ዳግማዊት ሞገስ ለሸገር ከንቲባነት #ግርማካሳ

አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት ከንቲባ የላትም። በምክትል ከንቲባ ነው የምትመራው። የአዲስ አበባ ምክር ቤት ከአባላቱ መካክል ከንቲባ መምረጥ ሲገባው፣ ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ “የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ብቻ ሳይኮን ምክትል ከንቲባ መሆን ይቻላል” የሚል ሕግ፣ ፓርላማው፣ ሰው ትኩረት ባልሰጠበት ወቅት አጸደቀ። የአዲስ አበቤዎችን ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብትን በመጨፍለቅ።

ብዙም አልቆየም ኢንጂነር ታከለ ኡማ በምክትል ከንቲባነት፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ብቻ ሳይሆን የከተማዋም ነዋሪ ሳይሆኑ ፣ የኦህዴድ ሹመኛ ሆነው ፣ ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ ምክትል ከንቲባ ተደረጉ። ከኢንጂነር ታከለ በፊት ምክትል ከንቲባ ሆና ትሰራ የነበረችው ፣ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ በምክትል ከንቲባነቷ ቀጠለች፣ በአሰራር ክኢንጂነር ታከለ በታች ሆና።

ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ ሰሞኑን በባህር ዳር በተደርገው የብአዴን ጉባዬ፣ ክጉባዬተኛው ትልቅ ድጋፍ አገኝች። ከብዙ እጮዎች መካከል ተወዳድራ፣ የብአዴን/አዴፓ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ ብአዴን/አዴፓን ወክላ የኢሕአዴግ የፖሊት ቢሮ አባል ሆና ተመረጠች።

ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ የሸገር ሙሉ ከንቲባ ትሆን ዘንድ እጠይቃለሁ።አንደኛ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት ናት፣ ሁለተኛ የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት፣ ሶስተኛ ብቃት ያላት ናት።እርሷን ከንቲባ ማድረግ በሕግ አንጻር፣ የአዲስ አበቤዎች ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ካለመጨፍለቅ አንጻር አዋጭ ነው።አራተኛ አዲስ አበባ ሙሉ ከንቲባ ይኖራታል።

አንዳንድ ወገኖች ኢንጂነር ታከለ ኡማ ቢቀጥል ምን ችግር አለው የሚሉ አሉ። በተለይም ኢንጂነሩ የዶ/ር አብይ ወዳጅ በመሆኑ።

አስፈላጊ ከሆነ በምክትል ከንቲባነት፣ የወ/ሮ ዳግማዊት ረዳት ሆኖ መቀጠል ይችላሉ። ግን የአዲስ አበባ መስተዳደር ቁንጮ ሆነው መቀጠላቸው ግን ተገቢ አይመስለኝም። ታከለ ኡማ የሸገርን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎትን የሚያስቀድሙ ናቸው የሚል እምነት ብዙዎች የላቸውም። ሸገሮች ከአሁን ለአሁን ኢንጂነር ታከለ የዶ/ር አብይ ወዳጅ ናቸው በሚል፣ ለሸገር ህዝብ ጥቅም ያልቆሙን መሪ የሚሸከሙበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይቻልም!!!!

አዴፓ በጉባዬው አዲስ አበባ የነዋሪቿ ናት በሚል በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለዉን አቋም ግልጽ አድርገዋል። በመሆኑም የአዲስ አበባ ህዝብ ፍላጎትና ጥቅምን የሚያስጠበቅ አስተዳደር ይኖር ዘንድ በአዋሳው ጉባዬ ግፊት ማድረግ መቻል አለበት። የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነ፣ የአዲስ አበባን ጥቅም የሚያስጠብቅ ከንቲባ ያስፈላጋል። ለዚህም ነው ህዝብ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን ለከንቲባነት የምለው። !!!!!

በነገራችን ላይ ላለፉት 27 አመታት አንድ ያልተጻፈው ሕግ አለ። የብ አዴን አባል ጠቅላይ ሚኒስተርና የአዲስ አበባ ከንቲባ አይሆንም። አሁንም ይሄ ሕግ ካለም አዴፓ ይሄንን ሕግ ማስቀየር አለበት።