሆኖም በሌሎች የምስራቅ ጎጃም አካባቢዎችም መሣሪያ ለመንጠቅ እቅድ ስላለ ገበሬዎች መሣሪያቸውን እንዳይቀሙ በንቃት እንዲጠብቁ መረጃውን ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል እነዚህ ሆድ አደሮች ማለትም አቶ አበረ በላይ የጎንቻ ሲሶነሴ ባህር ጊዎርጊስ አካባቢ የተወለደ ሲሆን ሌላኛው አቶ ጌታቸው ደግሞ የመካነ ሰላም አካባቢ ልጅ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡    
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“አሁንስ እቺ ሀገር ኢትዮጵያ አልመስል አለችን” በኦሮሚያ ክልል መሬታቸውን የተቀሙ የአማራ ገበሬዎች

“አሁንስ እቺ ሀገር ኢትዮጵያ አልመስል አለችን” በኦሮሚያ ክልል መሬታቸውን የተቀሙ የአማራ ገበሬዎች  
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጎንደር ወጣቶች በከተማው ባለስልጣናት ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ።

ጎንደር ቀበሌ 18 አበራ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ግቢ የሚገኝ የዲያቆናት መኖርያዎች መቃጠላቸውን ምንጮች ገልፀዋል። ህዝብ የመንግስት አካል እንዲደርስ ጥረት ቢያደርግን የእሳት አደጋም ሆነ ሌሎች የመንግስት አካላት/ተቋማት ሊደርሱ አልቻሉም። የመንግስት አካል ሊደርስ ባለመቻሉ ሕዝብ እሳቱን ተረባርቦ አጥፍቷል። የከተማው ወጣቶች የመንግስት አካላት እሳቱን ለማጥፋት ጥረት አለማድረጋቸውን በመቃወም ጩኸት ሲያሰሙ እንደነበር ተገልፆአል። ወጣቶች “ለኃይማኖታችን ይፈሳል ደማችን” የሚል መፈክር እያሰሙ ወደ ፒያሳ ሲሄዱ ኮሌጅ አካባቢ ልዩ ኃይል እንዲመለሱ አድርጓል ተብሏል። በቃጠሎው ወቅት የመንግስት አካል እንዲደርስ ማንቂያ ይሆን ዘንድ ሕዝብ በርካታ ጥይት እንደተኮሰ ምንጮች ገልፀዋል።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሕዴድ የዞንና የወረዳ አመራሮች የአማራውን መሬት እየነጠቁ ለቄሮ በማደል ላይ ናቸው።

2 ሺህ አባወራዎች ችግር ላይ ናቸው። ለዓመታት በህጋዊ መንገድ ስንጠቀምበት የኖርነውን የእርሻ መሬት እየተወሰደብን ነው ሲሉ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ የሚገኙ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች ቅሬታ አቀረቡ፡፡ በወረዳው በሚገኙ አዋዲ ጉልፋና አጅላ ዳሌ ቀበሌዎች 2ሺህ አባወራዎች ችግር እንዳጋጠማቸው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ከ20 ዓመታት በላይ የእርሻ መሬት ግብር የከፈሉበት ካርኒና የመሬት ማረጋገጫ ደብተር እንዳላቸው የአማራ ብዙኋን መገናኛ ድርጅት አረጋግጧል፡፡ ከአካባቢው ህዝብ ጋር ለዘመናት ተፋቅረንና ተዋልደን እየኖርን ባለበት ወቅት የወረዳና የዞን አመራሮች መሬታችንን እየነጠቁ ለቄሮ እየሰጡብን ነው ብለዋል ቅሬታ አቅራቢዎቹ፡፡ ለበርካታ ዓመታት ግብር ሲከፍሉ የቆዩ በርካታ አርሶ አደሮችን አናውቃችሁም፤ መባላቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ ለቅሬታ የመጡ የአማራ ተወላጆች ለአማራ ብዙኋን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል፡፡ ምንጭ:- የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የብሔርተኝነት እና የጽንፈኝነት ልዩነት (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

እንደምታውቁት ብሔርተኝነትንና ጽንፈኝነትን ያመጡብን የጥፋት ኃይሎች (ወያኔ/ኢሕአዴግ፣ ኦነግና ሸአቢያ) ናቸው፡፡ ብሔርተኝነት የሚጎዳ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ብሔርተኝነት ተፈጥሯዊና ጤናማ ስለሆነ፡፡ ብሔርተኝነት ተፈጥሯዊና ጤናማ ከሆነ ከነኝህ የጥፋት ኃይሎች በፊትም አማራ ሀገር ያሥተዳድር በነበረበት ረጅም ዘመናትም ነበረ ማለት ነዋ? ብላቹህ ትጠይቁ ይሆናል፡፡ መልሱ አማራ ብሔርተኝነት ለሀገር አንድነትና ህልውና አደጋ ይፈጥራል ብሎ በመሥጋት ብሔርተኝነትን ይጸየፍ ይንቅ ስለነበረ ብሔርተኝነትን ያቀነቅን አልነበረም የሚለው ነው፡፡ ያው አማራ ብሔርተኝነትን የናቀውና የተጸየፈው ብሔርተኝነት ተፈጥሯዊ ሆኖ ህልው ስለሆነ እንደሆነ ልብ በሉ፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮው ለራሱ ለግሉ አሳቢ ቆርቋሪ ነው፡፡ ይሄንን ስሜት አሐዳዊነት ወዳለው ቡድን ስትወስዱት ማለት ነው ብሔርተኝነት ማለት፡፡ ሰው ለራሱ ካሰበ፣ ለራሱ ከተቆረቆረ፣ ነፍሱን ከወደደ ሌሎችን አያጠቃም አይተነኩስም፡፡ ለዚህ ነው ብሔርተኝነት ሊያስጠብቀው የሚፈልገው የቡድን ጥቅም እያለም ጤናማ የሚሆነው፡፡ ጽንፈኝነት ማለት ደግሞ ለኔ ብቻ ማለት ነው፡፡ ስለዚህም የጽንፈኝነት አስተሳሰብ ካላቹህ ጥቅማቹህን ሌሎቹን በማጥፋት ላይ ትመሠርታላቹህ፡፡ ለኔ ብቻ የምትሉ ከሆነ ደግሞ ሌሎቹ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ እናንተን ለማጥፋት እንዲገደዱ ታደርጓቸዋላቹህ፡፡ አሁን የሁለቱን ልዩነት ተረድታቹሀል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እዚህ ላይ “አማራ ለኔ ብቻ በማለቱ አይደለም ወይ ሀገሪቱን በብቸኝነት ሲገዛ የኖረው?” ትሉ ይሆናል፡፡ ነገሩን ልብ ብላቹህ ከተመለከታቹህት ግን እውነታው ይሄ አይደለም፡፡ አዎ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐቲት ምክንያት ማለትም እግዚአብሔር ለቅዱስ ዳዊት “በትርን (ሥልጣንን) ከዘርህ አላጠፋም!” ብሎ በገባለት ቃል መሠረት በአውሮፓ፣ ዓረቦችን ጨምሮ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በእስያ፣ በአፍሪካ የዘር ሐረጋቸውን ከእስራኤሉ ንጉሥ ከዳዊት (ከዳውድ) የሚመዙ ነገሥታት እንደገዙ ሁሉ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቤምሻንጉል ክልል ደህንነት ቢሮ አባል በአሶሳ ከተማ ተገደለ።

በቤምሻንጉል ጉምዝ መዲና አሶሳ ከተማ የሰሞኑን የአማራወች መፈናቀል በስውር አስፈፅሟል የተባለ የቤምሻንጉል ክልል አስተዳደርና ፀጥታ(ደህንነት) ቢሮ አባል የሆነ እስማኤል አብዱ የተባለ የደህንነት አባል አሶሳ ከተማ የቀድሞ ስታዲየም ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰወች ተገድሎ ተገኝቷል።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአስራ አራት አመቱ ታዳጊ የአበጥር ወርቁ ጉዳይ በአማራ ላይ የሚሰሩ ሴራ ፣ ተንኮልና ደባ አንዱ ማሳያ ነው።

የአስራ አራት አመቱ ታዳጊ የአበጥር ወርቁ ጉዳይ በአማራ ላይ የሚሰሩ ሴራ ፣ ተንኮልና ደባ አንዱ ማሳያ ነው።Minilik Salsawi   ወያኔና ሻእቢያ አማራ ታሪካዊ ጠላታቸው እንደሆነ ከመናገር አልፈው በተግባር አማራን እያሳደዱ እየገደሉ አያፈናቀሉና ኢሰብዓዊ ድርጊት እየፈጸሙበት ይገናል። እንዲሁም በነሱ ድጋፍ የሚተዳደሩና ቀለብ የሚሰፈርላቸው ሚዲያዎች ስለ ኣማራው ጉዳይ አንድም ትንፍሽ ላለማለት ተማምለዋል።   ሆን ተብሎ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በገሃድና በድብቅ እየተደረገበት ነው። ይህ ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ነው። በአማራ ስም ከመነገድና አማራውን ከማስገደል ከማሳሰር ጀምሮ በአማራው ላይ መንግስታዊ ወንጀል ተፈጽሟል። ይህ መንግስታዊ ሽብር በአማራ ላይ ሲፈጸም ከመንግስት ባለስልጣናት ጀምሮ እስከ ተቃዋሚ ነን ባዮች ድረስ የዚሁ ግፍ ተባባሪ ሆነዋል።   በቤንሻንጉል ጉምዝ በ አማራ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ምስክር ነው። አማራው ከመፈናቀል ጀምሮ እስከ መታረድ ሲደርስበት ለመሸፋፈንና አድበስብሶ ለማስቀረት የሚደረገው ሙከራ ነገ ሃገሪቷ ላይ ከባድ አደጋ ያመጣል። የአስራ አራት አመቱ የአበጥር ወርቁ ጉዳይ የዚሁ ሴራ ተንኮልና ደባ አንዱ ማሳያ ነው። #MinilikSalsawi
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመተከል ዞን ታዳጊው ላይ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡

በመተከል ዞን ታዳጊው ላይ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡ በመተከል ዞን ዲባጢ ወረዳ በአንድ የአማራ ተወላጅ ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደበሌ በልጋፎ ተናገሩ፡፡ የተሰራው ወንጀል ወረዳውን እንዳሳዘነ አቶ ደበሌ ገልፀው እንደዚህ አይነት ችግሮች ዳግም እንዳይፈጠሩ ማህበረሰባዊ ውይይቶችን እያደረግን ነው ብለዋል፡፡የተጠርጣሪዎችን የምርመራ ውጤትም ለህዝብ እንገልፃለን ብለዋል፡፡ የ 14 ዓመቱ ተጎጂ አበጠር ወርቁ አጎት አቶ አያሌው አበረ በበኩላቸው በወንድማቸው ልጅ ላይ የደረሰው አስነዋሪ ድርጊት እንዳሳዘናቸው ገልፀው፣ተጎጂው ለህክምና ከፓዊ ወደ ባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል እንደገባ አረጋግጠውልናል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደበሌም ለከፍተኛ ህክምና ወደ ባህርዳር እንደሚሄድ ቀደም ብለው ያረጋገጡ ሲሆን፣ወረዳው ከተጎጂው ጎን ይቆማልም ብለዋል፡፡ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቱን ለማጥፋትም እንደሚሰራ ተገልጧል፡፡ በዲባጢ ወረዳ የአማራ፣የኦሮሞ፣የጉምዝ፣የሽናሻ ወ.ዘ.ተ ህዝቦች በጋራ እንደሚኖሩ አቶ ደበሌ ተናግረዋል ፡፡ የሺሀሳብ አበራ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአቦይ ፕሮፌሰር መስፍን መነሻና መድረሻ

ከቴዎድሮስ ሃይለማሪያም (ዶ/ር) በቀደምለት አቦይ መስፍን ‹‹የአማራ ፋሽስቶች›› የምትል ነገር በፊስቡክ ለጥፈው ጥቂት ትኩረት መሳብ ችለው ነበር፡፡ ምናልባትም ሶስት ተከታታይ የስድብ መፃህፍት ስላወጡ ፣ ከተሳካላቸው አራተኛውን በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ይዘው ለመምጣት ሳያስቡ እንደማይቀሩ እገምታለሁ፡፡ እስከዚያው መስፍን ባረጁበት ማናለብኝነት ‹‹ፋሽስት›› የሚለውን ፍረጃ የተጠቀሙት ‹‹እናትክን›› እንደሚለው የብልግና ስድብ በመሆኑ መልስ መስጠት አያስፈልገውም ነበር፡፡ ነገር ግን በርካታ ሰዎች ሰውየው ይህን ያህል የበገኑበትን ምክንያት ስለጠየቁኝ እንደሚከተለው ላስረዳ፡፡ 1. የመስፍን መነሻ (በውይይት መፅሄት ቁ.21 ላይ ‹‹አስቸኳይ መፍትሄ የሚሻው የአማራ ህዝብ ጥያቄ›› በሚል ርዕስ ያቀረብኩት ፅሁፍ ነው፡፡ እሳቸውን የሚመለከተው በአጭሩ እነሆ) ‹‹የመስፍን መላምት ፤ ‹‹አማራ የለም !›› ‹‹አማራ የለም!›› የለዘብተኛ ፖለቲካ ፍልስፍና ቃና ያለውና ብዙውን ጊዜ ራሳቸውንም ብሄረሰቡንም ከ‹‹አማራ›› ይልቅ ‹‹አማርኛ ተናጋሪ›› ብለው ከሚጠሩ ወገን የሚሰነዘር ነው፡፡ እንደምናስታውሰው ፕሮፌሰር መስፍንን ትዝብት ላይ የጣላቸው ወለምታ ነበር፡፡ ምናልባት በመጥፎ ወቅት የተሰነዘረ ቀና አስተያየት ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንዳንዶች ‹‹የክህደት ቁልቁለት›› ብለውታል፡፡ መስፍን ከዚያ ታሪካዊ ክርክር በኋላ ሃሳባቸውን ያሻሽሉት ወይስ በዚያው ይፅኑ አላውቅም፡፡ አንዳንዴ ግን የትችት አለንጋቸውን ወይ የአማራ ህዝብ ላይ ወይ የአማራ ልሂቅ ላይ መሰንዘር ስለሚቀናቸው ፣ መቼም የሌለ ህዝብ አይተቹም የሚል እምነት አለኝ፡፡›› 2. የመስፍን መድረሻ (በግዮን መፅሄት ቅፅ 1 ቁጥር 6 ላይ ‹‹የአማራ ምሁራንና ብአዴን ከጣውንትነት ወዴት?›› በሚል ርዕስ ያቀረብኩት ፅሁፍ ነው፡፡ እሳቸው የቆነፀሉት እነሆ:- ‹‹የአማራ ብሄርተኝነት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ስጋት የማይሆንበት ተጨማሪ ምክንያት የብሄረሰቡ ትክለ ስብዕና
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጂማ ሊሙ ሦስት አማሮች ሌሊት ላይ በገጀራ ታርደዋል

በጂማ ሊሙ ዛሬ የሚከበረውን የክርስቶስ እርገት ለማክበር በማታ ወደ ጨንጊ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ላይ የነበሩ ሦስት የአማራ ተወላጆ በገጀራ ታርደው የተገደሉ ሲሆን አንድ ሰው በከባድ ጉዳት ሕክምና ገብቷል፡፡ ሁሉም የተገደሉት የገብረ መንፈስ ቅዱስ ማኅበርተኞች ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት በ1999 ዓም በርካታ አማሮች በሻሻ አቦ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በገጀራና በእሳት መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ሀብታም የሆኑ የአማራ ተወላጆች በብዛት እየተገደሉ ነው፡፡ ትናንት በገጀራ ታርደው የተገደሉት ስም ዝርዝር 1. አስማማው አማረ 2. መርሻ መኮንን 3. መኳንንት የተባሉ ሲሆን የቆሰለው ብርሀኑ ጌቱ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቃሉ አማራዎች እና የህገመንግስቱ አንድምታ (ዘላለም እሼቱ)

ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቃሉ አማራዎች እና የህገመንግስቱ አንድምታ (ዘላለም እሼቱ) በሀገሪቱ የመዘዋወር መብት እንዲሁም ቋሚ የመኖሪያ ቦታ የመመስረት ለሁሉም ዜጎች በዘር በሀይማኖት በብሔር ልዩነት ሳይደረግ የተሰጠ ሰፊ መብት መሆኑን ከህገመንግስቱ አንቀፅ 32 ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል። ይህ መብት ለኢትዮጵያውያን ብቻ የተሰጠ መብት አይደለም በህጋዊ መንገድ የገቡ የውጭ ሀገር ዜጎችን ሁሉ የሚያጠቃልል መብት ነው። የዚህ ፁሑፍ አላማ ግን በተለያዬ ጊዜ ስለሚፈናቀሉ ህዝቦች በተለይም የአማራ ህዝብ ስለደረሰባቸው የመብት ጥሰት እና በዚሁ ምክነያት ስለደረሰው ጉዳት መፍተሔ እና ስለተጠያቂ እንዲሁም ጠያቂ አካላት የሚዳስስ ነው። የአማራ ክልል ህዝቦች በተለያዬ ጊዜ በየቦታው በየጊዜው ሲፈናቀሉ ማየት እንደልምድ በመቆጠሩ ሰሞኑን ከቤንሻንጉል ክልል ስለተፈናቀሉት 527 አባውራዎች መንግስት ዝም ማለቱ ለቅሶ ሲደጋገም እንደ ዘፈን ተቆጥሮብናል እነዚህ ሰዎች የተፈናቀሉት መነሻው በሁለት ግለሰቦች የግል ግጭት መሆኑን መረጃ በተፈናቀሉት ሰዎች በኩል ልናገኝ ችለናል። የእነዚህ ሰዎች የደረሰባቸው መብቶች የህገመንግስቱን አይነኬ የተባሉትን እና ባስቸኳይ ጋዜ አዎጁ እንኳን የማይታገዱ መብቶች ተጥሰዋል። እነዚህ ተፈናቃይ ሰዎች የተጣሱባቸው እንዲሁም በጥቅሉ የአማራ ብሔር የደረሰበት የመብት ጥሰቶች። 1) መዘዋወር ነፃነት የኢፌድሪ ህገመንግስት በጊዜ በቦታ በዘር እንዲሁም በሀይማኖት ልዩነት ሳይደረግ ለማንኛውም ኢትዮጰያዊ በኢትዮጰያ ውስጥ ተንቀሳቅሶ የመስራት እንዲሁም መኖሪያ ቦታ የመመሰረት መብት በአንቀፅ 32(1) ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል ነገር ግን ቤኒሻንጉል ላይ አማራዎቹ ግን የዚህ ሰፊ መብት ተጠቃሚ ሊሆኑ አልቻሉም። 2) የእኩልነት መብት አማራ በመሆናቸው ብቻ ነው ከቤኒሻንጉል ክልል እንዲፈናቀሉ የተደረጉት። በዚህም አማራ ከሌሎች
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፕሮፌሰር መስፍን ምን ነካቸው? (ጌታቸው ሺፈራው)

በጠዋቱ የፕሮፌሰር ገፅ ላይ አንድ ፅሁፍ አነበብኩ። “የአማራ ፋሽዝም” ይላል። ጥቅስ ውስጥ እንኳን አላስገቡትም። እንደተረጋገጠ ሀቅ የፃፉት ነው። አላመንኩም። ደግሜ አየሁት። ከሌላ ሰው ጋር አየሁት። ያው ነው! ፋሽዝም ወንጀል ጭምር ነው። ሌሎች ላይ የዘመተ፣ የፈጀ ርዕዮት አለም ነው። በጀት ብቻ ሳይሆን በመርዝ ጋዝ፣ የሰውን ልጅ ታይቶ በማይታወቅ ጭካኔ የጨረሰ ርዕዮት አለም ነው። ፋሽዝም ፋሽስቶቹ የእኛ ነው ብለው የወሰዱት ርዕዮትም ጭምር እንጅ ፍረጃ ብቻ አይደለም። ፕሮፌሰር ርዕዮቱን እንደ ህዝብ የለም ለሚሉት አማራ ጠቅልለው ሲሰጡት አይቼ ማመን አቃተኝ። ለዚህ ደግሞ መነሻቸው ስሙን ያልጠሩት ግለሰብ ነው። ምን አልባት በማይታወቅ ስም ፌስቡክ ላይ ፅፎ አንብበው ይሆናል። እኔ ጠይቄ ማን እንደሆነ አላወኩም። እሽ ይሁን! ፕሮፌሰር በግለሰብ ማንነት አምናለሁ የሚሉ ሰው ናቸው። አንድ ሰው ተነስቶ ስለ ፈለገው ሊፅፍ ይችላል። ለምሳሌ አንዱ የውጭ ሀገር ቱሪስት ስለ ወደደው ሕዝብ አሞካሽቶ ሊፅፍ ይችላል። ያ የውጭ ሰው ስለ ሌላ ሀገር ሕዝብ ስለፃፈ በዛ አንድ ፀሀፊ ስም ሕዝብ ይፈረጃል? ያውም ወንጀል በሆነ ርዕዮት አለም? እሽ! ያ ግለሰብ ከፃፈለት ሕዝብ የወጣ ይሁን። አንድ ግለሰብ ከፃፈው የግል አስተያየት ተነስቶ ሕዝብ ወንጀል በሆነ ርዕዮት ይፈረጃል? ወኪልነቱም ይቅር! ያ ሰው ሆን ብሎ በህዝብ ስም የሚጠቀም (ደህንነት) ይሁን ታጋይ ሳያረጋግጡ? ስሙን ሳይጠቅሱልን ህዝብ ይወነጀላል? የህዝብ ርዕዮት ዓለም ይሆናል? ሰውየው ህዝብን ወክያለሁ የሚልም ይሁን። ህዝብን ወክያለሁ ብሎ የተናገረ ሁሉ የፃፈው ሕዝብን ለመፈረጅና ለመወንጀል ያበቃል? “አማራ ነን፣ የአማራ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ፋሺዝም (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወርቅ መሆኑን ከተናገረ ከጥቂት ወራት በኋላ በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ላይ ተሳታፊ ነበርሁ፡፡ በጉባኤው ላይ ባደርገረሁት ንግግር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋሺስታዊ ንግግር አደረገ ብዬ ነበር፡፡ ስወጣ የቅርብ ወዳጄ የነበረ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተቆጥቶ እጆቹን እያወናጨፈ ‹‹አይባልም! አይባልም!›› እያለ ወደኔ መጣ፡፡ እኔም ረጋ ብዬ ‹‹አዎ አይባልም፤ ለዚህ ነው እኔም የተናገርሁት!›› ወዳጄ አምባሳደሩ የወጣለት ምሁር ነበር፡፡ ነገር ግን የፋሺስት አሽከር መሆኑ ገሀድ እንዳይወጣበት ሰግቶ ነበር፡፡ ያው አንድ ፋሺስት በቀደደው ዛሬ ብዙ ፋሺስቶች ተከትለውታል፡፡ እንዲያውም በዚህ ጉዳይ መለስ ዜናዊን የሚያስንቁ ፋሺስቶች ፈልተዋል፡፡ አንድ ምሳሌ «የአማራ ብሄርተኝነት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ስጋት የማይሆንበት ተጨማሪ ምክንያት የብሄረሰቡ ትክለ ስብዕና ነው፡፡ ዐማራ የጥበብ መሃንዲስ ነው፣ ታሪክ ሰሪ፣ ድንበር አስከባሪ፣ አሰተዋይ መሪ ነው፡፡ ለአከርካሪው ሲቃጡት አናት የሚያፈርስ የጀግኖች አውራ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጰያ አማራ የእግዜር የበኩር ልጅ ነው፡፡ በሃይማኖቱ፣ በቁርጠኛነቱ በደግነቱና በትዕግስቱ ያሰበበት ደራሽ ነው፡፡…..» እንዲህ ያለው ባዶ ቀረርቶ ሌላ ባዶ ቀረርቶን ይጋብዛልና አይጠቅምም፡፡ የዚህ ጽሑፍ አማርኛ ቢጠና መልካም ይመስለኛል፡፡  
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

97 የአማራ ተወላጅ የፖለቲካ እስረኞች የት እንደገቡ አልታወቀም

97 የአማራ ተወላጅ የፖለቲካ እስረኞች የት እንደገቡ አልታወቀም (Getachew Shiferaw) ~ባለፉት ሳምንታት የፖለቲካ እስረኞች ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ። እስረኞቹ መንግስት ክስ ማንሳቱን፣ ፍርድ ቤቱም በተነሳ ክስ ላይ የተከሳሽ ጉዳይን የማየት ስልጣን እንደሌለው በመግለፅ ወደ ፍርድ ቤት አንሄድም ብለዋል። ~ሆኖም ፍርድ ቤቱ አልቀረቡም ያላቸውን ተከሳሾች በሌሉበት እስከ አንድ አመት እየቀጣ፣ ቅጣቱን በደብዳቤ ይልክላቸዋል። ተከሳሾች ውሳኔውን አንቀበልም ይላሉ። ~የቂሊንጦ እስር ቤት ፍርድ ቤት ባልተገኙበት የተፈረደባቸውን የፖለቲካ እስረኞች ወደ ቃሊቲ እንዲዛወሩ ሲጠይቅ ተከሳሾቹ ተቃውመዋል። አንዱ የተቃውሞ ምክንያት ከአንድ ወር በፊት ገበየሁ ፈንታሁን የተባለ የባህርዳር ልጅ ወደ ቃሊቲ በተዛወረ በሁለተኛ ቀኑ ለህልፈት በመዳረጉ ነው። ይህ ወጣት ከእነ ሙሉ ጤናው ወደ ቃሊቲ ተዛውሮ ለህልፈት መዳረጉ ሌሎች ተከሳሾች ላይም ስጋት ፈጥሯል። ~ሚያዝያ 30/2010 ዓም በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል ብይኑን አንቀበልም በማለታቸው በተነሳ አለመግባባት ችሎት በመቋረጡ ቂሊንጦ እስር ቤት ያለ ስልጣኑ እስረኞችን ቀጥቷል። ጨለማ ቤት አስገብቷል። ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል። ወደ ዝዋይና ወዳልታወቀ እስር ቤት ተዛውረዋል። ~የቂሊንጦ እስር ቤት የፖለቲካ እስረኞችን ወደ ቃሊቲና ወደ ዝዋይ ለመጫን ሲሞክር ከእስረኞች ተቃውሞ ገጥሞታል። ተከሳሾች በሚደርስባቸው በደል የርሃብ አድማ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት እስር ቤቱ ግንቦት 2/2010 ዓም በጠዋት የሚጀመረውን የቤተሰብ ጥየቃ ከልክሎ በየማማው መሳርያዎችን በመጥመድና በርካታ የፖሊስ ሀይል በማዘጋጀት ሲያስፈራራ እንደነበር ታውቋል። ~የቂሊንጦ እስር ቤት 150 የፖለቲካ እስረኞችን ወደ ሌላ እስር ቤት ለማዛወር ከየዞን ግቢያቸው አስወጥቶ እንደነበር ታውቋል። ሆኖም
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሀት ከአማራው ህዝብ ከፍተኛ አመጽ ሊቀሰቀስ እንደሚችል በስጋት እየገለጸች ነው። (መሳይ መኮንን)

ትኩረት ወደ አማራው (መሳይ መኮንን) ህወሀት በቅርቡ በትግራይ ውስጥ አንድ ሚስጢራዊ ስብሰባ አድርጋ ነበር። በስብሰባው ላይ የህወሀት የጦር መኮንኖች ብቻ የተገኙ ሲሆን መድረኩን የሚመሩት አባይ ጸሀዬ፡ በረከት ስምዖንና የህወሀት ጄነራሎች ነበሩ። ዓላማው የዶ/ር አብይ አህመድን ስልጣንና አካሄድ ከህወሀት ጥቅምና ፍላጎት አንጻር መፈተሽ ነበር። የትግራይ ተወላጆች ከፌደራል መንግስቱ ቁልፍ ቦታዎች ተገፍትረው ወጥተዋል የሚል የከረረ ቅሬታ ከህወሀት የጦር ሹማምንቶች የተሰማ ሲሆን እነአባይ ጸሀዬ ”አሁንም ቁልፍ ቦታዎች በእጃችን ናቸው። መከላከያውን ከህወሀት መዳፍ ፈልቅቆ የሚነጥቅ በተአምር አይኖርም። ዋናዋናዎቹ የመከላከያ ክፍሎች ትግራይ ገብተዋል። የሚያሰጋን ነገር የለም” በሚል ለማረጋጋት መሞከራቸው ተሰምቷል። የሚስጢራዊው ስብሰባ ዋና ዓላማ ከአማራው ህዝብ የሚመጣውን ቀጣይ አመጽ እንዴት እንመክተዋለን የሚል ነበር። ህወሀት ከአማራው ህዝብ ከፍተኛ አመጽ ሊቀሰቀስ እንደሚችል በስጋት እየገለጸች ነው። እነበረከትም በሚስጢራዊው ስብሰባው ላይ እንዲታደሙ የተደረገው ይህን አይቀሬ አመጽ እንዴት መመከት ይቻላል የሚለውን ለመምከር ነው። በረከት ስለህወሀት ጥቅም በአማራው ላይ የተጣበቀ አልቅት መሆኑን በተደጋጋሚ አስመስክሯል። ህወሀት አደጋ ውስጥ ስትገባ ከእነስብሃት ነጋ ጎን ተሰልፎ ምሽግ የሚይዝ መሆኑም ይታወቃል። አሁንም ይህን ‘ከህወሀቶች በላይ ህወህት’ መሆኑን እያሳየ ነው። ሰሞኑን ብአዴን ቁርጡ ይለይለታል የተባለ ስብሰባ ተቀምጦ ከርሟል። እነበረከት የመስመር ክህደት ተፈጽሟል የሚል አጀንዳ ቀርጸው ህወሀት ላይ ያመጹ የድርጅቱን አመራሮች ለማሸማቀቅና ከተቻለ ለማሰር የጠሩት ስብሰባ መፈንቅለ አጀንዳ ተፈጽሞበታል። ለዓመታት የህወሀት ተላላኪ፡ አሽከር፡ ባሪያ እየተባለ ሲረገም የነበረው ብአዴን በተለይም መካከለኛና የታች አመራሩ ”ይለያል ዘንድሮ” ብሎ ተነስቷል። የለማ መገርሳን
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የባህር ዳሩ የብአዴን ኮንፈረንስ መበጣበጡን ቀጥሏል

ቲም ገዱ ሰይፍ በሆነ አንደበት ሕዝቤን ማለት ጀምሯል፤ ፍርሃት ተገፎ በድፍረት ተተክቷል፥ ብአዴን አደጋ ላይ ነው፥ ትልቁ ህዝብ አማራ ባህርዳር ላይ ዱካው እየተሰማ ነው። ከጥሩነህ ይርጋ ገፅ የተወሰደ በረከት ስምኦንና ጥንቅሹ ከዛ አምባዬ የሚባል ወፍጮ ፊት ጋር ነገር ከብዶባቸው ተደናግጠዋል ይላል ዘገባው። የብአዴን ኮንፈረንስ የትናት ውሎ፦ (ረዘም ያለ ነው። ፅሁፉ ትንሽ ብቻ ነው የተስተካከለ እንጅ እንደወረደ ነው። ) የብአዴን ኮንፈረንስ በሰሞኑ ስብሰባ ከተናጋሪዎች ውስጥ ሁለት የኃይል አስላለፍ እንዳለ አመላከቷል፤ #የለውጥ ፈላጊ ቡድን ዶ/ ር አንባቸው መኮነን ፀጋ አራጌ ላቀ አያሌው ንጉሱ ጥላሁን እዘዝ ዋሴ (በትናንትናው መድረክ በረከትን ቀድሞ ያዋረደው ነው) ጌታቸው ጀንበር እና ሌሎች ወጣቶች ሲሆኑ #ከለውጥ ናፋቂው በተቃራኒ #ለማፈራረስ የተሰለፉት በረከት ስምኦን ታደሰ ጥንቅሹ ከበደ ጫኔ ዝማም አሰፋ ህላዊ ዮሴፍ አዲሱ ለገሰ ጌታቸው አምባየ እና ሌሎችም ሽማግሌዎችና ተላላኪዎች የመድረኩ አጀማመር በቀደም እለት ሽማግሌዎቹ ሲናገሩ ከቆዩ በኃላ ብዙም መልስና ክርክር ተደርጎ ነበር ማለት አይቻልም፤ እናማ እላችኃለሁ ተወዝፎ ያደረው ውይይት ቀጠለ፤ ከዚህ ቀጥሎ የትናንት ውሎ በተመለከተ ዋና ዋና የምላቸውንና ሰው ቢሰማቸው ይተቅማሉ ያልኳቸውን ሃሳቦች ብቻ እንዳለ እና እንደወረደ አቀርባላችኋለው ድራማውን ተከታተሉ፤ #ፀጋ አራጌ፡ – ከሰሜን ወሎ ፤ ከነ አለምነው መኮንን መንደር የተገኘ ጀግና፤ አሁን በክልሉ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ነው፡፡ የመጀመሪያውን እድል ወሰደ፤ ሽማግሌዎቹን እንዳልሆኑ አደረጋቸው ፤ የሚበቃውን ተናገረ፤መቸም እውነት ነው የምላችሁ መጫዎቻ ነው ያደረጋቸው፤ ዶ/ር #አንባቸው መኮንን ( የቴወድሮስ ወራሽ፤የገብርየ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አማራን ማጥፋት ማዳከም ለታላቋ ትግራይ ምስረታ የመሰረት ድንጋይ ነው ( መንግስቱ ሙሴ)

አማራን ማጥፋት ማዳከም ለታላቋ ትግራይ ምስረታ የመሰረት ድንጋይ ነው ( መንግስቱ ሙሴ) =========================== በሰሞኑ አማራ ናችሁ ውጡ ተብለው ከራሳቸው ሀገር የተፈናቀሉ ዜጎች በባሕርዳር፣ በፉነተሰላም እና ቡሬ የገጠማቸው ችግር አሁንም እንደቀጠለ ነው። ከሚያሳዝነው አንዱ በሀገራቸው መጠለያ ተከልክለው በጅምላ ወንጀለኞች ተብለው መቆሚያ እና መቀመጫ መከልከል አሳዛኝ ብቻ አይደለም ታሪካዊ እና ሀገራዊ ወንጀልም ጭምር ነው። ይህ ከአገራቸው በታቀደው መሰረት እንዳይኖሩ ተከልክለው መባረራቸው ለአለፉት 27 አመታት ስድት (6) ግዜ መሆኑ ሲሆን። የዘር ማጥፋቱ ህወሓታዊ ወንጀል ተጠናክሮ መቀጠሉን ይህ አዲሡ ፍልሰት አስረጅ ነው። ልክ በዮጎዝላቪያ እንደተካሄደው፣ በናዚ ጀርመኒም እንደተደረገው በኢትዮጵያ ለአለፉት 27 አመታት አማራን ማጽዳት ወንጀል ሳይሆ በተለያዩ ክልሎች የሚተገበር መልካም ዘመቻ መሆኑ እጅግ ያሳዝነናል። Group Percentage Jablawi 26.7% Gumuz 23.4% Amhara 22.2% Oromo 12.8% Shinasha 6.9% Other ethnic groups 8.0% combined ይህ ከመተከል እስከ ጋንቤላ ያለው ሲሆን ከታች የመተከል አውራጃን የህዝብ ቁጥር የምያሳይ ለጥፌአለሁ ይመልከቱ ከላይ UNITED NATIONS DEVELOPMENT PROGRAMME Emergencies Unit for Ethiopia የወጣ ሰንጠረጅ እንደሚያሳየው በጠቅላላ ቤሻንጉል ጉምዝ ተብሎ በተሰየመው ክልል በተለይም በጎጃም ክፍለሀገር እና መተከል አውራጃ የአማራው ቁጥር የላቀ መሆኑን ማየት ይቻላል። ሽናሻ ከአማራው ሲደባለቅ ቁጥሩ ከሁሉም ሊበልጥ እንደሚችል የሚያሳይ የህዝብ ቆጠራ ነው። ይህ በ1996 እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር የወጣ ሰንጠረጅ ሲሆን የትግራይ ጠባብ ቡድን ለታላቋ ትግራይ ምስረታ በጓሮ ካስቀመጣችው የዘር መንደሮቿ አንዱ እና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል። በአዴን የተባለው የህወሓት የአማራ ክልል መዋቅር
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራው መደራጀት ለወያኔ ብቻ ሳይሆን ለሻእቢያም ስጋት ነው ።

ምንሊክ ሳልሳዊ አማራው መደራጀት ፣ መታጠቅ ፣ መልሶ ማጥቃት ፣ ራሱን መከላከል ግዴታው ነው ፤ ሁሉም በብሔሩ ተደራጅቶ ዘራፍ ዘሬን ሲል ዝም ብለናል አማራው ሲደራጅ መነጫነጭ አያዋጣም ፤ ቢደራጅ ማንንም የሚጎዳው ነገር የለም ፤ ስርአቱ ግን የአማራው መደራጀት ነቀርሳ ስለሆነበት በቀጥታና በተዘዋዋሪ እያስጮኸ ሲሆን ሻእቢያ ሳይቀር የአማራ መደራጀት ስጋት እንደሆነበት ሒደቶቹ እያሳዩን ነው ፤ ሌላው በብሔሩ ሲደራጅ አማራው ግን ራሱን ከጥቃት ለመከላከል መደራጀቱ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ነው ። የብሔር አደረጃጀት ወያኔ የቀደደው ቦይ ቢሆንም በራሱ ቦይ ውስጥ ለመቅበር የሚቻለው በሚሔድበት መንገድ ሁሉ ራስን ለመከላከል በመደራጀት ነው ። ስለዚህ የአማራው መደራጀትም ራስን ከመከላከል ውጪ ለኢትዮጵያ ስጋት አይሆንም ። #MinilikSalsawi
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከተፈናቀሉት መካከል የ340 አባውራና እማውራዎች ዝርዝር ( ጌታቸው ሽፈራው )

ከተፈናቀሉት መካከል የ340 አባውራና እማውራዎች ዝርዝር ( ጌታቸው ሽፈራው ) ጥቅምት 16/2010 ዞነ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማሺ ዞን ከበለው ጅጋንፎይ ወረዳ በለው ደዴሳ ቀበሌ በሁለት ግለሰቦች ፀብ አንድ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተወላጅ በመገደሉ ምክንያት የይዞታ ማረጋገጫ እያላቸው “ህገ ወጥ ተብለው ከተባረሩት የአማራ ተወላጆች መካከል የ340 አባውራዎችና ባው እና እማውራዎች መካከል ያስተዳድሩት የነበረው ቤተሰብ ቁጥር ከስር በዝርዝር ቀርቧል። በዝርዝሩ የቀረበው የ340 አባውራዎች እና እማውራዎች ዝርዝር ሲሆን የተፈናቀሉት 527 አባውራና እማውራዎች ናቸው። 1)ቄስ ምንአለ አያሌው (የቤተሰብ ብዛት 8 2)ዋሴ ጥላሁን (የቤተሰብ ብዛት 5 3) ተስፋየ ዋለ (6 4) ምን አለ ተሾመ (የቤተሰብ ብዛት 3) 5) ድረስ ታረቀኝ (የቤተሰብ ብዛት 4) 6) አእምሮ ተገኘ (የቤተሰብ ብዛት 5) 7) አዱኛ ታረቀኝ (የቤተሰብ ብዛት 8……) 8ኛ ) ይልቃል መኮንን (የቤተሰብ ብዛት 6) 9) የስጋ ሽበሽ (የቤተሰብ ብዛት 5) 10) አንተነህ ምስሌ (የቤተሰብ ብዛት 4) 11) ቄስ ጎጀም በየነ (የቤተሰብ ብዛት 7 12) ቄስ ውበቱ እብየው (የቤተሰብ ብዛት 3) 13) ታገለ ፈንቴ (የቤተሰብ ብዛት 3) 14) ገሬ አወቀ (የቤተሰብ ብዛት 3) 15) ጌታነህ ሽፈራው (የቤተሰብ ብዛት 3) 16) ተሾመ ደረሰ (የቤተሰብ ብዛት 5) 17) አለማየሁ ዋለ (የቤተሰብ ብዛት 2) 18) ዘላለም ዋሴ (የቤተሰብ ብዛት 2) 19) እንቻለው አበበ (የቤተሰብ ብዛት 6) 20) በቃል እንቻለው (የቤተሰብ ብዛት 2) 21) ቄስ አዲስ አንተነህ (የቤተሰብ ብዛት 5) 22) አስሜ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተፈናቃይ አባወራዎች ጥፋት አማራ መሆናቸው ብቻ ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

የሕወሓቱ ነውረኛ ድርጅት ብአዴን ላለፉት 27 አመታት አማራ ባገሩ ስደተኛ ሆኖ ሲፈናቀልና ሲገደል ለይምሰል እንኳ መግለጫ አውጥቶ አያውቅም። ነውረኞቹ ብአዴዎች ውክልናቸው የትግራይ እንጂ የአማራ ስላልሆነ የአማራ ጉዳይ አይመለከታቸውም። ባለፈው ጥር ወር ላይ ግን በወልድያ፣ በቆቦና በመርሳ የትግራይ ነፍሰ በላ ወታደሮች አማራ ሲጨፈጭፉና አማራ ራሱን የመከላከያ ርምጃ ሲወስድ ሁሉም የብአዴን ድርጅታዊ መዋቅሮች መግለጫ አወጡ። የብአዴን ቃል አቀባዩ Nigussu Tilahun፣ እንደራሴው ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተብዮው፣ የነውረኛው ብአዴን ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮምቴ አባላት በሙሉ የትግራይ ተወላጆች ተጠቁ ብለው የተጨፈጨፈውን አማራ የሚያወግዝ መግለጫ በሬዲዮ፣ በጋዜጣና በቴሌቭዥን አስተላለፉ። አማራ ሲፈናቀልና ሲሰደድ፣ ሲገደልና ሜዳ ላይ ሲጣል ግን ባለፈው ጥር ወር ለገዳይ የትግራይ ወታደሮች አዝነው መግለጫ ያዥጎደጎዱት እነ ንጉሱ ጥላሁን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተብዮው፣ የነውረኛው ብአዴን ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮምቴ ትንፋሻቸው የለም። እንዴውም በተቃራኒው በክህደት ተሰማርተው ከጎጃም መተከል የተፈናቀሉትን አማሮች የመለስ ዜናዊን አገላለጽ በመጠቀም «ሕገ ሰፋሪዎች» በማድረግ እየወነጀሏቸው ነው። ከታች የታተሙት ፎቶዎች «ሕገ ወጦች» ተብለው የተፈናቀሉት አማሮች የተፈናቀሉበት ምድር «የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ» ደብተሮች ናቸው። እነዚህ ደብተሮች አገርና መንግሥት አልባ ሆነው ባህር ዳር አባይ ማዶ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ተባራሪ አርሷደሮች የተባረሩበት መሬት «የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ» ደብተሮች ናቸው። ይህ በግልጽ የሚያሳየው አባወራዎቹ የተባረሩት አማራ ብቻ በመሆናቸው ብቻ እንደሆነ ነው።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በህገወጥ መንገድ ዱከም ላይ የሚቸበቸበዉ የወሎ ኦፓል

በህገወጥ መንገድ ዱከም ላይ የሚቸበቸበዉ የወሎ ኦፓል By Miky Amhara ———— የወሎ ኦፓል በአለም ቁጥር አንድ ኦፓል ነዉ፡፡ ከዚህ በፊት የአዉስትራሊያዉ ኦፓል ቁጥር አንድ ሁኖ ቢቆይም አሁን ግን ወገል ጠና የሚገኘዉ ኦፓል የአለም ገቢያን ተቆጣጥሮታል፡፡ አማራ ክልል ከሰሊጥ ቀጥሎ ትልቁ ወደ ዉጪ የሚላክ እቃ ነዉ፡፡ ነገር ግን ስለ ኦፓል ኤክስፖርት በዜናም ይሁን በማንኛዉም መንገድ ሰምተን አናዉቅም፡፡ ለምን ሚለዉን መልሱ ወዲህ ነዉ፡፡ በ 2015/16 በአለም የኦፓል ገቢያ ዉስጥ ኢትዮጵያ 28 ሺህ ኪሎ ግራም አቅርባለች፡፡ በ2012/13 14 ሺህ ኪሎ ግራም አቅርባለች፡፡ በ2013 የተቆረጠ እና ፖሊሽድ የሆነ የወሎ ኦፓል 100 ኪሎ ግራሙ 2.5 ሚሊየን ዶላር ተሽጧል፡፡ እንግዲህ 28 ሺህ ኪሎግራሙን በዚህ ስሌት ብናስበዉ በመቶ ሚሊየን ዶላር ወይም በ 10 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር አካባቢ ነዉ፡፡ ይህ ሪፖርት የአለም ባንክና የ አሜሪካ ጂኦሎጅግካል ሰርቬየ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን ለዉጭ አቀረብኩት ያለዉ ኦፓል በ2012/13 4500 ኪሎ ግራም ነዉ፡፡ ሌላዉን 10ሽህ ኪሎግራሙን አላዉቅም ብሏል፡፡ ያ ማለት በህገወጥ መንገድ ነዉ የወጣዉ ማለት ነዉ፡፡ Image may contain: one or more people and outdoor ነገሩ እንዲህ ነዉ የህወሃት ሀገወጥ ነጋዴወች የኦፓል ምርቱን ሰወችን ከአሜሪካ እና ከቻይና ድርስ በማስመጣት እዛዉ ወገል ጠና ላይ ሳይቀር ይሸጡታል፡፡ አዲስ አበባ ላይ ዱከም የቻይኖች የኢንዱስተሪ መንደር ዉስጥ አንዱ ትልቁ ህገወጥ ገቢያ የሚካሄድበት ቦታ ነዉ፡፡ የህወሃት ባለሃብቶችና በላስልጣኖች ከቻይናወች ጋር በመደራደር ይሸጡላቸዋል፡፡ ከዱከም የሚወጣ የኢንዱስተሪ ምርት ጋር ተቀላቅሎ የፋብሪካ ምርት ነዉ ተብሎ ይወጣል፡፡ ባንኮክ ሄዶ
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጀታቸው እየተመዘበረ ሆን ተብሎ እንዲፈርሱ የተደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች እና ጤና ጣቢያዎች በርካቶች ናቸው

ሆን ተብሎ እንዲደኸይ የተፈረደበት የዐማራ ሕዝብ (ምንሊክ ሳልሳዊ) ተማሪው ከፍተኛ የሆነ የማቴሪያልና የትምህርት መርጃ ባሌለበት ሁኔታ ትምህርት የሚያገኘው ሜዳ ላይ ነው። የማቴሪያልና የመድሃኒት አቅርቦት ባሌለበት በሽተኞች ሕክምና የሚያገኙት ሜዳ ላይ ነው ; የውሃና የመብራት አቅራቢ የሆነው የአማራ ክልል ሕዝብ ውሃና መብራት በፍጹም የለውም። በጀታቸው እየተመዘበረ ሆን ተብሎ እንዲፈርሱ የተደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች እና ጤና ጣቢያዎች በርካቶች ናቸው። ይሄ ሕዝብ ስለምን ግብር ይከፍላል? ሰሞኑን ማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሰፊው በአማራ ክልል ሆን ተብሎ በሕወሃት መራሹ የፌዴራሉ መንግስትና በክልሉ መስተዳደር ብ አዴን በተባለው አሽከር ድርጅት በኩል በጃታቸው እየተመዘበረ ንብረታቸው እየተጫነ ሆን ተብሎ እንዲፈርሱና የተማሪዎችን የመማር የመምህራንን የማስተማር ሞራል እየገደሉ ስለሚገኙ መንግስታዊ ተንኮሎችና ግፎችን የሚያመለክቱ ትምህርት ቤቶች በይፋ እየተዘገቡ ምስላቸው እየተለጠፈ ይገኛል። በወጣቶች ስም ብዙ ተነግዷል!”ለወጣቶች ስራ እድል” እየተባለ ቢሊዮን ብር ይመደባል። “ሸድ” እያሉ ይሰራሉ። መስርያ በጀት ግን አይሰጧቸውም። በርካታ ቢሊዮን ብር እንዲሁ ባክኗል።ሸድ ምስራቅ በለሳ ወረዳ የተሰራ በጀት ስለሌለ ሳይሰራበት እየፈረሰ ነው! በአማራ ክልል የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጉዳይ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን ብዙ ሰው የተረዳ ይመስላል። የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት እነዚህን ትምህርት ቤቶች ይሰራቸዋል ተብሎ አይታሰብም። እነዚህ ትምህርት ቤት እንዲህ የሆኑት በበጀት እጥረት አይደለም። ሆን ተብሎም ነው! እነዚህ ትምህርት ቤቶች መሰራት አለባቸው። ትምህርት ቤቶቹ ልክ እንደ ጣና የሕዝብ ርብርብ ይፈልጋሉ! ለዚህም:_ ~ስለ ትምህርትና ትምህርት ቤቶች የመምህራንን ያህል እውቀት ያለው አይኖርም። በተለይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ሕዝብ አገልግሎት ለማይሰጠው መንግስት ለምን ግብር ይከፍላል? መክፈል የለበትም!

የአማራ ሕዝብ አገልግሎት ለማይሰጠው መንግስት ለምን ግብር ይከፍላል? መክፈል የለበትም! ለፌዴራል መንግስቱ ከፍተኛውን ግብር የሚከፍለው የአማራ ክልል ሕዝብ ነው ። የክልሉ ሕዝብ ግብር ቢከፍልም ምንም አይነት አገልግሎት አያገኝም ፤ በደርግ ጊዜ በተሰሩ ትምህርት ቤትች መንገዶች ጤና ጣቢያዎች መንገዶች ድልድዮችና የአገልግሎት መስጫዎች ቢጠቀምም እያረጁ በመፈራረስ ላይ ናቸው። ይህ ሕዝብ ለምን ለመንግስት ግብር ይከፍላል? ምን አገልግሎት አግኝቶ? ~ትምህርት ቤት የለውም። የተሰሩት ፈርሰዋል! ~ጤና ጣቢያ የለውም ~መንገድ የለውም ~ውሃ፣ መብራት… ……የለም አገልግሎት ለማይሰጠው መንግስት ለምን ግብር ይከፍላል? መክፈል የለበትም! #MinilikSalsawi #Ethiopia #Amhara
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዘራችን እየተጠቃን ነው… ይህን ቀንበር መሸከም አንችልም – መምህር ጌታ አስራደ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲው መምህር ጌታ አስራዳ ዛሬ ሚያዝያ 16/2010 ዓም ለ19ኛ ወንጀል ችሎት የተናገረው ማዕከላዊ ሲደበድበን የነበረው በሀሰት ምስክር ነው። እኛ የተከሰስነው በሀሰት ነው። መንግስት ሊገለብጡ ነው ተብለን ተከሰን አንዳችንም መሳርያ የለንም። እኛ እየተጠቃን ያለነው በዘራችን ነው። እውነት ፍትህ የምትሰጡ ቢሆን ማን እየዘረፈ እና እየመዘበረ እንዳለ ይታወቃል። ማን እየሰረቀ እንዳለ፣ በዚህ ሀገር ወንጀለኛው ማን እንደሆነ ይታወቃል። ቤተሰባችን ተበትኗል። ተሰቃይተናል። አካላችን ተጎድቷል። ይህ ወንድማችን እጁ ተጎድቷል። ይህኛው ወንድማችን አንድ እጅ የለውም። (የተቆረጠውን እጁን እያነሳ)። ልብስ ማጠብ እንኳ ስለማይችል ወደ እኛ ዞን እንዲመጣ ለምነን ነው የመጣ ው። ልብስ እንኳ የምናጥብለት እኛ ነን። ማዕከላዊ ተገርፈናል። ፍትህ የማትሰጡን ከሆነ ልታሰናብቱን ይገባል። ይህን ሁሉ ቀንበር መሸከም አቅቶናል። በዘራችን ነው እየተጠቃን ያለነው። ፍትሕ እስካላገኘን ድረስ መጮሃችን እንቀጥላለን።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕዝብ ፍሬ ያፈራው የባህርዳሩ ጉባዬ ፤ ለኢሕአዴጉ ጠሚ ዶክተር አብይ ላይ ትልቅ ብድርና እዳ ያሸከመ የሕዝብ መድረክ ነበር (ምንሊክ ሳልሳዊ)

(ምንሊክ ሳልሳዊ) – የሕዝብ ፍሬ ያፈራው የባህርዳሩ ጉባዬ ፤ ለኢሕአዴጉ ጠሚ ዶክተር አብይ ላይ ትልቅ ብድርና እዳ ያሸከመ የሕዝብ መድረክ ነበር። የኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር በባህር ዳር ባደረገው ሕዝባዊ ኮንፈረንስ ላይ ሕወሓት እንዳሰበው ሳይሆን የሕዝብ ብሶት የተደመጠበት የወያኔ ገበና የተጋለጠበት ፍሬ ያፈራ ስብሰባ ነበር። ሕዝቡ መተንፈስ ያለበትን ሁሉ ተንፍሶ ወደ ተግባር እንዲገባ አስረግጦ ተናግሯል።ትላንትና ጠሚው ጎንደር ላይ የጎንደር ሕዝብ እያለ ባደረገው ንግ ግር የተቆጩት አቶ ገዱ በዛሬው የባህርዳር ስብሰባ የ አማራ ሕዝብ ብሎ እንዲናገር በጎ ምክራቸውን መለገሳቸውን የስብሰባው ምንጮች ይጠቁማሉ። ባለፉት አመታት የላሸቀና ወኔው የሞተ ሱሰኛ ወጣትን ለማፍራት ሲተጋ የነበረው ሕወሓት የተኮላሸበት ወላጆች የነቁ ወጣቶች የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች እስኪበቃቸው የተናገሩበት ታላቅ ሕዝባዊ ስኬት ነበር። የክልሉ የተፈጥሮ ሃብት እየተበዘበዘ ለሌላ ክልል ማልሚያ መዋሉ ፣ የወልቃይት ጉዳይ ፣ ከኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ግብር ከፋይ አማራ ክልል ሆኖ አንድም ኢንዱስትሪና የላማት ማእከል ሲልም የወጣቶች መዝናኛ ያልተሰራለት መሆኑን ሕዝቡ በሰፊው ተናግሯል። ፖለቲካ በሃይማኖት ውስጥ ገብቶ እንደሚበጠብጥ የባለስልጣኖች እጅ ረዥም መሆኑ በፊትለፊትና በተዘዋዋሪ በመናገር ለዶክተር አብይ ላይ ትልቅ ብድርና እዳ ያሸከመ የሕዝብ መድረክ ነበር። በቁጭትና በእልህ ትላልቅ ቁምነገሮች የተነሱበት የባህርዳሩ የሕዝብ መድረክ የኢሕአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያስደነገጠ ነበር። የዶክተር አቢይ ሁኔታ ለመገመት አስቸጋሪና ከባድ እየሆነ መጥቷል፤ የሕወሓት ሰዎች ያልተገኙበት ይህ መድረክ በግልጽነት የተካሔደ ሲሆን ሕወሃት ሲነዛው የነበረው ባህርዳር ላይ ካድሬ ብቻ ነው ስብሰባው ላይ የሚገባው ፕሮፓጋንዳ ከመክሸፉም
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከጎንደር: ወልዲያ: ቆቦ: መርሳ፣ ከኦሮሚያ ክልል ሸሽተው የመጡ ትግሬዎች በራያ-አላማጣ ለማስፈር ገበሬው መሬቱን እየተነጠቀ ነው

ስጋት ያንዣበበት የራያ ማንነት ጉዳይ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ አውቀው ይሁን ስተው የልማት ጥያቄ ነው ማለታቸው ጋብ ብሎ የቆየው የማንነት ጥያቄና እንቅስቃሴ በተለየ መልክ እንዲቀጥል ምክንያት ሆነዋል። ዘለግ ላለ ጊዜ የዘለቀው የወልቃይት ጉዳይ በስፋት እውቅና ማገኝቱ የበለጠ ትኩረትም አግኝቷል። ነገር ግን ብዙም ትኩረት ያላገኘችው በአማራ ክልል በሰሜን ምስራቅ የምትገኘው ራያ-አላማጣ ተመሳሳይ አደጋ ላይ ከወደቀች ሰነባብታለች። አሁን ደግሞ ገበሬው ከመሬቱ እየተነቀለ በምትኩ ከሌላ አካባቢ ለመጡ ሰዎች በልማት ስም እየታደለ ነው። “ራያን በትግራይ ክልል የማካተት እቅድ አካል ነው” ያለኝ አንድ ወዳጄ “በግድ ትግሬ ናችሁ እያሉን ነው” በማለት ነበር ወቅታዊ ሁኔታውን በምሬት የገለፀው። “ከጎንደር: ወልዲያ: ቆቦ: መርሳ፣ ከኦሮሚያ ክልል ሸሽተው የመጡ ትግሬዎች በራያ-አላማጣ ለማስፈር ገበሬው መሬቱን እየተነጠቀ ነው ያለው። አላማቸው መሬት መንጠቅ ብቻ ሳይሆን የማንነት ጥያቄ እንዳይነሳ በመፍራት የህዝቡ Demograpy መቀየርም ጭምር ነው። ልክ እንደ ወልቃይት ማለት ነው። እውነቴን ነው እምልህ እንደ ራያ ህዝብ ሚፈሩት የለም። ብዙ አክትቭስቶች ብዙ ይፅፉሉ ዋናው ወያኔ ጥያቄ እንዲነሳም ማይፈልጉት የራያ ጉዳይ ነው፣ ማንሳት ያለባቸውም ይሄው ነው።” ይህ አካሄድ በእውነቱ ማንንም አይጠቅምም – ‘ሳይቃጠል በቅጠል’ እንዲሉ እንዲህ ያሉ ጉዳዮች መፍትሄ ካላገኙ መዘዛቸው መጠነ ሰፊ እንደሚሆን ለመናገር ነብይነት ከስፈላጊ አይመስለኝም። ከህዝብ ፍላጎት ውጪም በብልጣ-ብልጥነት የሚደረግ ማንኛውም የድንበር ማካለልም ይሁን የክልል አወቃቀር በህግም ይሁን በሞራል ፍፁም ተቀባይነት የለውም። ጠቅላይ ምኒስትር አብይም እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን ከማድበስበስ እና እውቅና
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ትግሬ ያልወደደው ወንበሩ አይረጋለትም አይነት አካሄድ ይዘው የአማራውን አይን መውጋት መዘዝ አለው !

መስከረም አበራ ትናንት አቶ አታላይ ዛፌ በቪኦኤ ቀርበው በርቱዕ አንደበት የወልቃይትን ጉዳይ አስቀምጠዋል፨ ነገሩ ከአብይ አቅም በላይ እንደሆነ እግዜርም ሴጣንም ያውቃሉ፨ ሆኖም ዶ/ር አብይ ከአቅማቸው በላይ የሆነን ነገር በማድበስበስ ባራድኛ ከልለው የተቀመጡበትን ወንበር የሚያዙበት ማስመሰላቸውን ማቆም አለባቸው፨ ጠሚው የተቀመጡበት ወንበር የእውነት ነው ካሉ፣ አፋቸው የሚያወራው ልባቸው ያሰበውን ከሆነ፣ በምላሳቸው ላይ ጠበንጃ የያዘ ዘበኛ ከሌለ ደግሞ የወልቃይትን ጉዳይ ማንሳት ያለባቸው ወልቃይት የእኔ ነው የሚሉትን ሁለቱንም አካላት ሰብስበው መሆን አለበት፨ እንጅ ትግሬ ያልወደደው ወንበሩ አይረጋለትም አይነት አካሄድ ይዘው የአማራውን አይን መውጋት መዘዝ አለው! በአማራው ላይ መሳለቅ ከመለስ ጋር ተቀብሯል! ለሰው ሁለተኛ እድል በመስጠት አምናለሁ በግሌ፤ ለሁለተኛው እንዲህ ባለ መውጫ በሌለው ስህተት ውስጥ ከመቦራጨቃቸው በፊት አሰብ ማድረጉ አይከፋም፨ ካልሆነም አለቆቻቸው በሚዘውሩት አጀንዳ ላይ ፖርላማ ቀርተው ቅዝምዝምን ባሳለፉበት ስታይል ዝም ብሎ ማሳለፍ ይሻላል – ከንግግር ብዛት ስህተት አይጠፋም እንዲል መፅሃፍ !
Tagged with: , , , ,
Posted in Ethiopian News

የኢሕአዴግ ጠቅላይ ምኒስትር ወልቃይትና አርማጮህን አስመልክቶ የተናገሩትን የወልቃይት ኮሚቴ አመራር ተቃወሙ

አቶ አታላይ ዛፌ ጥያቄያቸው የማንነት እንጂ የልማት እንዳልሆነ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የወልቃይት ኮሚቴ አመራር አባላት አቶ አታላይ ዛፌ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ መቀሌ ተጉዘው ከሕዝብ ጋራ ባደረጉት ውይይት የወልቃይትን የአርማጮ ጥያቄ የልማት መሆኑን በመናገራቸው እጅግ ማዘናቸውንም ተንግረዋል። ከአቶ አታላይ ዛፌ ጋራ የተደረገውን ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ
Tagged with: , ,
Posted in Ethiopian News

የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት ላይ የትግራይ ክልል አዲስ ክስ መሰረተ ።

ማንነታችን በማሰር በማሸማቀቅ ወደሃላ አይቀለበስ አሁንም አማራ ነን። እኛ ተከሳሾች ክሳችን በፌደራል ዓ/ህግ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን በከተማ ሁመራ ለ05/08/2010 ዓ/ም አንድንቀርብ የክሱ ቻርጀር ለ7ተከሳሾች የደረሰን ሲሆን የተከሰስንበት ምክንያት የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ በመጠየቃችን ለዚህ ክስ ተዳርናል ይሁን እንጂ እኛ በወልቃይት ወረዳ በከተማው አድረመጥ የተወለድን ስንሆን በተወለድንበት ቦታ ህገ መንግስታዊ መሠረት የደረገ የማንነት ጥያቄ ብንጠይቅም የጠየቅነው ጥያቄ በህጋዊ መንገድ መሆኑን መንግሥት እስከ ሚመልስልን በአከባቢያችን/በወረዳችን የፈጠርነው ህውከት ያወደምነው ንብረት የማንም ይሁን የማንም የፖለቲካ ጥገኝነት/ደጋፊዎች እንዳልሆነ ባለው ስርአት ተጠቅመን ህገ መንግሥታችን ተገን በማድረግ ጥያቅያችን በሰላማዊ ምንገድ እየተከታተልን መሆናችንን የክልሉ መንግስት ይሁን የዞን እስከ ወረዳ ያሉ መሥተዳድሮችና እስከ ቀበሌ ያሉ በደንብ እያወቁናል ይህ መሆኑን እያወቁ የሃሰት ክስ በመመስረት መብታችንን ለማፈን ህገ መንግሥታዊ ጥያቅያችንን ለማደናቀፍ መሆኑን መላው ህዝባችን እንታውቁልን ለመግለፅ እንወዳለን ፡፡ ለማንነታችን ዛሬም ይሁ ነገም አንደራደርም፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook