“የልጆቼን ጥያቄ ባለመመለሴ . . እንደ እናት መከታ አልሆንኳቸውም ብዬ ራሴን እወቅሳለሁ” ሚለን ኃለፎም

አቶ ሳምሶን ተክለሚካኤል ከሁለት ዓመት በፊት በኬንያ መዲና ናይሮቢ፣ ኪሌሌሽዋ በተባለ አካባቢ የግል መኪናውን ሲያሽከረክር ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች መንገድ በመዝጋት ከመኪናቸው ካስወረዱ በኋላ ወደሌላ ተሽከርካሪ አስገብተው ሲወስዷቸው በወቅቱ በመንገደኞች ተቀርጾ ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ከተለቀቀ ምስል መረዳት ተችሏል። ባለቤቱ ሚለን ኃለፎም ሁለት ዓመት ሙሉ ቤተሰቡ የት አንዳለ እና ያለበትን ሁኔታ አለ…