የሰላም ንግግሩ ተስፋ እና የሀገሪቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ

ከወራት ዝምታ በኋላ ተፋላሚ ወገኖች ለሌላ የሰላም ንግግር በታንዛንያዋ የንግድ ከተማ ዳሬ ሰላም ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ንግግር እየተደረገ መሆኑን ከሳምንት ዝምታ በኋላ ባለፈው ሐሙስ ነበር ይፋ ያደረገው ። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተደራዳሪዎቹ ከመንግስት ተወካዮች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ቀደም ብሎ ነበር ያስታወቀው።…