የሕወሓት ታጣቂዎች በወረባቦ ከ24 በላይ ንፁሃንን በግፍ ገድለው አስከሬናቸው በአውሬ እንዲበላ አደረጉ

May be an image of 1 person, child, tree and outdoorsየአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች ለጥቂት ቀናት በቆዩባቸው የወረባቦ ወረዳ አካባቢዎች ከ24 በላይ ንፁሃንን በግፍ ገድለው አስከሬናቸው በአውሬ እንዲበላ ማድረጋቸውን የሟቾች ቤተሰቦች ተናገሩ፡፡ የሽብር ቡድኑ በወረባቦ ወረዳ 18 ቀበሌ ብቻ ከ14 በላይ ስለ ፖለቲካ ምንም ያማያወቁ ንፁሃን አርሶ አደሮችን በመግደል የግፍ ድርጊት መፈፀሙን የጥቃቱ ሰለባ ቤተሰቦች ገልጸዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ አርሶ አደሮችን የገደለው ሰብላቸውን እየተንከባከቡ ባሉበት ሲሆን፤ አቅም ያላቸው ሴቶች ልጆቻቸውን በመያዝ ህይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተዋል፤ መሸሽ ያልቻሉ አቅመ ደካማዎች ደግሞ በግፍ ገድሏቸዋል ብለዋል፡፡ May be an image of 2 people, child, people standing and outdoorsአስክሬናቸውም እንዳይቀበር አድርጎ በአውሬ እንዲበላ ማድረጉን የሟቾች ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡
የወረባቦ ወረዳ 18 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ጠይባ መሀመድ በ22 ዓመታት ትዳራቸው 4 ልጆችን ያፈሩት አጋራቸው በሽብር ቡድኑ እንደተገደለባቸው ተናግረዋል።ቡድኑ አስክሬኑን አናስቀብረም ብሎ በአውሬ እንዲበላ አድርጓልም ነው ያሉት፡፡
ሌላኛዋ የወረባቦ ወረዳ 18 ቀበሌ ነዋሪ አይሻ ሰኢድ አሸባሪ ቡድኑ የተኩስ እርምታ ሲከፍትባቸው መኖሪያቸውን ለቀው የሸሹ ቢሆንም መሸሽ ያልቻሉ አቅመ ደካሞችን ጨምሮ የ60 ዓመት ወላጅ እናታቸው በሽብር ቡድኑ እንደተገደሉባቸው አስታውቀዋል። ሰርጎ ገቦቹ አስክሬናቸው በአውሬ እንዲበላ ማድረጉንም አክለዋል። በደቡብ ወሎ የወረባቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኻሊድ መሀመድ በወረዳው በ3 ቀበሌዎች 24 የሚሆኑ ህፃናትን ወጣቶችንና አቅመ ደካማ አርሶ አደሮችን አሸባሪ ቡድኑ በግፍ ገድሏል ሲሉ ለኢብኮ ተናግረዋል፡፡
May be an image of 1 person, standing and outdoors