ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሆስፒታል ገቡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የጤና ችግር አጋጥሟቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ በቅዱስነታቸው አለመገኘት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉ ተነግሯል።

ቅዱስነታቸው ፥ በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ላይ በሌሉበት ሁኔታ ጉባኤውን ማካሔድ ስለማይቻል የቅዱስ ፓትርያርኩ ጤና እስከሚመለስ ድረስ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን የቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል።