በ2014 ዓ.ም በእርግጠኝነት ድል እንጠብቃለን፤ ይሳካል – ብ/ ጀ ይታያል ገላው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ

‹‹በ2014 ዓ.ም በእርግጠኝነት ድል እንጠብቃለን፤ በእርግጠኝነትም ይህ ይሳካል›› ሲሉ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ክብር ከፍተኛ ተጋድሎና ጀብድ በመፈፀም አሸባሪው ህወሓት እየደቆሰ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ይታያል ገላው አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ይታያል ገላው በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ህወሓት በሁሉም አቅጣጫ እየተደቆሰ ሲሆን በአጭር ጊዜ ሀገሪቱ ሠላማዊ አየር እንድትተነፍስ ይደረጋል ብለዋል።

2014 የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና አባቶች ያቆዩትን ደማቅ ሀገራዊ አንድነት በበለጠ ተጠናክሮ የሚካሄድበት ዓመት እንደሚሆን ጠቁመው ድል የሚመጣው በውጊያ ብቻ አይደለም ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ፤ አሁን ያለው የድል ሠራዊትና ህዝብ በመሆኑና ጠንካራ ደጀን የተፈጠረ በመሆኑ በ2014 ዓ.ም በእርግጠኝነት ድል እንጠብቃለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምክትል አዛዡ እንዳብራሩትም መንግሥት የተናጠል ተኩስ አድርጎ የትግራይ ክልልን ለቆ ቢወጣም፤ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ዕድሉን ከመጠቀም ይልቅ በተለመደው የማደናበርና የመዋሸት ባህሪ ህዝቡን ሊያሳምንና ሊያሳስት መመኮሩን አመልክተዋል።

https://www.press.et/ama/?p=55685