የኦሮሚያ የጸጥታው ጀነራል ከማል በደራ መገነኘታቸው ጥያቄ እያስነሳ ነው -ናኦሚን በጋሻው

በስሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች እራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በማንሳት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። በወለጋ፣ በሃረርጌ በርካታ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች መጠነ ሰፊ የጸጥታ ችግሮች አያሉ፣ ካልጠፋ ቦታ ሰላማዊ በሆነው በደራ የክልሉ የጸጥታ ሃላፊ ጀነራል ከማል ገልቹ ተገኝተው የነበረ ሲሆን፣ የጀነራሉ በደራ መገኘት በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው።
የጸጥታው ሃላፊው ምን አልባት በደራ የተነሳውን የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ፣ የፖለቲካና ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ከመስጠት፣ በሃይል እርምጃ ለማፈን ከመታሰቡ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ ያላቸው አንዳንድ ወገኖች ቢኖሩም የተደረገው ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊና ምንም አይነት ችግር ያልታየበት ሰልፍ ነበር።
በደራ ወረዳ ከ 85% ነዋሪዎች አማርኛ ተናጋሪ ሲሆኑ፣ ኦሮምኛ ካልተናገራችሁ በሚል፣ ኦሮምኛ ባለማዋቃቸው ምንም አይነት የወረዳው፣ የዞኑና የክልል መንግስት አገልግሎት የማያገኙ ሲሆን፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ መብታቸውን ተነፍገው በአገራቸው በቃያቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረው ነው እየሰሩ ያሉት።
በደራ ወረዳ በቀዳሚነት ጥያቄው ገንፍሎ ወጣ እንጂ ከሰባ አምስት በላይ የኦሮሞ ክልል ወረዳዎች ኦሮምኛ የማይናገሩ፣ ወይም ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰባት በብዛት የሚኖሩባቸው ናቸው። እዚያው ሰሜን ሸዋ ሳንወጣ፣ በቅምብቢት ወረዳ 60%፣ በአብቹ ወረዳ 55% ነዋሪዎች አማርኛ ተናጋሪዎች ይኖራሉ። ወደ ምስራቅ ሸዋ ስንሄድ በአዳማ ልዩ፣ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ወረዳዎች ቢያንስ ከሰባ በመቶ በላይ ነዋሪው አማርኛ ተናጋሪ ነው። በጂማ በአሰላና አካባቢው፣ በተለያዩ የምስራቅ አርሲ ቦታዎች ቁጥራቸው ኦሮሞ ያልሆኑ ወይንም ሕብረሄራዊ የሆኑ ማህበረሰባት ብዙ ናቸው።
የደራ ህዝብ ያነሳው ጥያቄ በመላው የኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ማሀበረሰባት የሚያንሱት ጥያቄ ነው ። ከዚህም የተነሳ የደራ ንቅንቃ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ጮራ ፈንጣቂ ንቃናቄ ሊሆን ይችላል ተብሎም ይጠበቃል።

► መረጃ ፎረም - JOIN US