የኑሮ ውድነት ያላቆመው የቁርጥ ሥጋ ፍቅር

በአዲስ አበባ አሉ የሚባሉ የቁርጥ ቤቶች በሬውን ከማረዳቸው በፊት የኋላ ታሪኩን ያጠናሉ። ለደንበኞቻቸው ጤንነት የደኅንንት ስጋት እንዳይሆን በሚል የሚደረገው ይህ የጀርባ ታሪክ ጥናት፣ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚገኙ የቁርጥ ነጋዴዎችን ፉክክር አክርሮታል። ይህ ያላረካቸው ደግሞ የራሳቸውን በሬ በማድለብ ለደንበኞቻቸው ያቀርባሉ። ታዲያ በእነዚህ ቁርጥ ቤቶች ከቱጃሮች እስከ ፖለቲከኞች የጥሬ ሥጋ አም…