“መንግሥት አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መነጋገር አይፈልግም” ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

የአስራ አንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት (ሲኦፒ) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ለመወያየት የቀረበለትን ጥሪ ውድቅ ያደረገው መንግሥት በአገሪቱ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የመነጋገር ፍላጎት ስለሌለው መሆኑን ገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ከተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ሰኞ መጋቢት 23/2016 ዓ.ም. ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ የጥምረቱ አባላት ግን ሳይሳተፉ ቀርተዋል።…