ከመከላከያ ሰራዊት ለቀው የወጡ እና የተሰናበቱ አማራ ክልል ነዋሪ የሆኑ ወታደሮችን መንግስት እየለቀመ ማሰር ጀምሯል።

ከመከላከያ ሰራዊት ለቀው የወጡ እና የተሰናበቱ አማራ ክልል ነዋሪ የሆኑ ወታደሮችን መንግስት እየለቀመ ማሰር ጀምሯል። ሕወሓት እና ኦነግሸኔን ትጥቅ ማስፈታት ያልቻለው መንግስት ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት ኦፕሬሽኑን ጀምሯል። ይህ ኦፕሬሽን በተመስገን ጥሩነህ በአበባው ታደሰ እና በዘላለም የሚመራ ኦፕሬሽን ሲሆን በአማራ ክልል ያሉ በሕግ ማስከበሩ ስራ ላይ የተሰማሩ እንደ ፋኖ፣ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን፣ ሚሊሻዎችንና ሌሎች አገር ጠባቂ ኃይሎችንና አካላትን ማስወገድ ዋናው ተልዕኮው ነው።

በምዕራብ ጎጃም ዞን፤ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፤ ከባሕር ዳር ከተማ በአጭር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መርዓዊ ከተማ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ልዩ ሃይል አባልነት በፈቃዳቸው የተመለሱ 18 ወታደሮች ታስረዋል።

በተመሳሳይ በምዕራብ ጎጃም፤ ደቡብ አቸፈር ወረዳ፤ ዱርቤቴ ከተማ ውስጥ 14 ተመላሽ ወታደሮች በአብችክሊ ዙሪያ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል።

ዜጎች የፈለጉት ሰራዊት አባል የመሆን መብት ቢኖራቸውም፤ በሁለቱም ተቀራራቢ ከተሞች ወታደሮቹ የታሰሩት “የአማራ ሕዝባዊ ኃይልን (ፋኖ) ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ናችሁ” በሚል ምክንያት ነው እየተባለ ነው።

በመርዓዊ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ከታሰሩት 18 ወታደሮች መካከል አምስቱ ቀደም ሲል የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል በመሆን በርካታ ግዳጆችን በብቃት የተወጡ ናቸው። አምስቱንም ፖሊስ ጣቢያው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳልፎ የሰጣቸው ሲሆን፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የትና በምን ሁኔታ እንዳሉ አልታወቀም።

ከዚህ ቀደም ብሎ “ትታሰራላችሁ ወይም እርምጃ ይወሰድባችኋል” የሚል ማስጠንቀቂያ ይደርሳቸው እንደነበርም ለታዳኞች ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል።

ለእስር እየተፈለጉ ከሚገኙት መካከል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በሚያዩት እንቅስቃሴ በመከፋት፤ ከሰራዊቱ በፈቃዳቸው ከወጡ በኋላ የአማራ ልዩ ሃይልን ለመቀላቀል ጠይቀው የተከለከሉ ይገኙበታል።