ወደ አፋር የገባው እና ወደ ወልዲያ ሊሰብር ያለመው የጁንታው ሀይል አይቀጡ ቅጣት እየቀመሰ ነው።

የጁንታው የህወሓት ታጣቂ ዞብል ተራራን ይዞት ወልዲያ ሊገባ ሞክሮ አልተሳካለትም ተብሏል። ዞብል ተራራ ማለት በአማራ ክልል ቆቦ ወረዳ እና በአፋር ክልል ገላዋን ያሎ ወረዳዎች መካከል ያለ የድንበር ተራራ ነው። ከአፋር ክልል ተቀጥቅጦ እግሬ አውጪ በማለት ዞብል ተራራ ላይ ያለውጊያ የሰፈረው የተቆረጠው የጁንታውን ታጣቂ ድባቅ ለመምታት የቆቦ ህዝብ ከመከላከያና ከአማራ ልዩ ሃይሎች ጎን በመሆን ትልቅ ተጋድሎ አድርጓል።

በያሎና በገላዋን የተደመሰሰው በተለይ በገላዋን እንደ ቅጠል የረገፈው የጁንታው ሀይል የተረፈው የአፋርን ክልል ጥሶ ማለፍ ስላልቻለ ያለው አማራጭ ያለውን ይዞ ወደ ዞብል ተራራ መውጣት ግዴታው ስለሆነበት ዞብል ተራራ ላይ ተቀምጦ ነበር።

ዞብል ተራራ ከቆቦ 30 ኪ፡ሜ ሲርቅ ከወልዲያ ግን ከ80 ኪ፡ሜ ያላነሰ ይርቃል ዞብል የሚመናኘው ከቆቦ ጋር እንጂ ከወልዲያ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ዞብል ተራራ ላይ ያለው የጁንታው ብጥስጣሽ ሀይል እየተመታ መሆኑ ታውቋል።

የአፋር ጸጥታ ሀይልና አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ጁንታው ጦርነቱን በከፈተባቸው የዞን አራት ግንባሮች በሙሉ ድልን በመጎናጸፍ ላይ ይገኛሉ። የተወሰኑ ቦታዎችን ላለፉት አራት ቀናት ጁንታው ለመቆጣጠር ችሎ የነበረ ቢሆንም ጀግናው አፋር በአሸባሪው ቡዱኑ ላይ በሰነዘረው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻው ከቦታው ሊያስለቅቁት ችለዋል ። ጦርነቱ በቀጠናው በከባድ መልሶ ማጥቃት እየታጀበ በመካሄድ ላይ ይገኛል

የጁንታው ሕጻናት ወታደሮች በነፍስ ወከፍ መሳሪያ ይዘው ነው እየሮጡ በመግባት የጥይት እራት ሲሆኑ ማየት ያሳዝናል፣ ተዋጉ ብለው የሚልኳቸውን ሕጻናት የሆነ የሚያስጨሷቸው ነገር አለ እንጂ በጤናቸው እንዲህ አይሆኑም የሚማረኩትም ፈዘው ነው የሚገኙት እንዲሁም አፋር ላይ ያለቀው የህወሓት ታጣቂ ወጣትን በቁጥር ለማስቀመጥ ለመገመት አይቻልም፤ በሺዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖች በየሜዳው እንደሚታዩ በቦታው የሚገኙ ምንጮች የላኩልን መረጃ ያሳያል።