አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የባልደራስ አመራሮች አርባ ምንጭ ከተማ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ።

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የባልደራስ አመራሮች አርባ ምንጭ ከተማ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዝዳንቱ አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ እንደታሰሩበት አስታውቋል።

ፓርቲው አመራሮቹ የታሰሩበት አርባ ምንጭ ከተማ መሆኑን ገልጿል።

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው ልዑካን ዛሬ ወደ አርባምንጭ ያቀኑ ሲሆን ወደ አርባ ምንጭ የሄደቱ በደቡብ ክልል የፓርቲውን የሀገር አቀፍ ፊርማ ንቅናቄ ለማስጀመር እንደሆነ ተገልጿል።

ፓርቲው የፊርማ አሰባሰቡን ንቅናቄ ለማስጀመር በአርባ ምንጨ እና በወላይታ ሶዶ ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማድረግ ጠይቆ ከተፈቀደ ቦኃላ፣ ” ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው ” በሚል ስብሰባዎቹ እንዳይደረጉ እንደተከለከሉበት አስረድቷል።

ከዚህ በኃላ ነው ፓርቲው ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ ወደ አርባ ምንጭ የሄዱት ልዑካን በፖሊስ መታሰራቸውን ያሳወቀው።

ባልደራስ እስሩ ያለምንም ምክንያት የተፈፀመ ነው ብሏል።