Blog Archives

ሙስሊም የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናት 60ሺህ ብር ድጋፍ ሰጡ፡፡

ሙስሊም የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናት 60ሺህ ብር ድጋፍ ሰጡ፡፡ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ለአረፋ በዓል ቅድመ ዝግጅት የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ላሳዩት አብሮነት አመስግነዋል፡፡ በጎንደር ከተማ ዛሬ በተዘጋጀው የአብሮነት ፕሮግራም የሃይማኖቶቹ ተከታዮች ታድመዋል፡፡ለአረፋ በዓል ቅድመ ዝግጅት የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ላሳዩት አብሮነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ኃይማኖታዊ አንድነትን ለማደፍረስ የሚጥሩ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለተቃጠሉ አብያተ ክርስትያናት ሙስሊም የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች 60ሺህ ብር አበርክተዋል፡፡ ነሀሴ 19/2010(አብመድ)
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሱማሌ ክልል በተጠናና በታቀደ መልኩ ቤተክርስቲያንን በጅምላ የማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞብናል ሲሉ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተናገሩ።

ሶማሌ ክልል ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክ/ያን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ መልኩ በተጠና:በታቀደ መልኩ ክርስቲያንን እንዲሁም ቤተ ክ/ያንን በጅምላ የማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞብናል :: ከዚህ ወዲያ ይህን ሰይጣናዊ ስራ በየትኛውም ክልል ቢፈፀምብን የማንታገስ :ዝም የማንል መሆኑ ይታወቅልን:: ለጊዚያዊ መፍትሔ ይሆን ዘንድ ቤተ ክ/ያኗ የ8 ሚልዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋለች :: ሁሉም በአካባቢው ያለችውን ቤተ ክ/ያን በንቃት እንዲጠብቅ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ :: ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደገሃቡር ከተማ የተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ የክልሉን ነዋሪዎችና ህዝበ ሙስሊሙን አይወክልም ።

በደገሃቡር ከተማ የተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ የክልሉን ነዋሪዎችና ህዝበ ሙስሊሙን አይወክልም – ምሁራን $bp("Brid_44889_1", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-1783692171700630.mp4", name: "በደገሃቡር ከተማ የተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ የክልሉን ነዋሪዎችና ህዝበ ሙስሊሙን አይወክልም ።", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180817_232840.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጅግጅጋና በሌሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ አከባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እየሰፈነ ነው ።

በጅግጅጋና በሌሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ አከባቢዎች በተቀናጀ ጥረት ወደ አንጻራዊ ሠላም እየተመለሰ መሆኑ ተገለፀ፡፡ $bp("Brid_44013_2", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-292470164862771.mp4", name: "በጅግጅጋና በሌሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ አከባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እየሰፈነ ነው ።", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180815_163857.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News