የጠ/ሚር ፅ/ቤት የታይም መፅሄትን በስም ማጥፋት ወንጀል ከሰሰ!

ትናንት ከአለም ተፅእኖ ፈጣሪዎች አንዱ ብሎ መፅሄቱ የመረጣቸው ጠ/ሚር አብይ ላይ “ሆን ተብሎ የስም ማጥፋት እና ስብእናን የማጉደፍ ስራ ተሰርቷል” ይላል በቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ተፅፎ ከደቂቃዎች በፊት ለሚድያዎች የተሰራጨው ደብዳቤ።
ለዚህም አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ መፅሄቱ ተጠይቋል። በትናንትናው እለት የመንግስት ሚድያዎች ጉዳዩን እንደበጎ ነገር በሰበር ዜና ሲያራግቡት እንደነበር ይታወሳል።
ፋና፣ ኢቢሲ፣ ዋልታ፣ ኢፕድ እና ኢዜአ ትናንት ጠ/ሚር አብይ አህመድ በታይም መፅሄት “ተፅእኖ ፈጣሪ ሆነው ተመረጡ” ብለው ያቀረቡትን ዜና ሁሉም አጥፍተውታል።
ታይም መፅሄት ያለው ነገር አሁን 19ኛው ወሩን ያስቆጠረው የእርስ በርስ ጦርነት በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ግፍና በደል ምሳሌ ሆኗል፡ የአብይ ጦር በጅምላ ግድያ፣ ጾታዊ ጥቃት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ተከሷል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የተጎዱበት ረሃብ ያንዣብባል። በማርች ወር ላይ ለወራት ታግዶ የነበረውን ክልሉን ሰብአዊ አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል እርቅ አውጇል። ነገር ግን በጁን 2021 እንደ ቀደመው “የሰብአዊ እርቅ ስምምነት”፣ በአብዛኛው ስልታዊ ነው የሚመስለው፣ እና ጥቂት እውነተኛ እርዳታ ደርሷል። አብይ በጥላቻ ንግግራቸው የትግራይ ታጋዮችን “እንክርዳድ” ብሎ መጥራት ጀምሯል። የአፍሪካ ሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች ኢትዮጵያ እንደ ሩዋንዳ ወደሚመስል የዘር ማፅዳት እንዳትወስድ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተማጽነዋል። በጥር ወር የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ “ግጭቱን የማስቆም እና ለሰላም የበኩላቸውን አስተዋፅዖ የማድረግ ልዩ ሀላፊነት አለባቸው” በማለት አቢይን ነቅፎታል። ሲል ፅፏል ።
The civil war, now in its 19th month, has become a byword for atrocities against Tigrayans: Abiy’s forces have been accused of massacres, sexual assault, and ethnic cleansing. Famine looms with millions impacted. In March, he declared a truce to allow humanitarian access to the region, which had been blocked for months. But like a previous “humanitarian truce” in June 2021, it appears to be largely strategic, and little real aid has arrived. Abiy has started calling Tigrayan rebels “weeds” in a rise in hate speech. African civil-­society groups are now pleading with the U.N. to act, lest Ethiopia devolve into ethnic cleansing reminiscent of Rwanda. In January, the Norwegian Nobel Committee in a rare move criticized Abiy, noting he has “a special responsibility to end the conflict and contribute to peace.”

May be an image of text that says 'Dear Aryn and TIME Magazine colleagues dismay that thep purposef email Prime Ahmed published pproach se livelihoods the and instability other parts various past Please Human Forces nd the ts Prime blatantly station maiaa are We look forward your response. regards, Billene Seyoum Woldeyes -ቢልለኔሥዩም ቢልለኔ にግ8ርたんችት Secretariat Unit Ethiopia'