ሕወሓት ለንፁዓን ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይደርስ መንገድ መዝጋቱ ተሰማ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአፋር በኩል ወደ ትግራይ ክልል የእርዳታ እህል ጭነው የሚጓጓዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሽብር ጥቃት በመፈጸም የእርዳታ መስመር እንዲዘጋ ማድረጉን የብሄራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። አሸባሪው ህወሃት ለትግራይ ህዝብ ርህራሄ እንደሌለው በተግባር እያረጋገጠ መሆኑ ተጠቁሟል።

TPLF Blocks Humanitarian Support Being Transported to Tigray Region |  Ethiopian News Agencyየብሄራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት፤ ባለፉት ሶስት ቀናት በአፋር በኩል ወደ ትግራይ ክልል በመጓጓዝ ላይ የነበሩ ምግብና ምግብነክ ያልሆኑ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 189 ከባድ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ የሽብር ጥቃት በመፈጸም የእርዳታ መስመር ዘግቷል። በዚህም ምክንያት ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑት ከባድ ተሽከርካሪዎች ለመቆም ተገደዋል።
አሸባሪው ሕወሓት የእርዳታ መስመሩን የዘጋው በአፋር ክልል ዞን አራት ፈንቲረሱ ያሎ ወረዳ በከፈተው የሽብር ጥቃት ነው። መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም በማድረግ ለትግራይ ሕዝብ ሰብዓዊ እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን ያስታወሱት ኮሚሽነር ምትኩ፤ ለትግራይ ህዝብ ምንም ርህራሄ የሌለው አሸባሪ ሃይል ግን የእርዳታ መስመር በመዘጋት ሰብዓዊ ቀውስ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
መንግስት የዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች የሚሰጡትን እርዳታ እንዳይስተጓጎልና በወቅቱ እንዲደርስ ሁኔታዎችን ቢያመቻችም አሸባሪው ህወሃት የሽብር ጥቃት ከመፈጸም አለመታቀቡ ተገልጿል። በዓለም ምግብ ፕሮግራምና ሌሎች ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በኩል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የእርዳታ አቅርቦቶች በተገቢው መንገድ ወደ ትግራይ ክልል እንዲያጓጓዙ መንግስት ሁኔታዎችን እያመቻቸ ቢሆንም በቡድኑ የሽብር ጥቃት ምክንያት እየተስተጓጎለ መሆኑ ነው የተገለጸው። (ኢ.ፕ.ድ)