ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ቢሮ አይገቡም፤ ባለጉዳይም አናግረው አያውቁም ተባለ

የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጊዜያቸውን በዙረትና በስብሰባ ስለሚያጠፉ ቢሮ ገብተውም ይሁን ባለጉዳይ አናግረው አያውቁም ጭራሽ ቢሯቸውን አያውቁትም ሲሉ አብረዋቸው የሚሰሩት የስራ ባልደረቦቻቸው ይናገራሉ። ከበታች ያሉ ባለስልጣኖቻቸው ሊጎበኙትና ሊመርቁት ብሎም ሊመሩት የሚችሉት ስብሰባዎችን ሳይቀር ወይዘሮ አዳነች በቁጥጥራቸው ስር አውለውታል ሲሉ የስራ ባልደረቦቻቸው ይተቻሉ።

የስራ ባልደረቦቻቸው እንደሚሉት በሁሉም ቦታዎች ላይ ጆከር ሆነው ለመታየት የሚፈልጉት ከንቲባዋ ለሌሎች ባለስልጣናት እድል እንደማይሰጡና በህዝብ ፊት እርሳቸው ብቻ ደምቀውና ገዝፈው በመታየት ሕዝበኝነት መጠመዳቸውን ይናገራሉ። የባለጉዳዮችን ሮሮ፤ የየክፍለከተማውን መልካም አስተዳደርና የባለስልጣናትን ሙስና በተለይ የመሬት ችብቸባን አቤቱታ መፍታትና አትኩሮት ሰጥተው የተሻለ ስራ መስራት ያልቻሉት ከንቲባዋ በፍጹም የበታች ባለስልጣኖቻቸው ጎልተው እንዲወጡ እንደማይፈልጉ የስራ ባልደረቦቻቸው ይናገራሉ።

በቅርቡ እንኳን በምክትል ከንቲባውና በኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው እንዲሁም በባህልና ቱሪዝም በኪነጥበብ ጉዳይ ትችት ቀርቦባቸዋል። የፌዴራል መንግስት ኮሙኑኬችንን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች የኮሙኑኬሽን ኃላፊዎች በተለያዩ ጉዳዮች መግለጫዎችን ሲሰጡ የአዲስ አበባ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ኝ ለናሙና ተቀምጠው ምንም አይነት መግለጫ እንዳይሰጡ በከንቲባዋ ታግደው ከንቲባዋ ራሳቸው የኃላፊውን ስራ ይዘዋል ሲሉ ባልደረቦቻቸው ይተቿቸዋል።

እንዲሁም በዚህ ሰሞን የመስቀል አደባባይን በተመለከተ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የሚያራምዱት አቋም ተቃውሞ አስከትሎባቸዋል። ከንቲባዋ ሁሉንም ብሄሮችና ሃይማኖቶች በእኩልነት ማየት ሲገባቸው በአድልዎ ይሰራሉ ተብለዋል። ይህንን በተመለከተ እስከአሁን ምንም መፍትሄ ካለመገኘቱም በላይ ባለድርሻ አካላትን ለማናገር ፈቃደና አልሆኑም የሚል አቤቱታ ቀርቦባቸዋል።