የወራቤ ዩንቨርስቲ በርካታ የኦርቶዶክስ ተማሪዎች መታሰራቸውን ተከትሎ ፈተና እሰጣለሁ ማለቱ ከተማሪዎች ተቃውሞ ገጠመው

May be an image of 5 people, people standing and outdoorsየወራቤ ዩኒቨርሲት ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች የታሰሩ ተማሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ፣ የተጎዱትም ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ እጅግ ሠላማዊ በሆነ ሁኔታ የዩኒቨርስቲውን አስተዳደር በሰልፍ ጠይቀዋል።
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ በኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ላይ እያደረሰ የሚገኘው ስነ ልቦናዊ ጫና በእጅጉ ስለመበራከቱ የተገለፀ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በፊት ዩኒቨርሲቲው በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መልዕክት በወራቤ ከተማ የተቃጠለ ምንም አይነት ቤተ ክርስቲያን አለመኖሩን በመግለፅ ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጭ እና የቤተ ክርስቲያንን ጥቃት ሲሸፋፍን ቆይቷል።
በቅርቡም ሆን ተብሎ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን ለመጉዳት በሚመስል መልኩ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ጥቃት ደርሶባቸው ህክምናቸውን እየተከታተሉ እያሉ ፈተና እንሰጣለን በሚል ያወጣውን ማስታወቂያ ተማሪዎች ባደረጉት ሰልፍ በእጅጉ ተቃውመውታል።
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
May be an image of 3 people and people standing