በአፋር ክልል ከጦርነቱ በኋላ የህጻናት ጋብቻ አሃዝ መጨመሩ ተገለጸ

በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት ያክል የተካሄደው ጦርነት ሴቶችን ተገድዶ መደፈርን ጨምሮ ለተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶች ያጋለጠ ነበረ። የሁለት ዓመቱ ጦርነት የፈጠረውን ማኅበራዊ ቀውስ ተከትሎም በአፋር ክልል የህጻናት ሴቶች እና የልጃገረዶች ጋብቻ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን በመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል፤ ካርድ ኢትዮጵያ የተሰራ ጥናት አመላከተ።

የጥናቱን ይዘት እና በክልሉ ያለውን የህጻናት …