በህወሓት ታጣቂዎች የሚመለመሉ ህጻናት ከ9 እሰከ 15 አመት ያሉ ልጆች ናቸው – ጄፍ ፒርስ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
May be art of 1 personአለም የህጻናት “ወታደሮችን” ጉዳይ እንዲመለከት ማጋለጥ ከጀመሩ የውጭ ጸሃፊዎች አንዱ ጄፍ ፒርስ ነው። ጸሃፊው በተለያዩ ጊዜዎች ይህንን የጦር ወንጀል ከማጋለጥ ባሻገር አሸባሪው የህወሃት ቡድንን ችላ ያለውን አለም ልክ እንዳልሆነ ማስረጃ በመጥቀስ በጽሁፎቹ ወቅሷል። ሃያላኑ እና አለም አቀፍ ተቋማት ትኩረት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አውነት ለአለም ገልጧል።
ጄፍ ፒርስ ዛሬም ህወሓት የህጻናት ወታደርን መጠቀምና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ያሉ እውነታዎችን የሚያጋልጥ ዘርዝዘር ያለ ጸሁፍ አስነብቧል።
ፒርስ በዚሁ ጽሁፉ አሸባሪው ህወሓት ህጻናትን በስፋት ለውትድርና እየመለመለ መሆኑን፤ ህጻናቱ በህወሓትታጣቂዎች ከተወሰዱ በኋላ ወደቤተሰቦቻቸው ለመመለስ መንገዱን እንኳን እንደማያውቁና በአካባቢው ያሉ እናቶችን ደብቁን እያሉ እንደሚማጸኑ፣ በገጠራማውም ሆነ በከተሞች አካባቢ ያሉ ታጣቂዎች እናቶችን እለት በእለት ምግብ እያስገደዱ እንደሚያስበስሉና እንደሚወስዱ አስነብቧል።
May be an image of 10 people, child, people standing and outdoorsጄፍ ፒርስ በጸሁፉ ካነሳቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም …
👉 በህወሓት ታጣቂዎች የሚመለመሉ ህጻናት ከ9 እሰከ 15 አመት ያሉ ልጆች ናቸው፤
👉 በተለይ ከማዕከላዊ ትግራይ በታጣቂዎቹ ተይዘው ካሉ ህጻናት መካከል አብዛኛዎቹ የት እንዳሉ፤ ወደወላጆቻቸው ለመመለስ ቢፈልጉ እንኳን የቤታቸውን መንገድ አያውቁም፤
👉 የሚያውቁትም ቢሆን መመለስ አይችሉም፤ ምክንያቱም በመንገዳቸው ላይ የህወሓት ታጣቂ ቢያገኛቸው ያስራቸዋል፤ አሊያም ይገድላቸዋል፤
👉 ህጻናት ወታደሮችን እንደ ህዝብ ድጋፍ ማሳያ አድርጎ አሞካሽቶ በዘገባ ላይ ማውጣት ወንጀል መሆኑን የተረዳው የኒዮርክ ታይምስ ዘጋቢ ፎቶዎቹን ወዲያው አጥፍቷቸዋል፤ ይህ ግን ከሙያ ስነ ምግባር መጣስ አያድነውም፤
👉 ህወሓት ህጻናትን፣ ንጹሀንን በውትድርና እንደሚጠቀም ለመሸፋፋን መሞከር ራስን ከግምት ውስጥ ያስጥላል፤ ምክንያቱም የህወሓቱ መሪ በህዳር ወር ላይ ሁሉንም የትግራይ ህዝብ ህጻናትንም ጭምር ወደጦርነቱ በማሰለፍ ጦርነቱን ህዝባዊ እናደርጋለን ሲል መናገሩ አይዘነጋምና ነው፤
👉 ደብረጺዮን ሁሉም የትግራይ ህዝብ በጦርነቱ ይሳተፋል፤ ጦርነቱ ህዝባዊ ይሆናል፤ ህዝባዊ ጦርነት ማለት በንጹሀን የሚመራ ከህጻን ጨምሮ ሁሉም የሚሳተፍበት ይሆናል ማለት ነው ብሎ ተናግሮ ሲያበቃ አሁን ላይ ትግራይ ተርባላች፤ ትግራይ ውስጥ ንጹሀን ተገድለዋል ቢባል ማን ሊሰማ፤ ምን ያህልስ ተገቢ ሊሆን ይችላል፤
የፒርስን ሙሉ አርቲክል ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ያገኙታል