የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ከትግራይ እስከ አፋር ክልል እንዲሸኝ ፈቃድ ተሰጠ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

የተባበሩት መንግስታት በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ተማሪዎችን ከክልሉ እስከ አፋር ክልል እንዲሸኝለት መንግስት ጠይቋል።

የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በፃፉት ደብዳቤ፤ በትግራይ ክልል ያሉ ተማሪዎች በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠውን ሐምሌ 01/2013 ዓ.ም የጀመረውን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የእረፍት ጊዜ መጠቀም አለመቻላቸውን ይገልፃል።

በመሆኑም በመቐለ፣ አዲግራት፣ ራያ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ተማሪዎችን የተባበሩት መንግስታት ወደ አፋር ክልል አላባ ድረስ እንዲሸኝለት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና በትግራይ ያሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መጠየቃቸውን ገልጿል። ጥያቄውን የተቀበለው ዓለም ዐቀፉ ተቋም፤ አገልግሎቱን ለመስጠት የነዳጅ ፍጆታ እንዲፈቀድለት መጠየቁ በደብዳቤው ተገልጿል። ስለዚህም ጉዞውን ለማሳለጥ ሁለት (2) ታንከር ነዳጅ ለተባበሩት መንግስታት የተፈቀደ መሆኑን ያሳወቀው የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል። በትግራይ እና በአፋር ክልል መካከል ያሉ የፍተሻ ጣቢያዎች የፖሊስ አባላት ተማሪዎቹን ለሚያጓጉዙ አውቶቡሶች የይለፍ ፈቃድ እንዲሰጡም የሰላም ሚኒስቴር ጠይቋል።

በሰላም ሚኒስቴር ሚኒትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ፊርማ ሐምሌ 12 ቀን 2013 የወጣ እና ለአፋር ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የተላከ ደብዳቤ  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ከትግራይ ክልል እስከ አፋር ክልል እንዲሸኝ ፈቃድ የተሰጠበት ነው።

በደብዳቤው ላይ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመደበኛ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሃምሌ 1 ጀምሮ የክረምት እረፍት ጊዜ መስጠቱ ተጠቅሷል። ሰላም ሚኒስቴር ፥ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና በትግራይ ክልል ያሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተመድ (UN) በመቐለ፣ ዓዲግራት ፣ ራያ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ተማሪዎችን ወደ አፋር ክልል አባላ ድረስ እንዲሸኝለት ጠይቋል።

ተመድ (UN) ጥያቄውን መቀበሉ በደብዳቤው ላይ የተገለፀ ሲሆን ነገር ግን አገልግሎቱን የሚሰጥበት የነዳጅ ፍጆታ እንዲፈቀድለት ጠይቋል። በዚህም የሰላም ሚኒስቴር ፤ ተመድ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች (መቐለ፣ ራያ፣ ዓዲግራት ፣ አክሱም) ወደ አፋር ክልል አባላ እንዲያጓጉዝ ፈቃድ መስጠቱን አሳውቋል። በትግራይ ክልልና አፋር ክልል መካከል ያሉ የፍተሻ ጣቢያዎች የፖሊስ አባላት ተማሪዎችን ለሚያጓጉዙ አውቶብሶች የይለፍ ፈቃድ እንዲሰጡና ጉዞውን ለማሳለጥ ሁለት ታንከር ነዳጅ ለተመድ የተፈፈቀደ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ደብዳቤ ላይ ተገልጿል።