የሱዳን ሰራዊት ከትህነግ/ህወሓት ጋር በመተባበር በአማራ ገበሬዎች ላይ በፈፀመው ወረራ የቆሰሉት ገበሬዎች ገንዳውሃ ከተማ መተማ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ገብተዋል።
ሆኖም ቤተሰቦቻቸው ቁስለኞችን ገብተው መጠየቅ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል።
የእናቶች ዋይታ! በመተማ ሆስፒታል!
የደርግን መውደቅ ካስደስታቸው መከካል እናቶች ይቀድማሉ። “ዘመቻ የለም፣ ገፈፋ የለም፣ ጦርነት የለም” ይሉ ነበር። ልጆቻቸው ወደ ጦር ሜዳ በግድ ዝመቱ የተባሉባቸው እናቶች። ይህን ካሉ ግን ቆይተዋል።
ዛሬም ቢሆን ጦርነት አለ። ዛሬም ከደርግ የባሰ ጭራቅ ሀይል አለ። ዳር ድንበሩን ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ። ዳር ደንበሩን አሳልፎ ከሰጠው ጠላት ጋር ሆኖ ንፁሃንን በከባድ መሳርያ የሚጨርስ ጭራቅ ሀይል አለ። ከደርግ የባሰ!
ይህ የምታዩት ፎቶ ዛሬ የተነሳ ነው። ገንዳውሃ ከተማ መተማ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው። ትህነግ የሱዳን ጦርን መርቶ ቤተሰባቸውን በከባድ መሳርያ ያስመታባቸው እናት ሲያለቅሱ የሚያሳይ ነው። አንድ አባት ሊያፅናኑዋቸው ሲጥሩ ያሳያል።
ትህነግ የከፈለው የሱዳን ጦር ደንበር ጥሶ ሲመጣ የኢትዮጵያ የሚጠብቅ ጦር አልነበረም። የሱዳኑንም፣ የኢትዮጵያ ነው የሚባለውንም የሚመሩት ትህነጎች ናቸው። እናቶች ደግሞ ዋይታቸውን ለማንም ማሰማት አይችሉም። ወራሪውም አስወራሪውም ጠላት አድርጎ ፈርጇቸዋል። ደርግ እንኳን ወደቀ ያሉ እናቶች ከደርግ የባሰ ጭራቅ ጥሎባቸዋል። ዛሬም ዋይታቸው ቀጥሏል!
የሱዳን ጦር በአማራ ገበሬዎች ላይ የከፈተው ጦርነት የጀመረው ሰኔ 25/2010 ዓም ነው የሚባለው ስህተት ነው። ሰሚ ጆሮ አጥቶ ነው እንጅ ወረራው በአዲስ መልክ ወረራው ከጀመረ ከ25 ቀን በላይ ሆኖታል። ማስተካከያ የሚያስፈልገው ባለፉት ሶስት ሳምንታትም በርካታ ገበሬዎች ስለተገደሉ፣ ስለቆሰሉና ስለጠፉ ነው! ይህ ሁሉ