Blog Archives

የጅጅጋው ግርግር አስገራሚ ታሪክ ፡ በዮሴፍ ለገሰ ( ዶ/ር)

ወዳጅን ከአደጋ ለማስመለጥ ዘዴኛ መሆንን ይጠይቃል ። የጅጅጋው ግርግር አስገራሚ ታሪክ ፡ በዮሴፍ ለገሰ ( ዶ/ር)   በሰኔ ወር 2010 የእድሜ ባለጸጋ የሆኑ ከሀብሮ አውራጃ እስከ ጎዴ ልዩ ራስ ገዝ ድረስ በርካታ ሽልማቶች ከተበረከተላቸው አንጋፋ የተፈጥሮ ሀብት ባለሞያ ጋር ተገናኝተን እያወራን ነበር። የምስራቁን ኢትዮጵያ ከተሞች በደረጃ እንዲያስቀምጡልኝ ብጠይቃቸው ሁሉም ምርጥ ናቸው አሉኝ። ስነዘንዛቸው፥ ካስገደድከኝ፦ 1ኛ ጅጅጋ ፥2ኛ ድሬዳዋ ፥ 3ኛ ሀረር ናቸው አሉኝ። ጅግጅጋዬ እኔም እንደኛ እንደሆነች ነው የማውቀው። ሐምሌ 28/2010 ቅዳሜ ቀን ታድያ ዝናዋን የሚያጎድፍ፥ ደረጃዋን የማይመጥን፥ አንገት የሚያስደፋ ክስተት አጋጠማት። በእለቱ ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ገላዬን ለቅለቅ ብዬ፥ ቁርስ ፍለጋ ወጣሁ። ጎረስ-ጎረስ አደረግኲና ቡና ጠጥቼ ወደቤት ተመለስኩ። ጋደም ብዬ Facebook ከፈትኩ። ጓደኛዬ Tamiru L Kitata “Jigjiga town as of today” ብሎ የለጠፈውን አየው። በቀጥታ “ታሜ ምንድንው የለጠፍከው?” “ይሄ ውሸት ነው፤ እኔ አሁን ከውጪ መግባቴ ነው፤ ሰላም ነው” አልኩት። መሳርያ የተጠመደበት መኪና ምስል ልኮልኝ “ይሄስ?” አለኝ። ምናልባት ለበዓል ቀን የተነሳ እንደሚሆን ነገርኩት። በመቀጠል Nebil Selahdin “ባክህ ጅግጅጋ ምን እየሆነ ነው?” የሚል ጥያቄ አስከተለብኝ። ምንም ችግር እንደሌለ፥ሰላም እንደሆነ ነገርኩት። መደጋገሙ ግን አሳሰበኝ። ሁለቱንም ትክክለኛ መልስ እንድሰጣችሁ ጠብቁኝ ብያቸው መጀመርያ Facebook በመቀጠል ደግሞ ቤቴን ዘግቼ ወጣሁ። ጥቂት እርምጃዎች እንደተራመድኲ ጎረቤቴ ፈጠን ፈጠን እያለች ስትመጣ ተገናኘን። “የት ነው የምትሄደው ተመለስ ተመለስ፥ ከተማ ችግር አለ” አለችኝ። ጎረቤታሞች ቁጥራችን ከሁለት ወደ ሦስት ከፍ አለ። ጠርዝ ላይ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጅግጅጋና በሌሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ አከባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እየሰፈነ ነው ።

በጅግጅጋና በሌሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ አከባቢዎች በተቀናጀ ጥረት ወደ አንጻራዊ ሠላም እየተመለሰ መሆኑ ተገለፀ፡፡ $bp("Brid_44013_1", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-292470164862771.mp4", name: "በጅግጅጋና በሌሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ አከባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እየሰፈነ ነው ።", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/IMG_20180815_163857.jpg"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሶማሌ ክልል ጥቅማቸው የቀርባቸው የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች በተለይም ካቢኔው በህዝቡ ላይ ሽብር እየነዙ ነው።

ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አሳሳቢ መረጃ (ዮናታን ተስፋዬ) በአሁኑ ሰዓት መከላከያ አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍን ከሀገር ሽማግሌዎች እና ተቆርቋሪ ዜጓች ጋር እየሰራ ቢሆንም – ጥቅማቸው የቀርባቸው የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች በተለይም ካቢኔው በህዝቡ ላይ (መጤ ወይም ደገኛ በተባለው ህዝብ ላይ) ሽብር እየነዙ ነው። በሶማሊኛ ቋንቋ የሚተላለፈው ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እስካሁን በአብዲ ኢሌ ካቢኔ እና ዘመዶች ቁጥጥር ውስጥ በመሆኑ በህዝብ ላይ ከፍተኛ የሽብር ፕሮፖጋንዳ ከፍተው እያወኩ ነው። ከዚሀም የተነሳ ከ10 ሺህ በላይ ‘ደገኞች’ ክልሉን ለቀው በመውጣት ላይ ሲሆኑ – በአንዳንድ ቦታ በቴሌቪዥን ጣቢያው በሚተላለፈው ፕሮፖጋንዳ የተነሳ የተደራጀ ማፈናቀል እየተካሄደ ነው። የሀገር ሽማግሌዎች የፌደራል መንግስት ሚዲያውን በቁጥጥሩ ስር አውሎ ኃላፊነት በሚሰማው ሰው እንዲሰራ ጥሪ እያቀረቡ ነው።
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጂጂጋ ውስጥ የእስልምና የሃይማኖት አባቶችና ዑጋዞች ክርስቲያኖቹን ስብሰባ ጠርተው እያለቀሱ ለተፈጠረው ነገር ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

ጂጂጋ ውስጥ የእስልምና የሃይማኖት አባቶችና ዑጋዞች ክርስቲያኖቹን ስብሰባ ጠርተው እያለቀሱ ለተፈጠረው ነገር ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ በተደረገው ነገር ማዘናቸውን፡፤ ከእምነታቸውና ከባሕላቸው የወጣ ነገር መከናወኑን፡፤ የተቃጠሉትን አብረው እንደሚሠሩ፤ የተጎዱትን አብረው እንደሚረዱ ቃል ገብተዋል፡፡ የተዘረፉትን የሚያስመልስ ኮሚቴ ተመሥርቷል፡፡ ዛሬ ከሰዓትም ርዳታ ማከፋፈል ጀምረዋል፡፡ የርዳታ እህሎች ነገ ጂጂጋ ውስጥ ሊከፋፈሉ የሚችሉበት ዕድል ተፈጥሯል፡፡ አሁን በሌሎች ከተሞች ያለው ችግር ወደመፍታት ደግሞ እናምራ፡፡
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጅጅጋ የተፈጠረው ዘረፋና ስርአት አልበኝነት የሰብአዊ ቀውስ ከማድረሱ በፊት መንግስትና የእርዳታ ድርጅቶች እንዲደርሱ ተጠየቀ

በጅግጅጋ ከተማ ያለው ወደለየለት ሰብዓዊ ቀውስ (Humanitarian Crisis) እንዳይሸጋገር መንግስት ምንም ዓይነት እርምጃ እየወሰደ አይደለም! (ስዩም ተሾመ) ሃብትና ንብረታቸው የተዘረፈባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች አሁን ላይ እንኳን የሚበሉት ምግብና የሚጠጡት ውሃ የመመገቢያ ሳህንና ውሃ መጠጪያ ኩባያ የላቸውም፡፡ ዘረፋው የተፈፀመው ለመዝረፍ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምንም ቀሪ ሃብትና ንብረት እንዳይኖራቸው ለማድረግ ሆን ተብሎ ታቅዶ ነው፡፡ የዘረፉትን ዕቃ ወስደው፣ የቀረውን ሰብረው ወይም አቃጥለው ነው የሄዱት፡፡ እነዚህ ሰዎች ምንም ነገር የላቸውም!! መንግስት ሌሎች ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ምንም ሲያደርጉ አይስተዋል፡፡ የአንድ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪ ስልክ ደውሎ የነገረኝን እስኪ አድምጡት!! ይሄ ፖለቲካ አይደለም፣ ሰብዓዊነት ነው!! ከፍ ካለም የዜግነት ግዴታ ነው፡፡ $bp("Brid_41537_2", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Facebook-1725012790901367.mp4", name: "በጅጅጋ የተፈጠረው ዘረፋና ስርአት አልበኝነት የሰብአዊ ቀውስ ከማድረሱ በፊት መንግስትና የእርዳታ ድርጅቶች እንዲደርሱ ተጠየቀ", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Screenshot_2018-08-05-23-12-41.png"}, "width":"550","height":"309"});
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጅግጅጋ “አብዲ ኢሌ ይመለስልን እያላችሁ ሰልፍ ውጡ” የቤት ለቤት ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው።

“አብዲ ኢሌ ይመለስልን እያላችሁ ሰልፍ ውጡ” በአሁኑ ሰዓት በጅግጅጋ የቤት ለቤት ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው። ሰው ሰልፍ እንዲወጣ እና አብዲ ኢሌ እንዲመለስ እንዲጠይቅ በድምፅማጉያ ሳይቀር ቅስቀሳው በለሊት ተጀምሯል። የቤት ለቤት ቅስቀሳውን የሚያካሂዱት በቀዳሚነት የልዩ ፖሊስ አዛዧች ሚስቶችና ልጆች፤ የነሱ ስር ያሉ ሻለቃዎች ሚስቶች እና ልጆ ናቸው። ከነዚህ ጋርም ቀጥታ በአብዲ ኢሌ ትዕዛዝ በየወሩ 10,000 የሚከፈላቸው (በየመንደሩ ለአብዲ የሚሰልሉ እና ወሬ ያሰራጩ የነበሩ) በርካታ ሴቶች የቤት ለቤት ቅስቀሳውን እያካሄዱ ነው። በተጨማሪም በቪ8 እና ሌሎች መኪኖች የሚዞሩ የአብዲ ኢሌ ካቢኔዎች ከነ ቤተሰቦቻቸው በቅስበሳው እየተሳተፉ ሲሆን ሲኖሩ – ትልልቅ ስፒከር በጫኑ መኪናዎችም “ሰልፍ ውጡ – አብዲ እንዲመለስ ጠይቁ” በሚል ጥሪ እየተደረገ ነው። ሰልፉን የሚያስተባብሩት ደግሞ ከልዩ ፖሊስ አዛዥ የአብዲ ኢሌ አጓት ልጅ እና ከቀሩት ካቢኔዎቹ ጋር በመሆን ሂጎ የተባሉት ቡድኖች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ለበርካቶቹም ለኪስ እየተባለ አስር አስር ሺህ ብር እንደታሰረ እንደሚሰጣቸው የጠቆመኝ የሀገር ሽማግሌ ሰው ገንዘቡ ምንጭ ከየት ነው በማለት ላነሳሁለት ጥያቄ “የሶማሌ ክልል በጀት መች ውሃ እና መንገድ ዘርግቶ ያውቃል” ሲል የምሬት ሳቅ እየሳቀ የገንዘቡ ምንጭ ለሶማሌ ክልል ዓመታዊ በጀት እንደሆነ አስረድቶኛል። በሌላ መልካም ዜና – ብዙዎችን(ደገኛ የተባሉ ኦሮሞ አማራና ጉራጌ) ከለላ የሆነው ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩ ሰዎች በዛው በቤተክርስቲያኑ ግድም የሚገኘው መስጊድ “ጥቃት ሊደርስበት ነው” የሚል መረጃ ስለደረሳቸው እነዚሁ “ደገኛ” ክርስቲያኖች ተሰብስበው ለመስጊዱ ጥበቃ በማድረግ ላይ ናቸው። Yonatan tesfaye #JusticeForSomali
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከጅግጅጋ 120 ኪሎሜትር ላይ እስከ 8000 የሚደርስ የታጠቀ ጦር ሰፍሯል

16 ርጅመንት ልዩ ፖሊስ በኦበሌ ሰፍሯል-ለጦርነት ይሆን? ከአብዲ ኢሌ ብቻ ትዕዛዝ የሚቀበሉ 16 ርጅመንት የልዩ ፖሊስ ጦር በኦበሌ ደገሃቡር ዞን መስፈሩን ምንጮች ለረጆ አሳውቀዋል፡፡ አንድ ርጅመንት ከ400-500 ወታደሮችን ይይዛል፡፡ ይህም ማለት እስከ 8000 የሚደርስ የታጠቀ ጦር መሆኑ ነው፡፡ ኦበሌ ለጅግጅጋ 120ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኝ ቦታ ነች፡፡ አብዲ ኢሌ ይህንን ታማኝ ጦሩን ለመደራደሪያነት ይጠቀም ይሆን? መከላከያ ሠራዊት ይህን ጦር ለመደምሰስ ያመነታ ይሆን? የሚናየው ጉዳይ ይሆናል! RAJO ነዳጁን ተቆጣጥረውታል። የአብዲ ኢሌ ልዩ ሀይል ወታደሮች በቅርቡ በሶማሌ ክልል የተመረቀውን ድፍድፍ ነዳጅ ማምረቻ አካባቢ እንደያዙ ናቸው። (በፊትም ይጠብቁት ነበር) አሁን አብዲ ኢሌ ተያዘ መባሉን ተከትሎ እናፈነዳዋለን እያሉ በማስፈራራት ላይ ናቸው። ነዳጁን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መደራደሪያ አድርገውታል። ነዳጅ የማውጣት ስራ ላይ የነበሩ ቻይናዎችም ቦታውን ጥለው ወጥተዋል። ወያኔዎችና ሚዲያዎቻቸው የሃሰት ዜና እያሰራጩ ነው ። ከፖስታ አገልግሎት አንድ ሚሊዮን ብር የተቋረጠበት አውራምባታይምሱ ዳዊት ከበደ ፌክ ዜና በማሰራጨት ሽብር እየነዛ ይገኛል።አብዲ ኢሌ ወደ ሥልጣን ተመልሷል የሚል ሀሠተኛ ወሬ ተሠራጭቶ፣ ደጋፊዎቹና ተቃዋሚዎቹ በመኪና ሠልፍ ወጥተው ሡማሌዎቹ እየጨፈሩ ይገኛል። ስለዚህ ከመከላከያ ጋር ግጭት እንዳይፈጠር አሣውቅልን! በዚህ መሃል ልዩ ፖሊሦች ገብተው ተኩሥ ይከፍታሉ የሚል ሥጋት አለ። ህዝቡ ዳግም ጭንቀት ላይ ወድቋል!ከውጭ ከፍተኛ የሆነ ጩኸት ይሠማል። ሀበሾች ወደ ቤት ግቡ የሚል ትዕዛዝ ከመከላከያ ወገኖቻችን ተነግሮናል! የሶማሌ ተወላጆችም ሌላውም ጭምር አብዲ ኢሌ አልተልለሰም። ራሳችሁን ከግጭት ጠብቁ! #MinilikSalsawi
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጅጅጋ ተረጋግታለች ፤ የአብዲ ኢሌ ያደራጃቸው ሀይሎች HEEGO የተባሉት ለሊቱን ከከተማ ወጥተዋል።

የአብዲ ኢሌ ያደራጃቸው ሀይሎች HEEGO የተባሉት ለሊቱን ከከተማ ወጥተዋል። ዛሬ ከተማው ተረጋግቷል። ህዝቡ ወደ ቤቱ ገብቷል። . ህዝቡ መኪናና ባጃጅ የመሳሰሉ የተዘረፉ ንብረቶችን መልሶ ለማግኘት ጥረት እያደረገ ነው። . ዘረፋ ሲፈጽሙ የነበሩት የአብዲ ኢሌ ያደራጃቸው ሀይሎች በተለይም ራሳቸውን HEEGO ብለው የሚገልጹት ለሊቱን በመኪኖች ተጭነው ከከተማ ወጥተዋል። ከተማው ውስጥ የተሸሸጉም አሉ። (እየፈለግናቸው ነው ተብያለሁ) . ልዩ ሀይል የተባለው ታጣቂ አሁን እየሰራ አይደለም። . መከላከያ ሰራዊት ከክልሉ ፖሊስ ጋር እየሰራ ነው። የክልሉ ፖሊስ አሁን በከፍተኛ መንቀጥቀጥ ለመስራት እየሞከረ ነው። ባለፉት ቀናት ህዝቡን ከጥቃት መታደግ ባለመቻሉ የህዝብ ጥቃት ይደርስብኛል ብሎ ፈርቷል። ጅጅጋ መከላከያ እና የፌዴራል ፖሊስ ከገባበት ከትላንት ከሰዓት በሗላ ጀምሮ አንፃራዊ ሰላምን አግኝታለች:- -ለሊቱንና አሁን አካባቢ የተወሰነ ቦታዎች ላይ የተኩስ ድምፅ ከመሰማቱ በቀር ሰላማዊ ነበር: -በመደብሮች መዘጋት ምክንያት አሁንም ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት ከተማዋ ላይ አለ: ሚካኤል ቤተ ክ/ያን ያሉ ህፃናትና አዛውንት በቂ ምግብ ማግኘት አልቻሉም: -አሁንም የክልሉ ፖሊስ እና መከላከያ ተናበው መስራት ባለመቻላቸው እዚህም እዚያም ትንንሽ ጥፋቶች እየተከሰቱ ነው: -ጥቃት የደረሰባቸው ወጣቶች በመሰባሰብና መኪና ላይ ስፒከር በማድረግ ቀሪው ህዝብ እንዲረጋጋና ወደ መደበኛው ስራው እንዲመለስ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው : -የቤተ ክ/ያናት ቃጠሎ ለረጅም ጊዜ ታስቦበት በጥናት የተደረገ ዘመቻ እንደሆነ :ከተማዋንም ወደለየለት ቀውስ ለመክተት እንደታሰበ እንደነበር :አንዳንድ መረጃዎች እየተገኙ ነው: ኢንተርኔት ሲለቀቅ መረጃውን እንደሚያጋሩን ነግረውኛል: -አሁን ደግሞ እኛ በተራችን እንገድላለን እንዘርፋለን የሚሉ ውስን
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብዲ ኢሌ ከስልጣኑ ወርዷል ፤ አህመድ አብዲ የተባለው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊው ተክቶታል ።

አህመድ አብዲ የተባለው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊው ተክቶታል ። መከላከያ ጂጂጋን ተቆጣጥሯል ጉልበቱን ባልታጠቁ ንጽሃን ዜጎች ላይ ሲያሳይ የነበረው ቦቅቧቃው የአብዲ ልዮ ሀይል ከሀገር መከላከያ ስራዊት ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ ስላቃተው ከተማዋን ለቆ ፈርጥጧል ፤ ሽሽቶ ካንፓ ገብቷል የሚሉም አሉ ። ነፍሰ በላው አብዲ ኢሌ አሁን በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የቅርብ ክትትል ውስጥ ይገኛል ፤ አብዲ ኢሌን አህመድ አብዲ የተባለው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊው ተክቶታል ። አሁን ማምሻውን ደግሞ ክልሉን በተመለከተ የመንግስት ኮምኒኬሽን ሚኒስትሩ መግለጫ ሰጥተዋል ምኒስትሩ በመግለጫቸው ፤ የፀጥታ ሃይሉ ወደ ክልሉ ገብቶ ሰላም የማስከበር ስራውን እንዲሰራ መታዘዙን አስታውቀዋል ። በህዝብ ተወካዮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ላይ ከፍተኛ ወከባ በክልሉ መንግስት ጥቂት አመራሮች ሲደርስ እንደነበር የገለጹት ምኒስትሩ የክልሉ ፕሬዘዳንት “ስልጣን ልቀቅ ተብያለሁ፤ ስልጣኔን ከምለቅ ብሞት ይሻለኛል “ክልሉን አስገነጥላለሁ” በማለት ከፍተኛ ውዥንብር ሲፈፀም ቆይቷል ብለዋል። በደረሰው ጥፋት እጃቸው ያለበት ሰዎች ተጠያቂ እንደሚሆኑ እና የደረሰው ጥፋት ልክም ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ሀላፊው ገልጸዋል ። አብዲ ኢሌ ወንጀለኛ ነው ለፍርድ ይቀርብ !!!!
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጅጅጋ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በጅጅጋ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከጅጅጋው ግድያ ያመለጡ የመጀመሪያ ዙር ስደተኞች ሶማሌላንድ ገቡ – (ቪድዮ)

ከጅጅጋው ግድያ ያመለጡ የመጀመሪያ ዙር ስደተኞች ሶማሌላንድ ገቡ ። ስደተኞቹ ዋጃሌ የሚባል የሱማሌላንድ ግዛት ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የሱማሌላንድ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውም ስደተኛ እንዳይነካ መመሪያ አስተላልፈዋል ምንሊክ ሳልሳዊ ቪዲዮ እነሆ $bp("Brid_40575_3", {"id":"12272", ,"stats":{"wps":1}, "video": {src: "https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/SirSomaliland_1026176321234194432.mp4", name: "ከጅጅጋው ግድያ ያመለጡ የመጀመሪያ ዙር ስደተኞች ሶማሌላንድ ገቡ – (ቪድዮ)", image:"https://mereja.com/amharic/v2/wp-content/uploads/2018/08/Screenshot_2018-08-05-23-12-41.png"}, "width":"550","height":"309"}); First wave of refugees escaping Jigjiga conflict arrived in Wajaale, Somaliland this afternoon. Earlier today, H.E President Muse Biihi called on Somalilanders to welcome & protect Ethiopians in SL. Somaliland hopes the Jigjiga crisis will be solved through peaceful dialogue. #MinilikSalsawi
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጅግጅጋ ልጆች ኢቲቪ በር ላይ ተቃውሞ አድርገዋል

ኢቲቪ የጅግጅጋውን ጉዳይ እየዘገበ አይደለም። የጅግጅጋ ልጆች ኢቲቪ በር ላይ ተቃውሞ አድርገዋል ተብሏል!  
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው ከአብዲ ኢሌ የሠለጠኑ ገዳይ ወታደሮችና መቀሌ ከመሸጉ የተባረሩ ጄኔራሎች ጋር ነው፡፡

ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው ከአብዲ ኢሌ የሠለጠኑ ገዳይ ወታደሮች ጋር ብቻ አይደለም፡፡ እነሱን በምክርና አብረው ከነሱ ጋር የተሰለፉ 5 የህወኃት ኮርኔሎችና ጄኔራል ኳርተርና ሌሎች ከመከላከያ የተሰናበቱ ጄኔራሎች በምክር ከመቀሌ ሆነው እየመሩ ይገኛሉ፡፡ አሁን ደግሞ ኦብነግና አልሸባብ በጦርነቱ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ አብዲ ኢሌ ዛሬ የሀገር ሽማግሌዎችን በመጥራት እገነጠላለሁ የሚለው ወሬ በጠላቶቹ እንደተወራበትና እሱም ስልጣኑን እንደሚያስረክብ እነሱም ለሰላም መትጋት እንዳለባቸው ገልጿል፡፡ አያይዞም የመከላከያ ሠራዊት ወደከተማው እንዲገቡ መፍቀዱን ተናግሯል፡፡ ነገር ግን ይሄ ሰውዬ አሁን የተናገረውን ከሰዓት በኃላ ስለሚቀይረው ያለውን ለማመን አይቻልም፡፡ ጠላቶቹም ማን እንደሆኑ ሳይናገር በደፈናው አልፎታል፡፡ ዛሬ ረፋድ ላይ በጅግጅጋ የተቃጠለውን ቤተክርስትያን ሲጎበኝ ምዕመናኑ ሌባ ሌባ ሲሉት ግዜ ድንብርብሩ ወጥቶ አካባቢውን ለቆ በመጣበት ፍጥነት ተመልሶ ሄዷል፡፡ በጅግጅጋ ገራድ ውልዋል ኤርፖርት የመከላከያ ሠራዊት ቁጥር ወደ ሦስት ሺህ ደርሷል፡፡ በሶማሊያ ግዛት በለድዌይኔ የነበረው መከላከያ ሠራዊት ወደ አገር ቤት በመመለስ ድንበር አካባቢ ጥበቃ ማድረግ ጀምሯል፡፡ የሱማሌ ክልል ሽማግሌዎችና ምሁራን ከመከላከያ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን እየገለፁ ነው፡፡ አብዲ ኢሌ አልተያዘም! ውዥንብሩ የመጣው መከላከያ ሠራዊታችን ሕዝቡ እንዳይጨረስ ከመፈለግ አኳያ በማፈግፈግ ወደ ጦር ሠፈሩ በመመለሱ ነው፡፡ አብዲ ኢሌ ይህን በመጠቀም ለመደበቅ በቅቷል፡፡ የነበረበትን ቦታ ስላልታወቀ ሰዎች የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች ያወጡ ነበር፡፡ ረጆ ተይዟል የሚለውን መልዕክት ያስተላለፈችው የአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች ተስፋ ቆርጠው ወደጥፋት እንዳይገቡ ለመከላከል ነበር፡፡ አሁን የእውነታው ሰዓት ስለተቃረበ ሁሉም እውነቱን እንድያውቁ ረጆ ትሻለች፡፡ በነገራችን ላይ ሌላው ኢትዮጵያዊ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ድርድሩ አልተሳካም ፤ አብዲ ኢሌ የአልሸባብን እርዳታ የተማፀነ ሲሆን የፌዴራል ሠራዊት በተጠንቀቅ እንዲቆም ታዟል፡፡

የአብዲ ኢሌ የመጨረሻ ሰዓታት! በምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን የሚመራው ቡድን ከአብዲ ኢሌ ጋር ያደረገው በሰላም እጁን እንዲሰጥ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ የፌዴራል ሠራዊት በተጠንቀቅ እንዲቆም ታዟል፡፡ችግር የሆነው እስከ ሀረር ያለው መንገድ የአብዲ ኢሌ ልዩ ፖሊሶች በትላልቅ ድንጋይ ዘግተው እስከ ካራማራ ድረስ መሽገው ይገኛሉ፡፡ ከነሱም ጋር ጥቅት የህወኃት ኮርኔሎች ለውግያው እያዘጋጇቸው ይገኛሉ፡፡ አብዲ ኢሌ ከባድ መሳሪያ ለማግኘት ከአልሸባብ ጋር በመነጋገር ላይ ነው፡፡ ለአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ራሱን ለመሸጥ ጥሉ ከክርስትያኗ ኢትዮጵያ ጋር እንደሆነ ለማሳየት ዛሬ አምስተኛውን ቤተክርስትያን እንድቃጠል አድርጓል፡፡ዛሬ የተቃጠለው ቤተክርስትያን በሼህ ኑር ኢሴ አካባቢ የሚገኘው የጊዮርግስ ቤተክርስትያን ነው፡፡ ትላንትም ያስገደላቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖች ይህንኑ ሀሳቡን ለማጠናከር የተጠቀመበት ዘዴ ነው፡፡አብዲ ኢሌ ይህን ያደረገበት ዋንኛ ምክንያት የፀቡን አቅጣጫ በመቀየር ከአልሸባብ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ለማግኘት እንደሆነ ምንጮች ለረጆ አሳውቀዋል፡፡ ከዝሁ ጋር ተያይዞ አስመራ የሰለጠኑት የኦብነግ (ONLF) ወታደሮች ወደክልሉ እንዲገቡና ከሱ ልዩ ፖሊሶች ጋር በመቀናጀት እንዲዋጉ ከኦብነግ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን እነዝሁ ምንጮች ለረጆ አረጋግጠዋል፡፡ አብዲ ኢሌ የመርሲን ማፊያ ተብለው የሚታወቁትን ቤተሰቦቹን ዛሬ ከጅግጅጋ ከተማ ወደ መርሲን ከተማ አስወጥቷል፡፡ይህም የሚያሳየው እንደቀዳፊ እስከመጨረሻው ሰዓት ለመዋጋት ማቀዱንና ከዝህ በፊት ቃል እንደገባው ጅግጅጋን መቋድሾ ለማድረግ ማሰቡን ነው፡፡ እንደደረሰን መረጃ ከሆነ መከላከያ ሠራዊታችን በሄሊኮፕተር የከተማውን ዳርቻ ተቆጣጥረዋል፡፡ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በማንኛውም ደቂቃ ጦርነቱ ሊጀምር ይችላል፡፡ ድል ለመከላከያ ሠራዊታችን! ድል ለሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ! ድል ለሱማሌ ሕዝብ! ከጅግጅጋ የሞቱት ካህናት ፍታት ተደርጎላቸው
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሶማሊ ክልል የተሠራው ዘግናኝና አረመኔያዊ ሥራ ነው፡፡

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሶማሊ ክልል የተሠራው ዘግናኝና አረመኔያዊ ሥራ ነው፡፡ ሰውን በቁሙ ማቃጠል፡፡ ሴቶችን መድፈር፡፡ መኪና ይዞ በየቤቱ እየዞሩ የሰው ንብረት መዝረፍ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል፡፡ ለመሆኑ መንግሥት የለም? አንድ ክልልስ ሥልጣኑ የሰው ዘርን እስከማጥፋት ድረስ ነው? ይህን መሰሉ ግፍ ዚያድባሬ ኢትዮጵያን የወረረ ጊዜ ነበር በምሥራቁ ክፍል የተፈጸመው፡፡ ዚያድባሬ አለ ማለት ነው? የክልሉ ፕሬዚዳንት የልቡን ከሠራ በኀላ ትናንት ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መጥቶ እንመካከር ሲል ነበር፡፡ ሰው ከተቃጠለ፡ ንብረት ከተዘረፈ፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠለ በኀላ የምን ምከከር ነው? አሁን በዚያ ክልል ስላለው ሕዝብ እንደ አዲስ ማሰብ አለብን፡፡ ሌላ መፍትሔም ማምጣት አለብን፡፡ ከተቃጠለው ሕዝብ ይልቅ የአቃጣዩ አያያዝ በሚያስጨንቃቸው ሰዎች ሥር መኖር ከባድ ነው፡፡ በሰሞኑ ግጭት የተጎዱ አብያተ ክርስቲያናትና ካህናት 1. የዋርዴር ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠል ቄስ ያሬድ ኅቡዕ ተገደሉ፣ 2. ቀብሪ ደኃር ደብረ መድኃኒት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቃጥላለች፡፡ 3. ደጋሐቡር መካነ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ቄስ ኪዳነ ማርያም ንብረቱ ተገድለዋል፡፡ 4. በጅጅጋ የምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል እና የደብረ ሰዋስው ገዳም የተቃጠሉ ሲሆን አባ ገብረ ማርያም አስፋው፣ መ/ር አብርሃም ጽጋቡ ተገድለው አስከሬናቸው ተቃጥሏል፡፡
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጅጅጋ ሰላም ደፍርሷል። ግድያውና ዘረፋው ቀጥሏል።

በጂጂጋ ቤተክርስቲያን የይድረሱልን ደውል እያሰማች ነው ! አሁንም በኢትዮጵያዊያን ኦሮሞ፣ አማራ እና ጉራጌ ተወላጆቹ ላይ የተለየ ጥቃት እየተፈፀመ ነው ፤ ቁጥሩ በውል ተለይቶ ባይታወቅም ውድ የሆነው የሰው ልጅ ህይወት እየተቀጠፈ ነው ፤ ንብረት በማውደሙ ዘረፋ ቀጥሏል ፣ ቤተክርስቲያን እየተቃጠሉ ምዕመናንንም ሰማዕትነት እየከፈሉ ነው ፤ቤተ ክርስትያን አሁንም የይድረሱልን ደውል እያሰማች ነው ፤ የተወሰኑ የክልሉ ፖሊሶችና ልዩ ኃይል አባላት የመከላከያ ሰራዊት አገራዊ ኃላፊነቱን እንዳይወጣ ክልከላ እያደረጉ ነው ፣መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ ያልሰጠ እንደሆነ ውጤቱ እጅግ የከፋ ነው ፤ ይህ መረጃ ከቦታው በስልክ ያገኙሁት ነው። ከጅግጅጋ ዋርደር ገብርኤል ቤተ ክ/ያን ሙሉ ለሙሉ የተቃጠለና አብረው 2 ቄሶች እንዲሁም 1ዲያቆን ህይወት ያለፈበት: ቀብሪድሃር ማርያም ቤተ ክ/ያን የተቃጠለ: ደገሃቡር ጊዮርጊስ ቤተ ክ/ያን የተቃጠለ: እንዲሁም 1ቄስ ህይወት አልፏል ! አሁን የክልሉ ፖሊስ (ልዩ ሃይል)ብዙ ሺህ ሰው ወደተጠለለበት ሚካኤል ቤተ ክ/ያን በሃይል ሰብረው ለመግባት እየሞከሩ ነው ህዝቡ አትገቡም እያለ ነው ….አሁንም ኡኡታ ጅግጅጋ ላይ እየተሰማ ነው::አሁን የአይን እማኞች እንዳረጋገጡት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያንም ከነ ቤተልሔሟ ተቃጥላለች (2ኛው ቤተ ክ/ያን መሆኑ ነው) የሞቱት ካህናት :- ከአርሴማ መሪጌታ አብርሃም ጥጋቡ: እና አንድ ተጠማቂ: ከኪዳነ ምህረት መሪጌታ ጌራወርቅ(መፅሃፍ መምህር):አባ ገ/ማርያም አስፋው (መነኩሴ መንበር ጠባቂ) እንዲሁም ስሙ ለጊዜው ያልታወቀ አንድ ካህን: ሁሉንም ገድለው አቃጥለዋቸዋል !! አብዲ ኢሌ አልተያዘም አልታሰረምም የሚወራው ወሬ ውሸት ነው: አሁን ሚካኤል ቤተ ክ/ያን የተጠለሉትን ብዙ ሺህ ሰዎች ሊያናግር መጥቶ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከአብዲ ኢሌ ጋር የሚደረገውን ድርድር ተከትሎ መንግስት መግለጫ እንደሚሰጥ ተሰምቷል።

ከአብዲ ኢሌ ጋር የሚደረገውን ድርድር ተከትሎ መንግስት መግለጫ እንደሚሰጥ ተሰምቷል። ………. አብዲ ኢሌ ገዳይና ዘራፊ ነው የሚለው ኦብነግ በአብዲ ኢሌ ላይ በፌዴራሉ መንግስት የተወሰደውን እርምጃ አወገዘ። የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ብሎ ራሱን የሚጠራው ተቃዋሚ ቡድን አብዲ ኢሌን በመደገፍ ባወጣው መግለቻ የክልሉ ሕዝቦች አብዲ ኢሌንና ክልላቸውን ከወራሪዎች ምመጠበቅና መከላከል አለባቸው ብሏል። ሕገመንግስቱን አልቀበልም ብሉ የትጥቅ ትግል ላይ የሆነው ኦብነግ የጅጅጋው ድርጊት ሕገመንግስቱን የጣሰ ነው ሲል መናገሩ ትዝብት ላይ ጥሎታል ኦብነግ በተለያዩ ጊዜያት ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት የፌዴራሉን መንግስትና የክልሉን መንግስት በማብጠልጠልና በመክሰስ ይታወቃል። በተለይ አብዲ ኢሌ እብድ መሪ ነው ኢሰብዓዊ ነው ወዘተ የሚሉ ስሞችን በመስጠት ለዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ሲከሰው ከርሟል። አባሎቼን አፈነብኝ ሲልም ሲያማርር ከርሟል። ዛሬ የተከሰተውን የጅጅጋ ችግር ተገን አድርጎ ድርጅቱ እንዳለው መሪውንና ክልሉን ሕዝቡ እንዲጠብቅ ጥሪውን አስተላልፏል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ እርምጃዎችን እንዲያስቆሙ የጠየቀው ኦብነግ ሕዝቡ መብቱን እንዲያስከብርና ጉዳዩን ካለማንም ጣልቃ ገብነት እንዲፈታ አሳስቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴራል መንግስቱ ከአብዲ ኢሌ ጋር ስምምነት ላይ እንዲደርስ ሽምግልና መጀመሩንና ድርድር ተደርጎ መግባባት እንዲፈጠር የሕወሃት ሰዎችና የሶማሌላንድ ባለስልጣናት እየተሯሯጡ መሆኑ ተነግሯል። አቶ አብዲ ኢሌን በተመለከተ በሚዲያ ምንም አይነት ጉዳይ እንዳይነሳና በጂጂጋ ሁከት ከመነሳቱ ውጪ ለላ ዜና እንዳይቀርብ የተደረገ ሲሆን ከአብዲ ኢሌ ጋር የሚደረገውን ድርድር ተከትሎ መንግስት መግለጫ እንደሚሰጥ ተሰምቷል። #MinilikSalsawi
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር የዋለው በአንቀፅ 39 መሰረት የሶማሌ ክልልን ለመገንጠል ስብሰባ በመጥራቱ እንደሆነ ታወቀ!!!

መከላከያ ገብቶ ከተማውን ተቆጣጥሮታል። መከላከያ በኦራል እየዞረ ከተማውን እያረጋጋ ነው። የሚዘርፉትን ዘርፈዋል ሄደዋል። እንቅስቃሴ የለም። ሕዝብ በየቤቱ ተቀምጧል በሶማሌ ክልል ጎዴ ቀብሪደሀር፣ ደገሀቡር፣ የመሳሰሉ ከተሞች ውስጥ ውጥረት ነግሷል፡፡ ከሶማሌ ውጪ ባሉ የኢትዮጵያ ብሔሮች ላይም ጥቃት እየተሰነዘረ ነው፡፡ Abdi Illey will be placed under federal custody “in order to prevent further bloodshed in the region. (addis Standard) አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር የዋለው በአንቀፅ 39 መሰረት የሶማሌ ክልልን ለመገንጠል ስብሰባ በመጥራቱ እንደሆነ ታወቀ!!! የሱማሌ ክልል ፕረዜዳንት አብዲ ኢሌ በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር መሆኑ እርግጥ ነው። በትላንትናው ዕለት አብዲ ኢሌ ከፌደራሉ መንግስት እና የፀጥታና ደህንነት ኃላፊዎች ጋር በክልሉ እየተባባሰ ስላለው የፀጥታ ችግር ለመነጋገር ስብሰባ ተጠርቶ ነበር። አብዲ ኢሌ ግን ከፌደራሉ መንግስት የቀረበለትን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው የክልሉን ፓርላማ እና ካቢኔ ስብሰባ ይጠራል። የዚህ ስብሰባ ዋና ዓላማ የሕገ-መንግስቱን አንቀፅ 39 በመጠቀም የሱማሌ ክልልን ለመገንጠል ውሳኔ ለማሳለፍ እንደሆነ ታውቋል። በዚህ መሰረት ዛሬ ጠዋት አብዲ ኢሌ ከክልሉን ምክር ቤት እና ካቢኔ አባላት ጋር ስብሰባ ላይ እንዳለ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ቁጥጥር ስር ውሏል። ከሰዓት በኋላ በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርቦ የክልሉ ሕዝብ እንዲረጋጋ ጥሪ አቅርቧል። ማታ ላይ ደግሞ ስለ ጉዳዩ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ይሆናል። ሆኖም ግን አብዲ ኢሌ አንቀፅ 39 መሰረት የሲማሌ ክልልን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ጥረት ማድረጉ የተረጋገጠ ሀቅ ነው። ፍፁም ባልተጠበቀ መልኩ ሀገር ለመገንጠል ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት ግን
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጅጅጋ ሰላሟ እየተመለሰ እየተረጋጋች ነው።

የሶማሌው አብዲ ኢሌ በክልሉ ቲቪ ቀርበው መግለጫ ሰጡ፡፡ በመግለጫቸው ክልሉ ሰላም ስለሆነ ህብረተሰቡ እንዲረጋጋ በሶማሊኛ ቋንቋ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ያሉበት ሁኔታ ግን በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆኑን ያሳብቃል፡፡ መደበኛ ፕሮቶኮል ሳይጠብቁ ዛፍ ስር ቆመው ነው መልዕክቱን ያስተላለፉት፡፡ ምናልባትም ክልሉን በመወከል የሰጡት የመጨረሻ መግለጫቸው ሊሆን ይችላል፡፡
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓቱ ጄነራል አብረሃ አብዲ ኢሌ ያደራጃቸውን ልዩ ሀይል ለተደራጀ ዐመፅ እየመራ ይገኛል።

ሜጀር ጄነራል አብረሃ ወ/ማሪያም አብዲ ኢሌ ያደራጃቸውን ልዩ ፖሊስ/ሀይል ለተደራጀ ዐመፅ እየመራ ይገኛል በጅግጅጋ እና ግጭቱ በተቀሰቀሰባቸው የሶማሌ ክልል ከተሞች ዘረፋ፣ ግድያ… ቤተ ክርስቲያን፣ ባንክ እና ሱቆችን ማቃጠል እየፈፀሙ የሚገኙት እና የሚመሩት ልዩ ሀይሎች/ፖሊሶች ኳርተር የተባለው ሜ/ጄ አብርሃ እንደሚታዘዙ ታውቋል። ከዚሁ ጄነራል ጋርም ኮለኔል ገብሬ ጨምሮ አምስት የሚደርሱ ኮለኔሎች ልዩ ፖሊስ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ጦርነት እንዲገጥም እየገፋፉ እና እያመቻቹ ይገኛሉ። ሜ/ጄ አብርሃ ቴክኒካል እና ሎጀስቲክ ድጋፍ እያደረገ የሚመራው የአብዲ ኢሌ ልዩ ሀይል መከላከያ ላይ ተኩስ ከፍቷል ከከተማው ዳር በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ውስጥ ከአንድ ሬጅመንት የሚያንስ ወታደር በልዩ ሀይሉ ተከቦ ተኩስ ተከፍቶበት አካባቢውን እንዲለቅ እየተገደደ ነው። ልዩ ሀይሉ ከጄነራሉ በሚያገኘው ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቀ ነው። ጅግጅጋ አሁንም በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ጭስ ጭጋግ እንደተሸፈነች ሲሆን – ከከተማው ዳር የሚሰማው የተኩስ ድምፅ ነዋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተ (ከድምፃቸው ሳይቀር) መገንዘብ ችያለሁ።  
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር ውሏል

ጅግጅጋ ሜዳው ላይ አብዲ ለታገተ፤ ምነው መቀሌ ላይ ጩኸት በረከተ?! በFCR የጭነት መኪና አመፅ ሲቀሰቀሱ የነበሩ ከ80 የማያንሱ ሂጎ እና ልዩ ፖሊሶች ሞቱ። በከፍተኛ ፍጥነት እየበረረ በፕሬዘዳንት አብዲ ኢሌ ቢሮ ሲደርስ የተገለበጠው የጭነት መኪና የጫናቸውን ከ80 ያላነሱ የልዩ ፖሊስ አባላት እና ሂጎ የሚባሉ የአብዲ ኢሌ ቡድኖች ሙሉ በሙሉ በአደጋው ህይወታቸው አልፏል። አደጋው ከደረሰበት ስፍራ በርካታ አምቡላንሶች ሰዎቹን ለማትረፍ ቢረባረቡም፤ ወደ ካራማራ የተወሰዱት ሰዎች ሁሉም ህይወታቸው እንዳለፈ ታውቋል። በአሁኑ ሰዓት በጅግጅጋ ኔትወርክ የተቋረጠ ሲሆን ወደከተማው የገባው መከላከያ ሰራዊት እየተታኮሰ ከከተማዋ በመውጣት ላይ ይገኛል። ከሀረር በኩል የተላከ ሌላ የመከላከያ ሀይል ደግሞ በልዩ ፖሊስ ከግስጋሴው ተገትቶ ወደ ከተማው መግባት አልቻለም። የአብዲ ኢሌ ርዥራዥ ባለስልጣናት ደጋፊዎቻቸው እንዲነሱ ባደረጉት ጥሪ ሄጎዎችና ሲቪል ልብስ ያደረጉ ልዩ ፖሊሶች የመንግስት መኪኖችን በመጠቀም በጅግጅጋ ያሉትን አብዛኛውን ባንኮችንና መደብሮችን ዘርፈዋል፡፡ ከተዘረፉት መደብሮች የሚካኤል ቤተክርስትያን ይገኝበታል፡፡ የኪዳነ-ምህረት ቤተክርስትያንም ቃጠሎ ደርሶበታል፡፡ አንድ ሱማሌ ሰው ለምን ቤተክርስትያን ታቃጥላላችሁ ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን ድርጊት አጥብቀው ኮንነዋል ብሎ ሲናገር እሱም መደብደቡ ታውቋል፡፡ብሄር-ተኮር ጥቃቶችም እንድሁም የመደፈር ዕጣ የደረሰባቸው ወገኖች እንዳሉም እየተገለፀ ነው፡፡ በየመንገዱ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ አጠቃላይ ‘ደገኛ’ የተባሉ የክልሉ ነዋሪዎች እየተገደሉ ነው። ንብረታቸው እየተዘረፈ በጭካኔ እየተደበደቡ ነው። “አብይ ነዳጁን ከሶማሌ ነጥቆ ለኦሮሞ ሊያደርገው ነው – ነዳጁን ኢትዮጵያ እንጂ ሶማሌ አይጠቀምበትም” የሚል ቅስቀሳ በትልልቅ ስፒከሮች በአይሱዙ በተጫኑ ሂጎ የተባሉ ቡድኖች እና ልዩ ፖሊስ አማካኝነት ከፍተኛ ቅስቀሳ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብዲ ኢሌን ለመያዝ የመከላከያ ሰራዊት ጅጅጋን ተቆጣጠረ።

ጅጅጋ በመከላከያ ሰራዊት እጅ ገብታለች አብዲ ኢሌን ከበው አይዞህ ያሉት ወታደራዊ ጄኔራሎች ከበው እያናገሩት ነው ። በጅጅጋ የአብዲ ኢሌ ቤተመንግስት ፣ የጅጅጋ ቴሌቪዥን ጣቢያና ቴሌኮሙኒኬሽን በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውሏል ። በጅጅጋ የወጋገንና የኦሮሚያ ኢንተ. ባንክ ተዘርፈዋል፤ የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን እንደተቃጠለች ከቦታው የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ በጅጅጋ አመፅ እና ውጥረት አብዲ ኢሌ የመጨረሻ ካርዱን ስቧል ሲቪል የለበሱ “ልዩ ፖሊሶች” * ነዳጃችንን ይዘን ከኢትዮጵያ እንገነጠላለን * አብይ የአማራ እና ኦሮሞ የበላይነት ሊያመጣብን ነው * የአማራና የኦሮሞ ቤት አቃጥሉ * ኦሮ የሚል ታርጋ ያለበት መኪና አቃጥሉ … የመሳሰሉትን መፈክር በማሰማት በመቀስቀስ ያረፈዱ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት መከላከያ ወደ ከተማው ቢገባም የአብዲ ኢሌ ‘ልዩ ፖሊሶች’ ዩኒፎርማቸውን ለብሰውና ሙሉ ትጥቅ ታጥቀው ቤቶችንና መኪናዎችን በማቃጠል ላይ ናቸው። የሶማሌ ክልል ህዝብ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን – የንግድም ሆነ መደበኛ የመንግስት ስራዎች ቆመዋል። አብዲ ኢሌ በሔሪኮፕተር አዲስ አበባ አምጥተው ከአዲሱ የማእከላዊ እስር ቤት እንዲቀላቅሉት ፀሎታችን ነው። በቀጣይነት መቀሌ የመሸጉት አሸባሪዎችና ዘራፊዎች ታፍሰው ይመጣሉ። #MinilikSalsawi
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News