በሱማሌ ክልል በተጠናና በታቀደ መልኩ ቤተክርስቲያንን በጅምላ የማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞብናል ሲሉ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ተናገሩ።

ሶማሌ ክልል ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክ/ያን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ መልኩ በተጠና:በታቀደ መልኩ ክርስቲያንን እንዲሁም ቤተ ክ/ያንን በጅምላ የማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞብናል ::

ከዚህ ወዲያ ይህን ሰይጣናዊ ስራ በየትኛውም ክልል ቢፈፀምብን የማንታገስ :ዝም የማንል መሆኑ ይታወቅልን:: ለጊዚያዊ መፍትሔ ይሆን ዘንድ ቤተ ክ/ያኗ የ8 ሚልዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋለች ::
ሁሉም በአካባቢው ያለችውን ቤተ ክ/ያን በንቃት እንዲጠብቅ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ::

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ