Blog Archives

ኮማንድ ፖስቱ በሞያሌ ከተማ ትጥቅ እያስፈታ መሆኑ ታወቀ

ራሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ አስፈጻሚ እያለ የሚጠራው ኮማንድ ፖስት ትጥቅ እያስፈታ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ እንደ ግብረ ኃይሉ ገለጻ ትጥቅ የማስፈታት እንቅስቃሴ እየተደረገ ያለው በዋነኝነት በሞያሌ ከተማ ሲሆን፤ በተጨማሪም በሌሎች አካባቢዎችም ትጥቅ የማስፈታት እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ እሁድ ሚያዝያ 28 ቀን 2010 ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሚዋሰኑበት ሞያሌ ድንበር አካባቢ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እና በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት መካከል ረዥም ሰዓት የወሰደ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን መዘገባችን ይታወቃል፡፡ በዕለቱ ከረፋዱ አምስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ድረስ በተደረገው በዚሁ የተኩስ ልውውጥ፣ ከሁለቱም ወገኖች የሞት እና የመቁሰል ጉዳት ደርሷል፡፡ ይህን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ያወጣው ኮማንድ ፖስት፤ የተካሄደውን የተኩስ ልውውጥ፡- “በሁለት ጎራዎች የታጠቁ ኃይሎች መካከል ማኅበረሰቡን ዒላማ ያደረገ በመጠኑም ሰፋ ያለ ግጭት ተከስቶ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡” ሲል ገልጾታል፡፡ በተከሰተው ግጭትም “የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ የመቁሰል አደጋም ደርሷል፡፡” ሲል አክሏል፡፡ የተኩስ ልውውጡ የተካሄደው በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እና በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት መካከል መሆኑ ቢታወቅም፤ ኮማንድ ፖስቱ ግጭቱን ‹‹በሁለት ጎራዎች የታጠቁ ኃይሎች መካከል የተካሄደ›› ሲል መግለጹ ግራ አጋቢ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ እሁድ ዕለት በሁለቱ ክልሎች የፖሊስ አባላት መካከል የተካሄደውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በዛሬው መግለጫው፣ ትጥቅ የማስፈታት እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቀው ኮማንድ ፖስቱ፤ እስካሁን ድረስም የተለያዩ የመሳሪያ ዓይነቶችን መንጠቁን ተናግሯል፡፡ ግብረ ኃይሉ ከፖሊስ አባላት እጅ መሳሪያ እየነጠቀ መሆኑን በይፋ ባይገልጽም፤ መረጃዎች ግን በሞያሌ የሚገኙ ለጊዜው ቁጥራቸው
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አምቦ ዩንቨርስቲ ዋናው ካምፓስ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ ፤ ውጥረቱ አይሏል ።

አምቦ ዩንቨርስቲ ዋናው ካምፓስ የአግአዚ ሰራዊት ለተቃውሞ በወጡ ተማሪዎች ላይ የጥይት እሩምታ እያወረደ ነው ፤ ከዩኒቨርስቲው በኮማንድ ፖስቱ ታፍሰው የታሰሩ ተማሪዎችን ጨምሮ በሀገሪቱ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ተማሪዎቹ ጠይቀዋል ። በርካቶች ጉዳት እነንደደረሰባቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ ። Minilik Salsawi
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኮማንድ ፖስቱ ለጠቅላይ ሚኒስተሩና ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አላቀርብም ማለቱ ተሰማ።

  ኮማንድ ፖስቱ ለጠቅላይ ሚኒስተሩና ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አላቀርብም ማለቱ ተሰማ።   በፓርላማ ውድቅ የተደረገው ነገር ግን ህወሃት በጉልበት ያጸደቀው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ ከተደነገገበት የካቲት 9/2010 ዓ.ም ጀምሮ አገራችን ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቃ እየማቀቀች እንደሚገኝ ይታወቃል። በመሆኑም ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በበላይነት የሚያስፈጽሙትና የሚቆጣጠሩት ጠቅላይ ሚኒስተሩ፣የመረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቱ፣ የመከላከያ ሚኒስተሩ፣ የመከላከያ ኢታማዦር ሹም እንዲሁም የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽነር ናቸው። በዚህም መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተገኙ ውጤቶች፣ የጠፉ ጥፋቶች፣በአጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም እንዲገመገሙ በየቀጠናው የተሰበሰቡ መረጃዎች ተጠቃለው ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ዝርዝር ሪፖርት እንዲደረግ ያዛል። ይሁን እንጂ ኮማንድ ፖስቱን በበላይነት የሚቆጣጠሩት የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዦች የሆኑት የህወሃት ወታደራዊ አዛዦች ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር መረጃ እንዲሁም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት በመላ አገሪቱ ስለታሰሩት ዜጎች ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ለዶ/ር አቢይ አህመድ እንዲሁም ለፖለቲካው አመራር ሪፖርት አናደርግም ማለታቸውን የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል። የመረጃ ምንጮቻችን አክለው የህወሃት ሰዎች ለዶክተር አቢይ ሪፖርት ብናቀርብ ነገሮችን ያበላሽብናል ብለው መስጋታቸውን አብራርተዋል። በተለይ ጄነራል ሳሞራ የኑስ <<ትላንት ለእኔ በተጠንቀቅ ሰላምታ ይሰጠኝ ለነበረ ለአንድ ተራ ወታደር ዛሬ ገና ለገና ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ ብየ ሪፖርት አላቀርብም >> ሲል መናገሩ ተከትሎ ሁኔታው ዶ/ር አቢይ አህመድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም ያበላሽብናል ከሚል የመነጨ ብቻ ሳይሆን ከነሳሞራ አንሸነፍም ባይነት እንዲሁም የመታብይና የበታችነት ስሜት የተቀዳ መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል። በዚህም ምክንያት በእነሳሞራ በአጠቃላይ በህወሃት ሰዎች ጥርስ ውስጥ
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News