“የኛ ቲቪ” የተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ በመንግስት ማስጠንቀቂያ ተሰጠው

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙኃን ሐሰተኛና ወቅቱን ያላገናዘበ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ባለሥልጣኑ አሳሰበ
“የኛ ቲቪ” የተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ በተደጋጋሚ ሐሰተኛ መረጃን እያሰራጨ እና ወቅቱን ያላገናዘበ ዘገባ እየሰራ መሆኑን ከእለታዊ ክትትል የአዝማሚያ ትንታኔ እና ከዜጎች በቀረቡ ጥቆማዎች መነሻነት ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን ባለስልጣኑ ገልጿል።
በዚህ መነሻ ለቴሌቪዥን ጣቢያው የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙኃን በሙሉ ሐሰተኛ እና ወቅቱን ያላገናዘበ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ባለስልጣኑ አሳስቧል።