መንግሥት ወደ ትግራይ እርዳታ እንዳይደርስ እንቅፋት የሆነው ህወሓት ነው ሲል ከሰሰ

የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦት ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባ እገዳ አለመጣሉን እና ሕዝቡ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳያገኝ እንቅፋት የሆነው ህወሓት ነው አለ። የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ ሠራቱን ከክልሉ ካስወጣ በኋላ ለትግራይ ሕዝብ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ያለ ምንም መስተጓጐል በአፋር አብአላ በኩል በቀጥታ እንዲደርስ ማድረጉን አስታውሷል።…