በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት በፋኖ እና በአማራ ሕዝብ ላይ የጀመረውን ዘመቻ አወገዙ

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት በፋኖ እና በአማራ ሕዝብ ላይ የጀመረውን ዘመቻ በማውገዝ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጅ ላይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ይህ በባልደራስ፣ በዲሲ ግብረሃይል እና በአማራ አደረጃጀት አስተባባሪነት የተጠራውና በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት ሰልፍ የተለያዩ ተቃውሞዎችን አሰምቷል። እኔም ፋኖ ነኝ በሚል ግንባር ቀደም መፈክር የተመራው ሰልፍ በዶክተር አብይ አገዛዝ የሚካሄደውን አማራን የመጨፍጨፍ ዘመቻና ፋኖን የማሳደድ ኦፕሬሽንን አጥብቀው በመቃውም ድምጻቸውን አሰምተዋል። በወቅቱ በዘመቻው ለተገደሉ ዜጎች የሻማ ማብራት ስነ ስርዐት ተከናውኗል።

Image

Image

Image

Image