እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ “እንደ መደበኛ ታሳሪ እንዲታዩ” ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላለፈ

ከስምንት ወራት በኋላ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት የሕዝብ ተወካዮች እንዲሁም የአማራ ክልል እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት “እንደመደበኛ ታሳሪ እንዲታዩ” ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላለፈ። ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ያቀረበው ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ውድቅ እንደተደረገም የተከሳሾቹ ጠበቃ ለቢቢሲ ተናግረዋል።…