ከሚኒሊክ ሃውልት ይልቅ ሙዚየሙ ከመዘጋጃና ከአራዳ ህንፃ ጋር የተጣመረው ለምን ይመስልሃል ?

በሺህ የሚቆጠሩ ፎቶዎችን አይቻለው! በጣም ብዙ ቪድዮዎችን ተመልክቻለው! ይህንን ፕሮጀክት ከመዘጋጃ ጋር በድልድይ አገናኝተውታል! ምንም ከማይመለከተው ከአራዳ ህንፃ ጋር በመልክ አናበውታል በመልክ ብቻ ሳይሆን በመብራትና በቻሉት ማብለጭለጫ ሁሉ የታችኛውን የሙዚየም ክፍል አድምቀውታል።

ከዚህ ሁሉ የፕሮፓጋንዳ ምስሎችና ተንቀሳቃሽ ቪድዮዎች መሃል ይህንን ሙዚየም ከነባሩ የሚኒሊክ ሃውልት ጋር ሊያስታርቁት አልፈለጉም! ፎቶ እንኳን ሲያነሱት በድሮን ጭምር የሚኒሊክ ሃውልት እንዲገባ አይፈልጉም! ከአንድ ምስልና ቪድዮ በቀር ይህንን ፕሮጀክት ከሚኒሊክ ነባር ሃውልት ጋር ሊያዋህዱት አልፈለጉም! ደመቅመቁ ሁሉ ከመብራት እስከ ደናሽ ፋውንቴኖች በሺህ ከሚቆጠሩ ምስሎች መሃል ነገር አለሙ ሁሉ ያተኮረው በታችኛው የሙዚየም ክፍል በአራዳ በኩል ነው…

ከሚኒሊክ ሃውልት ይልቅ ሙዚየሙ ከመዘጋጃና ከአራዳ ህንፃ ጋር የተጣመረው ለምን ይመስልሃል? ይሄንን ተራና ተልካሻ ሃሳብ እንኳን አራዶቹ አራዳ ግዑዙ ህንፃ እንኳን ይባንነዋል!

አንዱ ሞኝ መጥቶ “ሚኒሊክ በሙዚየሙ ውስጥ ተሰርቶ የለ እንዴ?” ብሎ ሊያሞኘን ሲሞክር ከአራዳ ህንፃ ጋር ተያይተን

“የሲሚንቶና የመብራት ሰልፍ ታሪክ ሲያደበዝዙ አስበኸዋል” ብለን እንስቃለን 😂

 ሙሉቃል ቃል