የአማራ ህዝባዊ ኅይል/ፋኖ/ መልስ ሰጠ
””””'””””””

–
ዛሬ ጥር 06 ቀን 2014 ዓ.ም መንግስት ከተወሰኑ ፋኖወች ጋር ስብሰባ እንደሚያደረግ መረጃ ቢኖረንም እኛ በማናዉቀው እና የስብሰባው አዘጋጆች በሚያውቁት ምክንያት መንግስት የውይይት ጥሪውን ያደረገው መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከመሆኑም ባሻገር ለአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) እና ከአደረጃጀታችን ጋር ለሚሰሩ በርካታ ፋኖወች የስብሰባ ጥሪ አለማድረጉን እናሳዉቃለን።
–
እንዲሁም በግልም ሆነ በአደረጃጀት ደረጃ ባልተሳተፍንበት በዛሬው ውይይት የሚወሰን ማናቸውም ጉዳይ የአማራ ሕዝባዊ ኃይልን (ፋኖ)- APF የማይመለከት መሆኑን እናሳውቃለን።
–
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
ጥር 06 ቀን 2014 ዓ.ም
ባሕር ዳር-ኢትዮጵያ