Blog Archives

የተፈናቃይ አባወራዎች ጥፋት አማራ መሆናቸው ብቻ ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

የሕወሓቱ ነውረኛ ድርጅት ብአዴን ላለፉት 27 አመታት አማራ ባገሩ ስደተኛ ሆኖ ሲፈናቀልና ሲገደል ለይምሰል እንኳ መግለጫ አውጥቶ አያውቅም። ነውረኞቹ ብአዴዎች ውክልናቸው የትግራይ እንጂ የአማራ ስላልሆነ የአማራ ጉዳይ አይመለከታቸውም። ባለፈው ጥር ወር ላይ ግን በወልድያ፣ በቆቦና በመርሳ የትግራይ ነፍሰ በላ ወታደሮች አማራ ሲጨፈጭፉና አማራ ራሱን የመከላከያ ርምጃ ሲወስድ ሁሉም የብአዴን ድርጅታዊ መዋቅሮች መግለጫ አወጡ። የብአዴን ቃል አቀባዩ Nigussu Tilahun፣ እንደራሴው ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተብዮው፣ የነውረኛው ብአዴን ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮምቴ አባላት በሙሉ የትግራይ ተወላጆች ተጠቁ ብለው የተጨፈጨፈውን አማራ የሚያወግዝ መግለጫ በሬዲዮ፣ በጋዜጣና በቴሌቭዥን አስተላለፉ። አማራ ሲፈናቀልና ሲሰደድ፣ ሲገደልና ሜዳ ላይ ሲጣል ግን ባለፈው ጥር ወር ለገዳይ የትግራይ ወታደሮች አዝነው መግለጫ ያዥጎደጎዱት እነ ንጉሱ ጥላሁን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተብዮው፣ የነውረኛው ብአዴን ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮምቴ ትንፋሻቸው የለም። እንዴውም በተቃራኒው በክህደት ተሰማርተው ከጎጃም መተከል የተፈናቀሉትን አማሮች የመለስ ዜናዊን አገላለጽ በመጠቀም «ሕገ ሰፋሪዎች» በማድረግ እየወነጀሏቸው ነው። ከታች የታተሙት ፎቶዎች «ሕገ ወጦች» ተብለው የተፈናቀሉት አማሮች የተፈናቀሉበት ምድር «የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ» ደብተሮች ናቸው። እነዚህ ደብተሮች አገርና መንግሥት አልባ ሆነው ባህር ዳር አባይ ማዶ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ተባራሪ አርሷደሮች የተባረሩበት መሬት «የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ» ደብተሮች ናቸው። ይህ በግልጽ የሚያሳየው አባወራዎቹ የተባረሩት አማራ ብቻ በመሆናቸው ብቻ እንደሆነ ነው።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News