አርቲስት ቴዲ አፍሮ የደም ልገሳውን የከለከሉትን ደም ለጋሾችን ያጉላሉትን የመንግስት አካላት አወገዘ

May be an image of 1 personአርቲስት ቴዲ አፍሮ የደም ልገሳውን የከለከሉትን የመንግስት አካላት አወገዘ። በማሕበራዊ ድረ ገፅ ያስተላለፈውን መልዕክት ከታች ያገኙታል።

የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን የሚውለውን የልደት በዓሌን በማስመልከት ላለፉት ረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በመገኘት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ ደም በመለገሰ ሰብአዊ ተግባር ለምትፈፅሙ የልብ አድናቂዎቼና ወዳጆቼ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፤ በዘንድሮው ደም የመለገስ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ባልተገባ ሁኔታ ለገጠማችሁ መጉላላት የተሰማኝን ኅዘን ስገልፅ ይህን ፍፁም ሰብአዊ ሕይወት የማዳን መርሐ ግብር በተገቢው ሁኔታ እንዳይከናወን ክልከላ ያደረጉ መንግሥታዊ አካላትን በጥብቅ በማውገዝ ነው።

በተጨማሪም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት መልካም ምኞታችሁን በተለያየ መንገድ ለገለፃችሁልኝ ክቡራን ወገኖቼ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።

ፍቅር ያሸንፋል

ቴዎድሮስ ካሣሁን ( ቴዲ አፍሮ)

May be an image of text