በመተማ ደለሎ ቁጥር አንድ ላይ ትናንት ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ•ም የተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ አምስት የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት እና ለመንግስት የሁለት ቀን የጊዜ ገደብ በመስጠት መጠናቀቁ ተሰማ
ከመተማ፣ከገንዳ ውሀ፣መሽሀ፣ላስታ፣ሽመለ ጋራ፣ከምዕራብ አርማጭሆ አብርሀ ጅራ እና ከሌሎችም አካባቢዎች ጥሪ የተደረገለት በአጠቃላይ እስከ 2000 የሚደርስ ህዝብ በስብሰባው ላይ መሳተፉ ተነግሯል።
በተለይ ሰሞኑን ለዳር ድንበራችን መከበር የተሰውትን አቶ ገብሬ አውለውንና ላቀው ሰሎሞንን በከባድ የተኩስ እሩምታ፣በጀግና ፍከራና ቀረርቶ ታጅቦ የቀብር ስነ ስርዓታቸውን የፈፀመው የመተማና ገንዳ ውሀ ህዝብ በከፍተኛ ቁጥር፣ሞራልና ተነሳሽነት በህዝባዊ ስብሰባው ላይ ተሳትፏል ተብሏል።
ስብሰባው በህዝብ የተመራ ቢሆንም የምዕራብ ጎንደር ዞን የአስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ጌትነት፣የዞኑ የድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊና መሬታችንን አነ አባይ ፀሀየ አሳልፈው ሲሰጡ በወቅቱ የመተማ አስተዳደርና ፀጥታ ሀላፊ የነበረውና በአሁኑ ስዓት የዞኑ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ ሆኖ የተሾመው አቶ አብነት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው በሽብር ወንጀል ታስረው የተፈቱት እነ ሀይሌ ማሞና ነጋ ባንቲሁን በስብሰባው ላይ መገኘታቸው ታውቋል።
የመከላከያ ሀላፊው ኮሎኔል ሻምበል በስፍረው ባይገኝም በስብሰባው ላይ ተደውሎለት ሀሳብ እንዲሰጥበት መደረጉ ተገልጧል።
የስብሰባው አጀንዳም የታጠቁ የሱዳን ወታደሮችን የትንኮሳ ጥቃት በመመከት ብሎም ዳር ድንበራችንን ቢያንስ እስከ ጓንግ ለማስከበር በጋንታ እና በቲም የመደራጀት አስፈላጊነትን የተመለከተ ነበር ተብሏል።
በስብሰባው ላይም በደለሎ ቁጥር 4 ከሱዳን ወታደሮች በቅርብ ርቀት ጎድቦ ያለው መከላከያ ሰራዊት ዳር ድንበሩን የማስከበር ታሪካዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ተገቢ የሆነ ትዕዛዝ እንዲሰጠውና ጓንግ ወዲህ ማዶ ሰፍሮ ያለን የሱዳን