የአዋሳ ጉባዬ ትልቁ ፈታና ሕወሃት ሳይሆን የአዴፓና የኦዴፓ ፍጥጫ ነው #ግርማ_ካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሕወሃቶች በአዋሳው ጉባዬ ተጽኖ ይኖራቸዋል ብዬ አላስብም። ወይ ይስማማሉ አሊያም ጥለው ይወጣሉ። ጥለው ከወጡም እንደም ግልግል ነው። ደሃዴኖች ያው በነፈሰበት ነው የሚሄዱት። በኔ እይታ ሕወሃት በፖለቲካ ሞታለች ብዬ ነው የማምነው።በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት በስፋት ትንታኔ መስጥት ይቻላል።

ትልቁ ጥያቄ አዴፓ(የገዱ ቲም) የሚጠይቃቸውን ጥያቂዎች ዶ/ር አብይና ድርጅቱ ኦዴፓ ይቀበላል ወይ የሚለው ነው።

“የሸገር የአዲስ አበቤዎች ናት፣ አሁን ያለው የፌዴራል አወቃቀር እንደገና መታየት አለበት” ..የሚሉ ጥያቄዎች አዴፓ አለው። እነዚህን ጥያቄዎች እነ ዶ.ር አብይ “መደመር፣ ለአፍሪካም እንበቃለን …..” እያሉ ደባብሰው የሚያልፉት ነገር አይደለም። ወይም ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ለጠየቃችው ጥያቄዎች ሌላ ጊዜ መልስ እንሰጥበታለን ተብሎ እንደታለፈው በእድር የሚቆዩ ጥያቄዎች አይደሉም። እነዚህን ጥያቄዎች ከጠቅላላ ጉባዬ ውጭ ሊመልሳቸው የሚችል ተቋም አይኖርም። አሁን ውሳኔ ካልተሰጠ ሌላ ጠቅላላ ጉባዬ እስኪደረግ ድረስ አሁን ባለንበት ነው የምንቀጥለው ማለት ነው።

እነ ገዱ በጉባያቸው ላይ የወሰኑትን አዋሳ ሄደው ማስወሰን ካልቻሉ፣ ሕዝቡ እሳት ጎርሶ ነው የሚጠብቃቸው። ከሕዝቡ ጋር ከሚጣሉ ከነ ዶ/ር አብይ መለየቱ ግድ ነው የሚሆንባቸው። ከማንም በላይ በጓደኝኘት ከነ ዶ/ር አብይ ጋር ከሕዝቡ ፍላጎት ውጭ ሊቀጥሉ አይችሉም።

የዶ/ር አብይ መንግስት ያለነ ገዱ የደሃዴኖን ድጋፍ በሙሉ ማግኘት ይኖርበታል። በፖለቲካ አመለካከት በአብዛኛው ደሃዴኖች ከነገዱ ጋር ፖለቲካዊ አመለካክታቸው ተቀራራቢ በመሆኑ፣ አዴፓን ትተው ኦዴፓን ይደግፋሉ ብዬ አልጠብቅም። ስለዚህ በአጭሩ የዶ/ር አብይ አስተዳደር የግድ የነገዱን ጥያቄ ማስተናገድ ይኖርበታል።

እነ ዶ/ር አብይ የአዴፓን ጥያቄ ተቀብለው ፣ አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች እንድትተዳደር ካደረጉና አሁን ያለው የጎሳ አወቃቀር እንደገና እንዲታይ ከተስማሙ፣ አዎን እነ ጃዋርና መሰሎቻቸው መⶐሃቸው አይቀርም። ከኦዴፓም ብዙዎች ሊቃወሙ ይችላሉ። ግን አዴፓ፣ ደሃዴንና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ስለሚደግፋችው እነ ዶ/ር አብይ በአስተማማኝ ሁኔታ መቀጠል ይቻላሉ።

እንግዲህ አዋሳ ላይ ትኩረት ሊሰጠት የሚገባው፣ በኔ እይታ ጌታችው አሰፋ፣ ማንጃሪኖ…ምናምን ሳይሆን የአዴፓና የኦዴፓ ፍጥጫ ነው። የአዋሳ ጉባዬው የኦሮሞ ፖለቲከኞች በበላይነት የተቆጣጠሩት፣ የሌሎች ማህበረሰባት ጥያቄ ያልተስተናገዱበት፣ ያኔ ሕወሃት እንደነበረው አሁን ደግሞ ኦዴድ/ኦዴፓ የበላይነቱን ያሳየበት፣ ከጎሳ ፖለቲካና አወቃቀር እንደምንወጣ የሚያሳይ ምልክትና ፍንጭ ያልታየበት ፣ በባህር ዳር የአዴፓ ጉባዬ የተወሰኑ መሰረታዊ የሕዥብ ጥያቄዎች ቁሻሻ ማጠራቂያ ውስጥ የተጣሉበት ጉባዬ ከሆነ ወገኖች የአዋሳው ጉባዬ ትልቅክ ክሽፈት ነው !!!!!