በአዲስ አበባ ከተማ ጎተራ አካባቢ ዛሬ ምሽቱን በርካታ የአማራ ተወላጆችና የኤርትራ ተወላጆችን በገፍ እያፈኑ መሆኑን የአይን እማኞች አስታወቁ።

(ኢትዮ 360- የካቲት 2/2016) በአዲስ አበባ ከተማ ጎተራ አካባቢ ዛሬ ምሽቱን በርካታ የአማራ ተወላጆችና የኤርትራ ተወላጆችን በገፍ እያፈኑ መሆኑን የኢትዮ 360 የአይን እማኞች አስታወቁ።

ምንጮቹ ይላሉ ዛሬ ምሽት ምሽት 2:30 ላይ ጎተራ የሚገኙት የጋራ መኖርያ ቤቶች ሲቪልና የፖሊስ ልብስ በለበሱ የሰው በላው ሃይሎች መከበባቸውን ይናገራሉ።

ይሄ አካባቢውን የወረረ ሃይልም በጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ያሉ የአማራ ተወልጆችንና ኤርትራውያንን እያፈነ ተዘጋጅተው በሚጠብቁት ተሽከርካርዎች መጫኑን ጠቁመዋል።

እነዚህ ፓትሮል ተሸከርካሪዎች በአንዴ ብቻ ሳይሆን እየተመላለሱ ማጋዝ መቀጠላቸውንም አስታውቀዋል።

በተለይ ይላሉ የኢትዮ 360 የአይን እማኞች ኤርትራውያን ተከራይተው የሚኖሩበትን ቤት እየመረጡ ሰብረው በመግባት ጭምር አፈናውን እያካሄዱ መሆኑን አጋልጠዋል።

ኢትዮ 360 አቅርቡ ባወጣው መረጃው የአድዋ በአል እስኪከበር ድረስ ከ10 እስከ 20ሺ የአማራ ተወላጆችን የማፈን መመሪያ ከሰው በላው ስብስብ መውረዱን ይፋ ማድረጉንም ያስታውሳሉ።

ከዛም አልፎ በዚሁ የጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለውና ከኦሮሚያ ክልል የመጣ የደህንነት ሃይል መግባቱን ኢትዮ 360 በመረጃው ማጋለጡንም ያስታውሳሉ።

በሴቶች ስም ገስት ሃውሶቹ እንዲከራዩለት የተደረገው ቡድን የመጣውም በመልስ አብዲሳ ትእዛዝ መሆኑንም መረጃው ማመልከቱ ይታወሳል።

ይሄ ደህንነት ነው የተባለው ስብስብ በጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በሚገኙ ግሮሰሪዎች ውስጥ የሰከሩ መስለው አማራውን ማሳፈን የጀመሩት የገቡ ቀን ማምሻውን እንደነበርም በመረጃው መውጣቱ ይታወሳል።

እናም ይሄ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ሰአትም የንጹሃን የአማራ ተወላጆችና የኤርትራውያን አፈና መቀጠሉን የኢትዮ 360 የአይን እማኞች ጠቁመዋል።