የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በእ.አ.አ 2020 የተደረገውን ምርጫ ውጤት ለመቀልበስ ሞክረዋል በሚል የተመሠረተባቸውን ክስ አስመልክቶ፣ ስለጉዳዩ ከፍርድ ቤት ውጪ እንዳይናገሩ ጉዳዩን በሚመለከቱት ዳኛ የተጣለባቸው እገዳ እንዲነሳ፣ ጠበቆቻቸው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትን ጠይቀዋል።
የትረምፕ ጠበቆች ዛሬ በፍርድ ቤት እንደተናገሩት፣ እገዳው የፖለቲካ ንግግርን የሚገታ ውሳኔ ነው ብለዋል።
…