" /> የሴቶች መብት ተሟጋች እና ጠበቃ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የሴቶች መብት ተሟጋች እና ጠበቃ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው ተሿሚዋን ተሰናባቹን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኜ መላኩ ተክተው እንዲሰሩ በእጩነት ያቀረቧቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወ/ሮ መዓዛ ባላቸው የዳበረ ልምድ ምክንያት የአገሪቱን የፍትህ ስርዓቱ ወፊት ያራምዱታል በሚል በእጩነት እንዳቀረቧቸው ለምክር ቤቱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ይሁንታውን ሰጥቷቸዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በህግ የዳበረ ልምድ ያላቸው ፣ በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ በማገልገል አንቱታን አትረፈዋል፡፡
ከህገ መንግስት አርቃቂ ከሚሽን አባልነት በግላቸው ለሴቶች ከለላ የሚሆን ድርጅት እስከማቋቋምም ደረሰዋል፡፡

በመሆኑም በዛሬው ዕለት የተሰጣቸው የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንትነት ሹመት በፍርድ ቤቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ያደርጋቸዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊም ቃለ መሃላ ፈፅመው በህዝብና በመንግስት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቲቪ


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV