ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ: በአ/አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ጳጳስ፤ የመናገሻ ቅ/ማርያም አበ ምኔት አባ ሞገስ ኀ/ማርያም ሥራ አስኪያጅነት ተመደቡ

ብፁዕነታቸው፣ የጉራጌ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ እስከ መጪው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ድረስ እየመሩ ይቆያሉ፤ ቋሚ ሲኖዶሱ፣ እስከ ምሽት ባዋለው ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው፣ የመናገሻ ቅድስት ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ የኾኑትን አባ ሞገስ ኀይለ ማርያምን፣በጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅነት መድቧቸዋል፤ ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ “የምጠቁመው ሰው የለኝም፤” ማለታቸውን ተከትሎ ከቋሚ ሲኖዶሱ አባላት የተጠቆሙት አባ ሞገስ፣ ያለልዩነት በሙሉ ድምፅ ነው የተመደቡት፤ …


መረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV