በትግራይ ዕርዳታ ለማድረስ የታጠቁ ኃይሎች እንቅፋት እንደፈጠሩ የዐለም ምግብ ድርጅት ገልጧል፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 በትግራይ ክልል ርሃብ ተከስቷል – የተመድ አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ

የተመድ አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ በክልሉ ርሃብ ተከስቷል ሲሉ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር አውጀዋል፡፡ ተወያዮቹ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የኤርትራ ወታደሮች ባስቸኳይ ከክልሉ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በትግራይ ክልል 350 ሺህ ሕዝብ የርሃብ አደጋ እንደተጋረጠበት የዐለም ምግብ ፕሮግራም፣ ዩኒሴፍ እና የዐለም ምግብና እርሻ ድርጅት ዛሬ በጋራ ባሰራጩት መረጃ አስጠንቅቀዋል፡፡ ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ በክልሉ ለተከሰተው ከባድ የምግብ ዕጥረት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የጠየቁት ድርጅቶቹ፣ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ሕዝብ ባንድ ሀገር ውስጥ ባንድ ጊዜ ለርሃብ ሲጋለጥ ባለፉት 10 ዐመታት የመጀመሪያ ነው ብለዋል፡፡

ለገጠራማ አካባቢዎች ዕርዳታ ለማድረስ የታጠቁ ኃይሎች እንቅፋት እንደፈጠሩ የዐለም ምግብ ድርጅት ገልጧል፡፡

የአሜሪካ ዩኤስአይዲ እና የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ እና ልማት ዕርዳታ ከፍተኛ ሃላፊዎች በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡ ተወያዮቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታን እንዳያሰናክልና ግጭት እንዲያቆም እና ርሃብ እንዳይከሰት ለማስቀረት ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ ጫና እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡