የእናቶች ዋይታ! በመተማ ሆስፒታል! ቤተሰቦቻቸው ቁስለኞችን ገብተው መጠየቅ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል።

የሱዳን ሰራዊት ከትህነግ/ህወሓት ጋር በመተባበር በአማራ ገበሬዎች ላይ በፈፀመው ወረራ የቆሰሉት ገበሬዎች ገንዳውሃ ከተማ መተማ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ገብተዋል።

ሆኖም ቤተሰቦቻቸው ቁስለኞችን ገብተው መጠየቅ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል።

የእናቶች ዋይታ! በመተማ ሆስፒታል!

የደርግን መውደቅ ካስደስታቸው መከካል እናቶች ይቀድማሉ። “ዘመቻ የለም፣ ገፈፋ የለም፣ ጦርነት የለም” ይሉ ነበር። ልጆቻቸው ወደ ጦር ሜዳ በግድ ዝመቱ የተባሉባቸው እናቶች። ይህን ካሉ ግን ቆይተዋል።

ዛሬም ቢሆን ጦርነት አለ። ዛሬም ከደርግ የባሰ ጭራቅ ሀይል አለ። ዳር ድንበሩን ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ። ዳር ደንበሩን አሳልፎ ከሰጠው ጠላት ጋር ሆኖ ንፁሃንን በከባድ መሳርያ የሚጨርስ ጭራቅ ሀይል አለ። ከደርግ የባሰ!

ይህ የምታዩት ፎቶ ዛሬ የተነሳ ነው። ገንዳውሃ ከተማ መተማ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው። ትህነግ የሱዳን ጦርን መርቶ ቤተሰባቸውን በከባድ መሳርያ ያስመታባቸው እናት ሲያለቅሱ የሚያሳይ ነው። አንድ አባት ሊያፅናኑዋቸው ሲጥሩ ያሳያል።

ትህነግ የከፈለው የሱዳን ጦር ደንበር ጥሶ ሲመጣ የኢትዮጵያ የሚጠብቅ ጦር አልነበረም። የሱዳኑንም፣ የኢትዮጵያ ነው የሚባለውንም የሚመሩት ትህነጎች ናቸው። እናቶች ደግሞ ዋይታቸውን ለማንም ማሰማት አይችሉም። ወራሪውም አስወራሪውም ጠላት አድርጎ ፈርጇቸዋል። ደርግ እንኳን ወደቀ ያሉ እናቶች ከደርግ የባሰ ጭራቅ ጥሎባቸዋል። ዛሬም ዋይታቸው ቀጥሏል!

የሱዳን ጦር በአማራ ገበሬዎች ላይ የከፈተው ጦርነት የጀመረው ሰኔ 25/2010 ዓም ነው የሚባለው ስህተት ነው። ሰሚ ጆሮ አጥቶ ነው እንጅ ወረራው በአዲስ መልክ ወረራው ከጀመረ ከ25 ቀን በላይ ሆኖታል። ማስተካከያ የሚያስፈልገው ባለፉት ሶስት ሳምንታትም በርካታ ገበሬዎች ስለተገደሉ፣ ስለቆሰሉና ስለጠፉ ነው! ይህ ሁሉ በሆነበት ጉዳዩን ትናንት የተፈጠረ ማስመሰል አግባብ አይደለም። እስካሁን የነበረውን ቸልተኝነት ለመሸፈን ካልሆነ!

ከ20 ቀን በፊት ሶስት ገበሬዎች በሱዳን ጦር ታፍነው ተወስደዋል። የተገደሉ አሉ።

ከአራት ቀን በፊት እንኳ አራት ሰራተኞች እንዲሁም አንድ ኢንቨስተር ከእርሻቸው ላይ እያሉ ታፍነው ተረሽነዋል። በሱዳን ጦር።

ከሳምንት በፊት የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ መሬት በመግባት የገበሬዎችን ማሳ አውድሟል!

ወረራው የጀመረው ሰኔ 25 ነው የሚለው ምንጩ ከኢሳት መሰለኝ። የማከብራቸው የኢሳት ጋዜጠኞች በዶክተር አብይ ድጋፍና መሰል ጉዳዮች ላይ ተጠምደው እንጅ ከሶስት ሳምንት በላይ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ እንዲሁም እኔ ወረራ መኖሩን ስንገልፅ ቆይተናል።

የሰሜን ዕዝ ዜና የማያመልጠው ኢሳት ለሶስት ሳምንት ይህን ሰሜን ጎንደር አካባቢ በድንበር ጠባቂ ገበሬዎች ላይ የተቃጣ ጥቃት ጉዳዬ አላለውም ለማለት እደፍራለሁ።

‹‹በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር መካከል የተፈጠረው ግጭት ምክንያቱ የእርሻ መሬት ይገባኛል ጥያቄ ነዉ፡፡›› አቶ ዘላለም ልጃለም፡- የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ

በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ግጭት ተፈጥሯል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበትን የእርሻ መሬት እንዳያርሱ መከልከላቸዉ ነዉ፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና በሱዳን የጸጥታ ኃይሎች መካከል ግጭት ተከስቷል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘላለም ልጃለም እንደነገሩን የእርሻ መሬቱን ለረጅም ዓመታት እየተጠቀሙበት የሚገኙት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ናቸዉ፡፡ አሁን ግን የሱዳን አመራሮች ‹‹የእርሻ መሬቱን መጠቀም ያለብን እኛ ነን›› የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ሃሳቡ ተገቢነት የሌለዉ መሆኑንም ለአካባቢዉ የሱዳን አመራሮች አስረድተናል ነው ያሉት አቶ ዘላለም፡፡ የሱዳን አመራሮች ግን ሃሳቡን ባለመቀበላቸዉ መግባባት እንዳልተቻለ ነዉ የነገሩን ዋና አስተዳዳሪው፡፡

ግጭቱ የተከሰተዉ በመተማ ወረዳ ደለሎ ቁጥር 4 የእርሻ እና የኢንቨስትመንት ቦታ እና በሱዳን ባሶንዳ ዞን መካከል በሚገኝ ቦታ ነዉ፡፡
በዚህም ከሁለቱም በኩል ህይዎታቸዉን ያጡ እና የቆሰሉ መኖራቸዉን ሰምተናል፡፡ የጉዳቱን መጠን በተመለከተም ዝርዝር መረጃ እንዳገኘን እናደርሳለን፡፡

ግጭቱን ለማረጋጋት የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ አካባቢዉ ተሰማርተዋል፡፡ አሁን አንጻራዊ መረጋጋት መፈጠሩንም አቶ ዘላለም ነግረዉናል፡